mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና
9 Apr 2024
በቅርብ ደባልቄ እና ላዩሽ

ባልቄ አውቶቡስ እየጠበቀ ነው፡፡ ሰው መተቸት ይወዳል። አካባቢ ማንበብ ይችላል። ቀዳዳ መድፈን እና ጎደሎ መሙላት ልማዱ ነው። ምን አጋጠመው? ደባልቄን ይወቁት!
(2013 ተከውኖ 2024 ላይ የታረመ ድንቅ ልብ-ወለድ)

ተጨማሪ

እጆች ይሰራሉ

ለሚሰራ እጅ

ምሳሌ አንድ ሰው ት/ቤት ገብቶ እጁ መጻፍ ይለምዳል። ከመጻፍ በኋላ ሃኪም፣ መሃንድስ፣ አስተማሪ፣ ነጋዴ፣ ገበሬ፣ ጸሃፊ፣ ከዋኝ ወዘተ ይሆናል። ለተለያዩ ችግሮች መፍትሄ ያበጃል። አዕምሮውን ለሚረባ ፈጠራ ያሰራዋል። እጃቹም አብሮው ይከተላሉ። እከሌ ደግ እና ታታሪ ነው! እከሌ ጥሩ ልምድ አለው የሚባለው ለዚህ ነው። አእምሮው ፈጥሮ፤ እጁ ሰርቶ ያሳያል።

ተጨማሪ

ልብ ይወዳል

ለሚወድ ልብ

ብ ከስሜት ጋር የተገናኘ ስለሆነ ውስብስብ ነው ይባላል። የሆነ ነገር ከሰማን እና ካየን በኋላ እንደ አይነቱ ልባችን ይሰማዋል። ልብ ግን ይሰማዋል እንጂ አያስብም። በልቡ የሚመራ ሰው ችግር ያባዛል። በልብ መመራት ማለት ለመወሰን ከአዕምሮ በፊት ልብን ማስቀደም ማለት ነው። ብልህ ልብ ከአዕምሮ ጋር ይተባበራል።

ተጨማሪ

እዕምሮ ያስባል

ለሚያስብ አዕምሮ

ዕምሮ ሲቀድም እጅ ትክክለኛ ነገር ይነካል። ልብ ተገቢ ርህራሄ ያሳያል። አፍ ሚዛናዊ ቃላት ያወጣል። አንድ ህዝብ በሰላም መኖር እንዲችል መከባበር ምን እንደሆነ ተምሮ ማደግ አለበት። የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ጠላት ኋላ ቀር አስተሳሰብ ነው። የአንዲት ሃገር እድገት እና ውድቀት በህዝቧ አዕምሮ አቅም ይለካል። ከሌለህ የለህም!

ተጨማሪ

እንኳን ደህና መጡ!

ለሚሰሩ እጆች፣
ለሚወድ ልብ
ለሚያስብ አዕምሮ፤
mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና!

ተጨማሪ

ከእኔ ጋር ይጓዙ!

እንኳን ወደ "መጀመር" መጡ!

ላም! ፋንታው እባላለሁ፡፡ ህይዎት ከባድ ትመስላልች። ልብ ለሚል ሰው ግን ከባድ አይደለችም። ለምሳሌ እንክርዳድ ከስንዴ ለመለየት በአይናችን ማየት በቂ ነው ። ክፉ እና ደግ ነገር ለመለየት ደግሞ አዕምሮአችን ማየት መቻል አለበት። የአይን እይታ እና የአዕምሮ እይታ ይለያያል። አዕምሮ በተከታተይ ልምምድ ይፈልጋል። የሚሰሩ እጆች፣ የሚወድ ልብ እና የሚያስብ አዕምሮ ካለን ግን በቀላሉ ይታዩናል። በዚህ አይነት መርህ ሁላችንም ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ የተሻለ ሰው መሆን እንችላለን። ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ከኔ ጋር ይጓዙ!

ተጨማሪ