mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ጀግና አስታውስ ተለማመድ

mejemer ethiopia hero remember

ሃሳብ አቅጣጫ እና ብርሃን ብታሳይ ሰነፎች መራመድና ማየት አይፈልጉም። መልካም ብትሆን ክፉዎች ሊጠሉህ ይችላሉ። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ክብራቸው ስለሚነካ ላይፈልጉህ ይችላሉ። ብሄራዊ ራዕይ ቢኖርህ ጠባቦች አርቀው ማሰብ ይሳናቸዋል። ጠንካራ አስተሳሰብ ሲኖርህ ሰወች ግር ሊላቸው ይችላል። የተለየ ሃሳብ ብታፈልቅ ከባህል፣ ከአስተዳደግ እና ከውሎአቸው ስለሚለይ ጥፋተኛ ሊያደርጉህ ይችላሉ። ሁሉንም ሰው ማስደሰት አይቻልም።

አስተውሰ። ተለማመድ። ትካሻህ ከፍ፣ አንገትህ ቀና፣ ፊትህ ዘና፣ አካሄድህ ላጥ ላጥ፣ ሃሳብህ ልዩ እና አሳታፊ መሆኑን ሁል ጊዜ አስብበት።

# ተለማመድ!

ሳብህ ሰወችን ለማስደሰት ሳይሆን ጥያቄ የሚያስነሳ ከሆነ ከፍተኛ ሚዛን አለው። አሳታፊ እና የጋራ ጥያቄ ላይ አተኩር። የችግር አባባሽ ሳይሆን የመፍትሄ አካል ያደርግሃል። አዲስ ሃሳብና ጥያቄ ያጀግናል! ልብ የሚሉ ያውቁታል። ያኔ ሰወች ሃሳብህን ባይቀበሉትም አንተን ግን አይንቁህም። ከመናቅ በታች የወረደ ህይወት የለም። ትካሻህ ከፍ፣ አንገትህ ቀና፣ ፊትህ ዘና፣ ሃሳብህ ልዩ እና አሳታፊ መሆኑን ሁል ጊዜ አስብበት። ደስ የሚሉ ቃላት ላይ ሳይሆን መፍትሄ የሚያፈልቁ ተግባራዊ ቃላት ላይ አተኩር። ሁል ጊዜ የምታውቀው እና የለመድከው ሃሳብ የማይሰራ ከሆነ ችክ አትበል። ለምሳሌ አንድ የሚያምር እና የምትወደው ጥቁር ቀለም ያለው ሸሚዝ አመቱን ሙሉ አይለበስም። ይሰላቻል። ሌሎችም ቀለሞች አሉ። ሞክራቸው። ሃሳብም እንደዛው ነው።

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!