ልባችን ከስሜት ጋር የተገናኘ ስለሆነ በቃላት ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን የሆነ ነገር ስናይ እና ስንሰማ እንደ አይነቱ ልባችን ላይ ተጽዕኖ አለው። የምንወደው ሰው ሲቀርበን ልብቻን ይደሰታል። ፈገግ ብለን ናፍቆት ለማጋራት እንፈልጋለን። የስጋት እና ድንጋጤ ስሜት ሲሆን ደግሞ ልባችን ይፈራል። የሆነ አደጋ ሊደርስ ይችላል ተብሎ ሲወራ ሰምተን ሊሆን ይችላል። መጥፎ ነገር ደርሶ ስናይ ደግሞ ሃዘን ይሰማናል። የምንወደው ተለይቶን ሊሆን ይችላል። በግላችን ደስ የሚለን ሃሳብ በሌላ ሰው ሲገለጽ ከሰማን እምነታችን ከፍ ይላል። አሁን እኔ የማላውቀው ሌላም የልብ ሚና ይኖራል።
የሰው ልጅ በልቡ ስሜት ብቻ ተመርቶ መወሰን ሲጀምር በራሱ ላይ ስህተት ይጨምራል። ለምሳሌ ዛሬ የተሰማን ትንሽ ቆይቶ ሊቀየር ይችላል። አሁን አደጋ መስሎ የተሰማን ነገ የምናልፈው ፈተና ብቻ ሊሆን ይችላል። ዛሬ የወደድነው ዘላቂ ላይሆን ይችላል። ደስ ለሚለን ነገር የዘፈነልን ሰው እውነቱን ላይሆን ይችላል። ልባችን የሚያየው በመስኮት መስታዎት ላይ የሚፈስ የዝናብ ውኋ ነው። ከቤት ውስጥ ሆነን ውኋውን እናየዋለን እንጂ መንካት አንችልም። በልብ መመራት ማለት ለመወሰን ከጭንቅላት በፊት ልብ ማስቀደም ማለት ነው። የመጨራሻውን ውሳኔ መወሰን ያለበት ግን ጭንቅላታችን ነው።
አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ልብህን ተከተል ይባላል። ዞሮ ዞሮ ግን ብልህ የሆነ ልብ ከጭንቅላት ጋር ይተባበራል። ምክንያቱም ልባችን እርህራሄ ጭንቅላት ደግሞ ብልሀት አለው። በልብ ብቻ ከሆነ ምክንያት አናይም። በጭንቅላት ብቻ ከሆነ ደረቅ ያደርገናል። እርህራሄ እና ብልሀት ያለው ሰው ሆኖ ለመገኘት ልብ እና ጭንቅላታችን ተባብረው እንዲሰሩ መፍቀድ አለብን። ሁለቱንም አመዛዝኖ መጠቀም ለጋራ ችግሮቻችን ስር ነቀል መፍትሄ መፈለጊያ መብራት ነው።
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች