mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ጠንካራ ይለፍ ቃል እና ወቅታዊ ቅያሬ

mejemer computer strong password

ብዣኛው ሰው ዊንዶውስ እንደሚጠቀም ይታወቃል። በዊንዶውስን ብዙ ስለሚጠቀምበት በዛው ልክ ደግሞ ለጥቃት የተጋለጠ ነው፡፡ የኮምፕዩተር ጥቃትን ለመቀነስ የተጠቃሚው አጠቃቀምና ባህሪ ወሳኝ ነው። የተጠቃሚው ባህሪ የአጠቃቀም ባህል ሊያስጠቃውም ሊያድነውም ይችላል። የሚከተሉት ነጥቦች ሁሉንም አይነት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ደህንንነትን ከፍ አድርጎ ለመጠቀም የሚረዱ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ዊንዶውስ ብዙ ቀዳዳ ስላለው በሚያስፈልግ ጊዜ በተለይ ዊንዶውስ እያልሁ እጠቅሳለሁ።

የመጀመሪያው ጥንቃቄ የመግቢያውን ጠንካራ ማለፊያ-ቃል መስራት ነው፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ማለፊያ ቃሁን አልፎ አልፎ መቀየር ነው፡፡ ማለፊያ ቃል ከሌላ ሰው ጋር የማይጋሩት የግል ብቻ ነው። ማን ኢንተርኔት ላይ እንደሚያፈነፍን ስለማይታወቅ ማለፊያ ቃል አልፎ አልፎ መቀየር አለበት። ለምሳሌ YezihAmet#2014QrtOne1 (የዚህ አመት ቁጥር 2014 ሩብ-አመት አንድ) ማለት ነው። ትልቅና ትንሽ ፊደሎች፣ ቁጥሮችና ምስል አለበት። እንደምታዩት ጠንካራ ምሳሌ ነው፡፡ ሌላ ጊዜ ከሶስት ወራት በኋላ ሲቀየር የመጨረሻወቹን አራት አሃዛት ብቻ መቀየር ይቻላል። አመቱ ሲያልቅ ደግሞ 2014 ይቀየራል። የራስወን የሚስማማወትንና የማይረሱትን ቅንብር መፍጠር ይችላሉ።

ተመሳሳይ ማለፊያ ቃል በየቦታው መጠቀም ለጥቃት ያጋልጣል። ለምሳሌ ለጉግል ኢሜይልና ለባንክ መግቢያ በአንድ አይነት ማለፊያ ቃል መጠቀም ለጥቃት ያጋልጣል። የኦፕሬቲንግ ሲስተም አያያዝና ተጨማሪ ሶፍትዌሮች፤ በተለይ ዊንዶውስ፤ ላይ ተጨማሪ ሶፍትዌሮች በየጊዜው ይዘምናሉ። የሚዘምኑት ደህንነትን ለመጨመርና ለመጠቀም የበለጠ ምቹ እንዲሆኑ ነው። በተለይ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ የዘመነ መሆኑን ማረጋገጥ የተጠቃሚውን ደህንነት ከፍ ያደርጋል፡፡ መጠቀሚያ ሶፍትዌሮችንም መዘመን የሚያስፈልጋቸው ከሆነ አልፎ አልፎ መፈተሽ ይጠቅማል። ጊዜቸው ያለፈባቸውንም ወይም መዘመን ያቆሙ ሶፍትዌሮች ካሉ ማስወጣት ቀዳዳ መድፈን ነው። ኮምፕዩተር ልክ እንደ መኪና እንክብካቤና ክትትል ያስፈልገዋል።

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!