ሰላም! ፋንታው እባላለሁ፡፡ ኢትዮጵያ እንዴት ብላ ማደግ ትችላለች እያሉ አስበው ያውቃሉ? አስተሳሰብዎ አንደኛ ደረጃ እንዲሆን ይፈልጋሉ? ለሃገሬ ምን ላርግ እያሉ ውስጥዎ ይቃጠላል? አስተሳሰብዎን ማስተዳደርና መቆጣጠር ይፈልጋሉ? ወይስ እንደ ነገሩ ልክ እንደ እንሰሳት በእግራችን ተንቀሳቀስን ውለን ካደርን በቂ ነው? እንግዳውስ ወደ ትክክለኛ ጣቢያ መጥተዋል፡፡ ዋናው አላማየ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ተከባብረው በሰላም እንዴት መኖር እንደሚችሉ በቀላሉ ለማስረዳት ነው፡፡ የሰለጠነ አስተሳሰብ ለማዳበር፤ ከራሴ ጀምሮ ማንም ሰው ቢሆን አቅጣጫ እና ልምምድ ይፈልጋል፡፡ ይኸን አቅጣጫ ለማሳየት የተቻለኝን ልባዊ ጥረት አደርጋለሁ፡፡
መፍትሄ ተኮር ለጨለማ መብራት፤የአንዲት ሃገር ክብር የሚለካው የዜጋዋ ጠንካራ ባህሪ እና ስልጣኔ በተግባር ሲታይ ነው፡፡ ሃይማኖት እና ታሪክ መሰረት ናቸው። ባህሪ እና ስልጣኔ ወቅታዊ ሚና አላቸው፡፡ አሁን ለምሳሌ ኢትዮጵያ ድሃ ሃገር ነች ይባላል፡፡ ኢትዮጵያ ግን ልክ እንደ ሃገር ድሃ ነች ብየ እኔ አላምንም፡፡ የሰው ባህሪ እንጂ የሃገር መጥፎ የለውም፡፡ ልክ እንደ ህዝብ ግን አስተሳሰባችን እንከን ስለበዛበት ኢትዮጵያን ድሃ መስላለች፡፡ የኢትዮጵያ እድሜ ከ 3ሺህ ዓመት በላይ ነው ይባላል፡፡ ይኸን የሚመጥን የረቀቀ እና የሰለጠነ አስተሳሰብ ሊኖረን ይገባ ነበር፡፡
ለምሳሌ....፤
መከባበር ከፍቅር ይቀድማል ፍቅር ያሸንፋል ይባላል፡፡ ለዘፈን እና ለመዝሙር ይመቻል። መከባበር ግን ከፍቅር ይቀድማል፡፡ በመስራት እና በመከባበር እንጂ በፍቅር ያደገ እና የሰለጠነ ዜጋ በታሪክ የለም፡፡ አንድነት በእውቀት አንድነት ሃይል ነው ይባላል፡፡ መጀመሪያ ግን የልብ ውህደት እና የአዕምሮ አንድነት የሚገነባ በቂ እውቀት በቦታው መኖር አለበት፡፡ አንድ እንሁን ማለት ተጨፍልቆ አንድ አይነት ዳቦ ይውጣን ማለት ሳይሆን እንከባበር ማለት ነው። ለመከባበር ግን እውቀት ይፈልጋል። ማየት ከመስማት ይበልጣል በጆሮ ከሰማነው ይልቅ በአይን የምናየው ይበልጣል፡፡ ይኸን ለይቶ ለማወቅ ከልብ ስሜት ይልቅ አዕምሮ መጠቀም ከስህተት ያድናል፡፡ ስንሰማው የሚወደድ ስናየው ክብር ይገባዋል ማለት አይደለም፡፡ሁሉም ነገር ጥቁርና ነጭ ነው ማለቴ አይደለም፡፡ በዚሁ ልክ ደግሞ ቆንጆ አስተሳሰብ ያለቸው ኢትዮጵያውያን እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ጠላት ኋላቀር አስተሳሰብ ነው፡፡ ማስተካከል ያለብን ነገሮች ብዙ ስለሆኑ ጊዜ ይወስዳሉ፡፡ ከአሁኑ መጀመር ግን ጥሩ ምርጫ ነው፡፡ ስለዚህ ይኸን ልዩ ጽሁፍ አይተው እና አንብበው ከወደዱት በተግባር ይሞክሩት፡፡ ጽሁፉ በኢትዮጵያዊያን ላይ ያተኮረ ቢሆንም ላደጉ እና በማደግ ላይ ላሉ ሃገሮችም ይጠቅማል፡፡ መጀመር ዶት ኮም ጣቢያ የትምህርት መስጫና የሞራል መገንቢያ ጣቢያ ነው፡፡ በትርፍ ጊዜዬ ከምሰራቸው ስራወች አንዱ ነው፡፡ ሙያየ አይደለም፡፡ ሞኝ ውኃ ሲወስደው ይስቃል እንደ ሚባለው ሆነን እንዳንቀር በማሰብ ነው፡፡
መጀመር ጣቢያ ልክ እንደ ይዘቱ ዘመናዊ ነው፡፡ ሃሳቦቹ የቤት ናቸው፡፡ አዲስ ባይሆኑም ልዩ ናቸው፡፡ ቤት ውስጥ የተሰራ የሚጥም ምግብ አይነት እንዲሆን የተቻለኝን ልባዊ ጥረት አድርጌአለሁ፡፡ ይዘቱ ንጹህ እና ግልጽ የሆነ ቆንጆ አስተሳሰብ ነው። መጀመር!
ከትላንት ይልቅ ዛሬ ሁላችንም የተሻለ ሰው መሆን እንችላለን!
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች