mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

የመስራት ባህሪ እና ልምድ

mejemer ethiopia amaharic working habit

ቶ ጀምሬ የሆነ ቦታ ለመሄድ አስበ፡፡ መንገዱን ሲያየው ግን ደስ አላለውም፡፡ መሄድ እና ማወቅ ያልበት ጉዳይ ስለሆነ የግድ ቀስስስ እያለ ሄደ፡ ሲደርስ ግን ዘግይቶ ደረሰ፡፡ ማወቅ የነበረበት አንዳንድ ነገር አመለጠው፡፡ ዘግይቶ መድረስ ዋጋ ያስከፍላል፡፡ አሁን የውኋና ቲሌቪዥን እውነተኛ ታሪክ ልንግራችሁ፡፡ ከውጭ ሃገር ወደ አገር ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የሄድኩ ጊዜ ነበር፡፡ ቆይቷል፡፡ እንደምታውቁት ኢትዮጵያ ውስጥ ቤተሰብ ይጠያየቃል፡፡ ህጻናት አሉ፡፡ ትልልቆች አሉ፡፡ ቡና ይፈላል፡፡ ጎረቤት ይሰባሰባል፡፡ ረጅሙን ታሪክ አጭር ለማድረግ፤ በጨዋታ መካከል ቢሆንም ፊት ለፊት ለብቻው ቁጭ ብሎ የሚያወራ ሰው ሰራሽ ሳጥን ያስፈልግ ነበር፡፡

አሁን አንዱን የእህቴን ልጅ ቴሌቪዢንና አንቴና እንግዛ እንዴ ብዬ ስጠይቀው እሺ አለኝ፡፡ በማግስቱ አካባቢ ይመስለኛል ተያይዘን ወደ ሱቅ፡፡ ትንሽ ዘወር ዘወር ብለን ካየን በኋላ ቴሊቪዢን፣ አንቴና፣ ሽቦና አንዳንድ ተጨማሪ ነገሮች ገዛን፡፡ አንቴና ስላችሁ ግን ባለሳህኑ አንቴና ሳይሆን ባለቅርንጫፉ አንቴና ማለቴ ነው፡፡ ከፍለን ከጨረስን በኋላ፤ ነጋዴው ሽቦውን ለክቶ ቆረጠና ሲጠቀልል ልክ እንደገመድ መጠቅለል ጀመረ፡፡ በድንጋጤ ቆይ ቆይ ቆይ ስለው በጣም ተገረመና ቀጥ ብሎ ቆመ፡፡ ድምጼ ሳላስበው ከፍ ብሎ ነበር፡፡ ምን ነካህ? ምንድነው አለኝ፡፡ እራሴን ለመረጋጋት ከሞከርኩ በኋላ "ሽቦው እንደዛ ሲጠቀለል ይበላሻል አልኩት፡፡ ምን! እኔ ከ20 አመት በላይ እዚህ ስራ ላይ ቆይቻለሁ፡፡ እስከዛሬ ድረስ አንድም ሰው ተበላሸብኝ ብሎ የወቀሰ የለም አለ፡፡ አሁን እኔ ምልክቱ ገባኝ፡፡

በውስጤ ግን፤ ያላየኋቸውና የማላውቃቸው ሰወች አሳዘኑኝ፡፡ የተጎዳ ሽቦ በገንዘባቸው እየገዙ ጥራቱ ያነሰ ምስል ያያሉ ማለት ነው ብየ አዘንኩላቸው፡፡ የሽቦውን ጸባይና አሰራር ሁሉም ሰው ማወቅ አይችልምና የነሱ ጥፋት አይደለም፡፡ ለማንኛውም በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ፤ እስካሁን ድረስ፤ አይደልም ሽቦ ለሰው ህይዎት ያለን ክብር አነስተኛ ነው፡፡ አሁን እኔ ሌላ ጭቅጭቅ ውስጥ መግባት አልፈለኩም፡፡ ወደሱ ጠጋ ብየ፤ እየውልህ ወንድም እንደምታውቀው የኮአክስ ሽቦው ልብስ ከሽንኩርት ልጣጫ ጋር ይመሳሰላል፡፡ የተደራረበ ነው፡፡ የመጀመሪያው ለምሳሌ ውጫዊ ርጥበትና ጨረር መከላከያ ነው፡፡ ቀጥሎ ያለው ደግሞ ዋናውና ተከታዩ ሲግናል እርስ በርስ እንዳይጋጭ የሚከለክል ነው፡፡ መጨረሻ ላይ ያለው የተዘጋ ቱቦ ደግሞ፤ ዋናው ሲግናል በሽቦው ሲተላለፍ እንዳይባክንና ከመንገድ እንዳይወጣ የሚረዳ ነው፡፡ እንዲህ እያለ ይቀጥላል፡፡ ስለዚህ እንደገመድ ሲጠቀለል ከውስጥ ያለው ዋናው ማስተላለፊያ ሽቦ ስለሚጎዳ ጥሩ ምስል አያስተላልፍም፡፡ ብትቀይርልን ደስ ይለኛል አልኩት ረጋ ብዬ፡፡

አንተ እንደምትለው አልጎዳሁትም እኮ ብሎ ትንሽ አስተባበለ፡፡ የተግባባን ይመስላል፡፡ ዋናው የሚፈለገው ውጤት ይኸ ነበረ፡፡ ረጋ ብሎ መናገርና ጥሩ ውጤት ላይ መድረስ፡፡ መጨረሻ ላይ ግን ከቀየረ በኋላ ቀስ ብሎ ሽቦው እንዳይጎዳ አድርጎ ጠቅልሎ ሰጠን፡፡ እቤትም ሄደን ከገጣጠምን በኋላ ቴሌቪዥኑ ነብስ ዘራበት፡፡ ኤሌክትሪክ ሲጠፋም አብሮ ጸጥ ይል ነበር፡፡

አሁን እናንተ ይኸን ስትሰሙ የሆነ ጥያቄ የላችሁም? እኔ አለኝ! የጥያቄ ነገር ሲነሳ ጀመሬን አስታውሳለሁ፡፡ ጀምሬ እኮ ነው፡፡ ከሆነ ስብሰባ በኋላ መጨረሻ ላይ ጥያቄ ወይም አስተያየት ያላችሁ ተብሎ ተጠየቀ፡፡ አንዳንድ ሰወች ጥያቄያቸውን ጠይቀው ጨረሱ፡፡ ጀምሬ ግን ጸጥ ብሎ ነበርና መጨረሻ ላይ ከማን አንሳለሁ ብሎ ድንገት እጁን አወጣ፡፡ የስብሰባው መሪ እሺ አቶ ጀምሬ ጥያቄዎት ምን ነበር ሲለው፤ አይ ጌቶች እኔኮ ጥያቄ የለኝም ለማለት ነው እጄን ያወጣሁት አለ ይባላል፡፡ እኔ ግን አንዲት ጥያቄ አለችኝ፡፡ ያ ሲጠቀለል የተበላሸ ሽቦ የት ደረስ? የት ገብቶ ይሆን? ነጋዴው ለሌላ ሰው ሽጦት ይሆን? አላውቅም፡፡ ሽቦው እንዲቀየር መጠየቄ ግን የኔ ጥፋት አይደለም፡፡ ለሌላ ሰው ሸጦት ከሆነ ደግሞ ከኔ ቁጥጥር ውጭ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፤ አሁን እኔ ሃገር፣ ሰውና እውቀት እያነጻጸርኩ አይደለም፡፡ እስካሁን የነገርኳችሁ ገጠመኝ አቃቂር እንዲወጣለት አልፈልግም፡፡ አላማውም ለዚህ አይደለም፡፡ ሁሉም ነጋዴ አንድ አይነት ነው አላልኩም፡፡

በተደጋጋሚ ያየሁትንና ያጋጠመኝ ስለሆነ ለናንተ ለማካፈል አስቤ ነው፡፡ ድምጽና ምስል በጣም ስለምወድ አንብቤ ያወኩት ነው እንጂ የተለየ ትምህርት የለኝም፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥም ቢሆን አይነቱና ብዛቱ ይለያያል እንጂ የሚነበብ አይጠፋም፡፡ በተለይ ደግሞ አንድ ሰው ስራየ ነው ካለ፡፡ አምብቡት! የገባ ያገለግላል የሚል አንድ ወዳጅ አለን፡፡ በሚቀጥለው ዙር ላይ ሚስኪኑ ሽቦ በየቦታው የመበላቸት እድሉ ትልቅ ስለሆነ በዝርዝር አቀርባለሁ፡፡ የስራ ባህላችን ጋር ግንኙነት አለው፡፡ ሽያጭ ላይ ብቻ ሳይሆን፤ ተዘርግቶ በስራ ላይ ሲውል እንዴት እንደተበደለ መጥቀሴ አይቀርም፡፡ የውኋውም ታሪክ ገና ይመጣል፡፡ የዝግጅቱ ስም ውኋና ቴሌቪዢኑ ስለሆነ ማለቴ ነው፡፡ እዚህ ድረስ ስላነበቡ አመሰግናለሁ! መልካም ውሎ መልካም ምሽት!!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!