mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ልጄ ነው ይበልህ!

mejemer ethiopia amaharic look up

እሱ ያውቃል ብለህ፣
አንገትህን ደፍትህ፣
ፊትህን ደብቀህ፣
እንዴት አርጎ ይስማህ፣
እንዴት አርጎ ይይህ፣
ልጅህ ነኝ አላልከው ቀና ብለህ አይተህ!

መዘምን አለፈህ፣
መሰልጠን ቀረብህ፣
እሱ ያውቃል ብለህ፣
አንገትህን ደፍተህ፣
በጸሎትህ ፀንተህ፤
በልመና አምርረህ፤
ት/ቤት ሄደህ፤
አተርፋለሁ መስሎህ፤
ግዜህን አቃጥለህ፤
እድሜህን ጨርሰህ፤
እንዴት አልታየህም አንድ እርምጃ ሄደህ?
ለራስህም ሆነ ወድምና እህትህ
ወይም ለሃገርህ፤
ምን ጠቀምኩኝ ብለህ
ወደታች እያየህ እንዴት ታውቀዋለህ?

መሬቱ እንደሆነ ምንም አይነግርህም፤
መደበቂያህ ሆኖ ስትኖርም ስትሞትም።

ቆልፎ ይዞሀል ሰነፉ ባህልህ፤
ወይ ባስተሳሰብህ፤ ወይ ባስተዳደግህ፣
ቄስና ሸሆቹ ፈዛዛ አድርገውህ፤
ወይ እናትህ ደርሳ አላሰተማረችህ፤
ወይ እድሜህ ሲገፋ በራስህ አልታየህ፤
ወደታች እያየህ እንዴት ታውቀዋለህ?

ቀና ብለህ እየው፣
ባየሩ በጉሙ ሲንሳፈፍ ካየኸው፤
ያንተ ልጅ ነኝ በለው፤
ወስነህ ንገረው፣
ሌላ ጊዜም ቢሆን እንዳታስቸግረው
መልሱንም አዳምጠው፡፡

ድርሻና ሚናህን ያኔ ታውቀዋለህ፣
ቀና ብሎ ማየት ትለማመዳለህ፣
ብቻህን እንደሆንክ ምልክት ታያለህ፣
ከራስ በላይ ንፋስ መሆኑን ታውቃለህ፣

አይደፋ አንገትህ፣
ቢሆንም ላባትህ፣
ቀና ብለህ እየው ፈጣሪህ ይኩራብህ፤
ልጄ ነው ይበልህ፣
ከሰማና ካየህ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!