አሁን ደግሞ ለቃለ መጠይቅ ከተጠሩ ምን አይነት ዝግጅትና ትኩረት ማድረግ እንደ ሚያስፈልግ አብረን እናያለን። ለቃለ መጠይቅ መጠራት ማለት ስራውን ለማግኘት እጩ መሆን ማለት ነው፡፡ ቀጣሪው አካል እርስዎን ፊት ለፊትና በቅርበት አነጋግሮ ማወቅና ማየት ይፈልጋል ማለት ነው፡፡ እርስዎ ጋር መተዋወቅ ይፈልጋል ማለት ነው፡፡ አሁንም ግን ሌሎች ተፎካካሪ አመልካቾች እንደርስዎ ለቃለ መጠይቅ ስለሚጠሩ ውድድሩ ተፋፋመ እንጂ አላለቀለም፡፡ ስለዚህ ስራውን አገኘዋለሁ ብለው በተስፋ ከመስከርና ቅዠት ውስጥ ከመግባት ይልቅ ለቃለ ምልልሱ መዘጋጀት አለብዎት፡፡
ተወዳጅና ተፈላጊ ስራ ማግኘት ያስደስታል፡፡ የፈጠራ ችሎታና እድገት ያስጨምራል፡፡ ደመወዝም የተለያዩ ወጭወች መሸፈኛ ስለሆነ ሁሉም ሰው ስራ ያስፈልገዋል፡፡ በወጪ ምክንያት ሳንቸገር መኖር አለብን፡፡ ይኸን ስራ ለማግኘት አቀራረብዎን አሳምረው ለቀጣሪው አካል ማሳየትና መሸጥ አለብዎት፡፡ አቀራረብ ነው እንጂ እዚህ ቦታ ላይ መልክ አይሰራም፡፡ ቀጣሪውም አካል እስካሁን ድረስ በድምጽና በማመልከቻ ብቻ ያውቅዎታል፡፡ አሁን ግን በአካል ተገኝተው ፊት ለፊት እንዲዎያዩ ተጋብዘዋል፡፡
ስለዚህ ልዩ የሆነ ዝግጅት ማድረግ አለብዎት፡፡ ለዕድል ቦታ መስጠት የለብዎትም፡፡ እድልና ጸሎት አይሰራም፡፡ እርምዎን ያውጡ፡፡
ለቃለ መጠይቅ ሲጠሩ፤ እንዳው ቀጣሪዎች ሲያዩኝ ይወዱኝ ይሆን? ምን ይጠይቁኝ ይሆን? ምን አይነት መልስ እሰጥ ይሆን? ምን ልልበስ? ምን ልጫመት? ወዘተ እያሉ ግራ መጋባት አይቀርም፡፡ እንዴት እንደሚዘጋጁ የማውቀውን በደንብ እነግረዎታለሁ፡፡ ምን አይነት መልስ እንደ ሚመልሱ ግን ምን አይነት ጥያቄዎች እንደ ሚጠየቁ ስለማላውቅ አንዳንድ ሊጠየቁ የሚችሉ ጥያቄዎችን ብቻ እጠቅሳለሁ፡፡ መልሶቹ ምናልባት ለርስዎ ሁኔታና ገጠመኝ ፊት ባያደርጉም አመላካች መልሶች ይሆናሉ ብየ አስባለህ፡፡ በጣም ብዙ ነገሮች ቁጥርና ግምት ውስጥ ይገባሉ፡፡ ለምሳሌ አቀራረብዎ አንሶ ትምህርትና የስራ ልምድ ብቻቸውን ግቡን አይመቱም፡፡ አቀራረብ ስራ ለማግኘት ብቻ ሳይሆን በማህበራዊ ኑሯችን ላይም እጅግ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ አቀራረብ ወሳኝ ከመሆኑ የተነሳ ስራ ለማግኘት ከመቶ ግማሹ ያህል ሊቆጠር ይችላል፡፡ ልብ ይበሉ! ከፍትፍቱ ፊቱ የሚባለው እዚህም ይሰራል፡፡
የካምፓኒው ነባር ሰራተኞች ጋር ሊቀላቀሉ ነው፡፡ ቤተሰብ ሊሆኑ ነው፡፡ ከዚህ ቤተሰብ ጋር ለመቀላቀል ግን ፈተናውን ማለፍ አለብዎት፡፡
ሊጠየቁ የሚችሉ ጥያቄወች ምን እንደ ሚመስሉ ቁጣዩ ገጽ ላይ አቅርቤአለሁ።
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች
አነበብኩት ትክክል ግንዛቤ የሚያስዝ መልክት ነው በርታ ፍንታው ወንድሜ እግዜር ያበርታህ
አመሰግናለሁ እንዳለ እሺ እበረታለሁ