mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ውስጤንም አሳየኝ መስታዎት

mejemer ethiopia amaharic the mirror

ወዳጄ መስታወት፣
እኔን የማይበት፣
ዋናው የግሌ ቤት፣
ገበያ ወጣሁኝ ላየን ለማሳየት፣
ሸጋ ነው፤ ቆንጆ ናት!
ስጠብቅ በናፍቆት፣
ሰወች እኔን አይተው በተገኘሁበት፣
ለመታየት እንጂ አነሰኝ የሚሰጥ።

ከረባት አሰርኩኝ፣
ጸጉሬንም ቀየርኩኝ፣
ጥምጣሜን አዞርኩኝ፣
እግዜርስ ኮራብኝ?
ቦርጬም አሳሰበኝ፣
መላጣዬ ታየኝ፣
ክሳቴ አስጨነቀኝ፣
ጡንቻየ አደገልኝ፣
ጥርሶቼ ነጡሉኝ፣
ፊቴ ግራ አጋባኝ፣
አልፎ አልፎ ደስ አለኝ፣
ሆዴ ገፍቶ ሳየው ተስፋዬ አበበልኝ፣
ሃሳቤ በሙሉ እኔን ብቻ ጠራኝ።

አሁን ደነገጥኩኝ ፣
በራሴ ላይ ስራ እንዴት አበዛሁኝ?
ወንድሜ የት ገባ ብዬ ካልጠየኩኝ፣
እህቴ የት አለች ብዬ ካልፈለኩኝ፣
እኔስ ምን ሆኛለሁ ብዬ ካላሰብኩኝ፣
ሚናየ በገሃድ ተገልጦ ካልታየኝ፣
የት ነው ያጠፋሁት ብዬ ካልፈለኩኝ፣
ጣቶቼን መቀሰር አሁን ካላቆምኩኝ፣
መስታወቱ እንደሆን ስጋ ነው ያሳየኝ።

ወዳጄ መስታወት እባክህ ንገረኝ፣
ግርግዳ ላይ ሆነህ ሁልጊዜ እምታየኝ፣
እራሴን አብዝቼ ማየቴ ሰለቸኝ፣
ምን አይነት ቃል ወጣኝ?፣
ዛሬ ምን አረኩኝ?
ምን ሃሳብ መጣልኝ?
ቁርጡን አሳውቀኝ!
መልኬን ብቻ ሳይሆን ውስጤንም አሳየኝ።

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!