mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ደባልቄ እና ፍቅረኛው!

mejemer ethiopia amaharic lemon love

ደባልቄ ጉደኛው፣
ጨምሮ ፈገግታው፣
ከነፈ በፍጥነት ገብቶ ከመኪናው፣
ትራፊክ ሳይዘው፣
እድል ነው ያወጣው፣
የፍቅር አምላክ ነው።

መኪናዋም ብትሆን የለም የጎደላት!
ትራፊኩ ሲያያት፣
አላያት! አያውቃት!
ፈጦ ያሳለፋት፣
አሳይታው ይሆን የፍቅር ምልክት?
እንደ ደባልቄ ፊት።

ዛሬ የኔ ቀን ነው!፣
አለና ለራሱ ደባልቄ ነገረው ፣
ሳርና ቅጠሉ የሚስቅ መሰለው፣
ትራፊኩም ቢሆን ሳይቀጣ አሳለፈው፣

ሲደርስ ከቦታው፣
ችግር የለበትም መኪና ማቆሚያው፣
ክፍት ቦታ ነበር የሚተባበረው፣
ማንም ሰው ያልያዘው፣
ለካ የሱ ቀን ነው፣

ፊቱን አየውና ከመስታወቱ ስር፣
ጥርሱ ውስጥ ካለ የተረፈ ምስር ፣
መራመድ ጀመረ እሷን ለመቀበል፣

አውሮፕላኑ አርፎ እሷ ቆይታለች፣
መተላለፊያው ላይ ትጠብቀዋለች፣
በዚያ ፍጥነት ነድቶ እሷ ቀድማዋለች!፣
ዛሬ የኔ ቀን ነው እንዳለው ከሆነች።

እየገለፈጠ ሄዶ ተጠጋና!
ፍቅሬ! እንኳን ደህና መጣሽ! አላት አቀፈና!
እቅፍ አረገችው እሷም ጠጋ ብላ፣
ወዲያውኑ ሳይቆይ ኪሱን ዳበሰና ፣
አንድ የሆነ ነገር ሰጣት አወጣና።

ዋት ዘ ሄል፣
ሎሚ ነዋ! ለፍቅረኛ ይሰጣል!
እ እ እ እ አለች፣
ወደ ሰማይ እያየች፣
ትላልቅ አይኖቿን እያገላበጠች።

ይቺ ልጅ ምን ነካት?
እንደሚላፋ ሰው ጎተተና አስጠጋት፣
ግጥም አርጎ ሳማት፣
ደሞ ተለጥፎ እዛው ላይ ቆየባት፣
በሎሚው ተናዶ ብቀላ መሰላት።

አንተ! እንዴ? ሞዛዛ! ትንፋሼን ወሰድከው!
ፈዞ ስለነበር ድምጿንም አልሰማው፣
ከንፈሯን ለትንሽ ቦጭቆ ሳይወስደው።

የኔ ደባልቄ! ከተሜ ባላገር!
ሎሚ ይወረወራል እንጂ በእጅ አይሰጥም፤ እሺ?
በቃ ተይው አሁን ሙድ አታበላሺ።

አንቺን ስቶ ሄዶ፣
መስታወቱን ሰብሮ፣
ሆስተስዋ ላይ አርፎ .......፣

ፈልገሽ ነበረ ሄደሽ ለመጣላት?
ድራማ ለመስራት፣
በፍቅራችን ቅናት .......

አስበኸው ነበር እኔ ዝም የምላት፣
ተንደርድሬ ሄጄ ሎሚውን ነጥቂያት፣
ከኔ ጋር ጨዋታ አይቻልም ብላት፣
አንድ ጥፊ አቅምሻት፣
እመለስ ነበር ትምህርት ሰጥቻት::

የኔ አንበሳ ድመት፣
ካለ አንቺ ለሌላ ልቤም አይከፈት፣
ፍቅር እና አክብሮት፣
ታውቂያለሽ አይደለ ላንቺ ያለኝ ስሜት፣
እንሂድ ወደቤት።

ጉደኛው ፍቅረኛ ጉዞውን ቀጠለ፣
በመጣበት መንገድ ይዟት ጥርግ አለ።

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!