mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ኦፐሬቲንግ ሲስተም ምንድነው?

mejemer computer operating system

ፐሬቲንግ ሲስተም ዋና ዋና ሚና ካላቸው አንዱ ክፍል ነው፡፡ ብዙ ሰወች ኦፐሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌር አደባልቀውና አደናግረው ይነጋራሉ፡፡ ሁለቱም ስለሚለያዩ በቀጥታ ትክክል አይደለም፡፡ ባጭሩ ዋናው የኦፐሬቲንግ ሲስተም ስራ የኮምፕዩተር የውስጥና የውጭ አካል እና ሶፍትዌሮች በአንድ ላይ ተጣጥመው ወይም እጅና ጓንት ሆነው ተባብረው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡ ከኦፐሬቲንግ ሲስተም ውጭ ኮምፑተርን አስነስቶ ስራ ለማከናወን ያስቸግራል፡፡ ኦፐሬቲንግ ሲስተሙ ስራውን የሚጀምረው ገና ኮምፕዩተሩ እንደተቀሰቀሰ ነው፡፡

ለምሳሌ ኮምፕዩተር ሲቀሰቀስ የሚያቃስተውና ጊዜ የሚወስድበት መጀመሪያ ማጣራት ያለብት ስራ ስላለው ነው፡፡ የውጭና የውስጥ ሃርድዌሮቹ መስማማታቸውንና መስራታቸውን ማወቅና መቆጣጠር ስላለበት ነው፡፡ ካወቀና ከተቆጣጠረ በኋላ አንገብጋቢ ስህተት ከተገኘ ኮምፕዩተሩ መልእክት ያሳያል ወይም ይቆማል፡፡ ኮምፕዩተሩ ከጀመረ በኋላም ኦፐሬቲንግ ሲስተሙ በዚሁ ተግባር ይቀጥላል፡፡ ከኦፕሬቲንግ ሲስተም ውጪ ሃርድዌርና ነጠላ ሶፍትዌር ብቻቸውን ምንም አያፈይዱም፡፡

ፕሬቲንግ ሲስተም፤ በኮምፕዩተር ተግባር እይታ የሁሉም ትእዛዝ ጥርቅሞች አስተዳዳሪና ተቆጣጣሪ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ዊንዶውስ፣ ማክ እና ሊነክስ ዋና ዋና የሚባሉት ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ናቸው፡፡ ዊንዶውስና ማክ በገንዘብ የሚገዙ ናቸው፡፡ ሊነክስ ግን ነጻ ነው፡፡ የነጻ ምንጭ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ይባላል፡፡ ሊነክስ በመቶ የሚቆጠሩ ዝርያወች አሉት፡፡

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!