mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ቀጠሮ የማንነት ማሳያ አጋጣሚ

mejemer ethiopia amaharic appointment

ተወጥቶ ተወርዶ የትም ሀገር ቢኖር፣
አገርቤትም ሆነ ከባህር ባሻገር፣
ጉድለት አለ ሲባል ሥሰማ ሲነገር፣
ብዙ ያገሬ ሰው ቃሉን ሳያከብር፣
እቅድ ሳያወጣ ባጋጣሚ መኖር፣
እንዲህ የገነነ አይመስለኝም ነበር፡፡

ስማችን አይጥፋ በቀጠሮ ምክንያት፣
እስኪ በቃ ብለን ዛሬ እንነሳበት፣
በሰዓቱ እንድረስ ቃል ለገባንለት፣
ቶሎ ሳንዘገይ በተባለው ሰዓት፣
ከዛ ከተባለው ቦታ ለመገኘት፣
ለቀጠርነውም ሰው ክብር ለማሳዬት፣
በደንብ ተገንዝበን የቀጠሮን ክብዴት።

በሰዓቱ መድረስ እንደምን አቃተን?
እስከመቼ ድረስ ሁልጊዜ ዘግይተን፣
በትንሿ ነገር ካልተለማመድን?
ነጻነትና እድገት መቼ እናገኛለን?

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

Avatar
New
argawsays...

ኣሁንም ጥሩ መለክት ኣስተላልፈሃል ብእውነቱ ያለህን እውቀት ለማካፈል እና ሌሎቻችንም መመርያ እንዲንከተል ለማበረታት የምታደርገው ጥረት እጅግ የሚደነቅ ነው እንበርታ ከኣርጋው

Admin:

 አመሰግናለሁ አርጋው //ፋንታው 

Avatar
New
አዲሱsays...

መልካም ነገር ሁሉ ሲያዩት ደስ ያሰኛል

መልካም ነገር ሁሉ ሲያዩት ደስ ያሰኛል

እንዲህ ያለ መረብ ከወዴት ይገኛል

በርታ ቀጥል ብልህ በጣም ደስ ይለኛል

Admin:

 አዲሱ ለድጋፍህ አመሰግናለሁ የግጥም አስተያየትህ ልዩ ነው! //ፋንታው 

Avatar
New
martha mekonensays...

i like it