mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

የሚወዱትን ስራ በዘዴ ያግኙት!

mejemer get the job introduction

ሚወደድ ስራ ማግኘትን የመሰለ ነገር የለም። የዚህ አይነት ስራ ማግኘት ደስተኛ ያደርጋል ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱም ጥሩ እና ሥራ ማግኘት ለደመወዝ ብቻ ሳይሆን በራሱ በስራው እርካታ ለማግኘት እና እድገት ለመጨመር ነው። ገና ሲጀመር ሥራ የማግኘቱን ሂዴት ስኬታማ ለማድረግ እራሱን የቻለ አካሄድና ስልት አለው። ይህ የሥራ አፈላለግ ስልት ውጭ በሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ላይ ያተኮረ ነው። ሆኖም ግን አማርኛ ለሚችል ለውጭ ዜጋም ቢሆን ሊጠቅም ይችላል። ምናልባት በማደግ ላይ ያሉ ሃገሮች ይኸን የሥራ አሰጣጥና አፈላለግ ስልት ሙሉ በሙሉ አይጠቀሙበት ይሆናል። ባደጉ ሃገሮች ውስጥ ግን ስልቱ የተለመደ ነው፡፡

ስለዚህ ማንኛውም ዜጋ አገሩ ውስጥም ሆነ ሌላ አገር ቢኖርም፤ እዚህ ጽሁፍ ላይ የተጠቀሰውን የሥራ አፈላለግ ደንብና ስርአት ቢያውቅ ይጠቅመዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ እርስዎ ስልቱን በትክክል ከተጠቀሙበት ከአንድ ስራ በላይ ሊያገኙ ስልሚችሉ ስራ መምረጥ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ እኔ ባንድ ወቅት ላይ ሁለት ሥራዎች አግኝቼ አንዱን የተሻለውን ልመርጥ ችያለሁ፡፡ ስራ ሲመርጡ ግን ወዳጅና ዘመድ ማማከር ምርጫውን ቀላል ያደርገዋል፡፡

ይህ ሊሆን የቻለው ሌላ ሥራ ላይ እያለሁ ቢሆንም ሶስት ዓመታት ሙሉ የተሻለ ሥራ ፍለጋ ላይ ነበርኩ። በዚህ ጊዜ ውስጥ የተለያየ ትምህርት ወስጃለሁ፤ ስህተቶችም ሰርቻለሁ፡፡ የመጀመሪያም ሆነ የተሻለ ሥራ ለማግኘት ቋሚ የሆነ ህግና ደንብ ወይም የስራ አፈላለግ ህግ የለም፡፡ እንደ ሁኔታው ይለያያል፡፡ መሰረታዊ አካሄዱ ግን ይመሳሰላል፡፡ በግሌ የማውቀውንና የወሰድኩትን ልምድ ለሌሎች ባካፍል ግን በጣም ደስ ይለኛል፡፡

እዚህ መጀመር ጣቢያ ላይ የቀረበው የስራ አፈላለግ ስልት የተጻፈው በአንድ ንጋት ወይም ምርምር አይደለም፡፡ ውጤትም ለማግኘት ከፈለጉ በስልቱ መሰረት ልምምድ፣ ክትትልና ትኩረት ማድረግ አለብዎት፡፡ ስልቱን በቅደም ተከተል አንብበውና ተረድተው በተግባር ከተረጎሙት ስራ የማግኘቱ ዕድል ይሰፋልዎታል! በሦስት አመታት ጊዜ ውስጥ ከመቶ በላይ ማመልከቻዎች ልኬ ወደ በርካታ ቃለ ምልልሶች ተጠርቼ ነበር፡፡ በደንብ እየታሸሁኝና እየበሸቅሁ ስህተትም ሆነ ትምህርት ወስጃለሁ፡፡ ስለዚህ እርስዎ ስልቱን በሚገባ ካዎቁት ልክ እንደኔ ማንም ወገኛ ስራ ቀጥሪ በነገር አያሸዎትም!!! ስልቱንም ለማወቅ ሶስት አመት መጠበቅ የለበዎትም፡፡ አሁን ተጽፎ በቃላት እያነበቡት ነው፡፡ ልምምድ ግን ይፈልጋል፡፡ አሁን ኮተት አታብዛብኝ፥ ወደ ቁም ነገሩ እንግባ አይሉኝም አንዴ…? እሺ በቃ…

ቅድመ ዝግጅት ይቀጥላል

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!