የአስተሳሰብ ጀግና መሆን እራሱን የቻለ ስራ እና ፈተና ነው! ችግር የለም! ያስተሳሰብ ጀግና እንዴት መሆን እንደሚቻል በቀላሉ ሃሳቤን ማጋራት እችላለሁ፡፡ ለዚህ የሚያበቁ 3 ዋነኛ ነጥቦች አሉ።
1ኛ ረጋ ማለትና ጊዜ መጠቀም፤
2ኛ ልብ ማለትና ትኩረት መስጠት፤
3ኛ መለማመድና መፈጸም ናቸው፡፡
ባሁኑ ዙር ላይ ረጋ ማለትና ጊዜ መጠቀም እንዴት እንደሚቻል ባጭሩ ላስረዳ፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ የቀሩት ሁለት ነጥቦች ይቀርባሉ፡፡ የመጀመሪያው፤ ረጋ ማለት ሃሳባችንን ለማሰባሰብ ይረዳናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ጊዜ ያስፈልገናል፡፡ ለዚህም ነው በህይወታቸው ውስጥ ጥሩ ውሳኔ የሚወስኑ ሰወች ላስብበት የሚሉት፡፡ ጊዜ እፈልጋለሁ፤ አስብበታለሁ የሚሉት፡፡ ምክንያቱም ማጣራትና ማወቅ ያለባቸው ነገር ካለ ረጋ ብለው ጊዜ ይጠቀማሉ፡፡ እንቁላል ቀስ በቀስ በግሩ ይሄዳል ይባል የለ፡፡ የጥንት አባቶቻችን አባባል እስካሁን ድረስ ይሰራል፡፡ አስተሳሰብም እንደዚሁ ነው፡፡ በኛ ባህል ላስብበት ማለት ብዙም የተለመደ አይደለም፡፡ ቀስ ብለው ያሰቡበት ጉዳይ ግን መጨረሻ ላይ ውጤቱ ያማረ ይሆናል፡፡ ሁሉም ነገር ላይ ዘገምተኛ እንሁን ማለቴ አይደለም፡፡ በፍጥነት መወሰን ያለብን ነገር ካለ ቶሎ መወሰን ይቻላል፡፡ ስንናገር እንኳ ትንፋሽ መውሰድና በሰኮንዶች ውስጥ ቃላት መምረጥ መቻል በራሱ በፍጥነት መወሰን ነው፡፡
በተለይ አሁን በምንኖርበት ዘመን ብዙ መረጃወች ይደርሱናል፡፡ በመስማት፣ በማየትና፣ ተካፋይ በመሆን የተለያዩ መረጃወች ይደርሱናል፡፡ ረጋ ማለትና ጊዜ መጠቀም ብቻ ሳይሆን መመርጥ መቻልም እራሱን የቻለ ፈተና ነው፡፡ የችኮላ አስተሳሰብና ስራ ነካ ነካ ስለሚሆን የመጨረሻ ውጤቱ የሚያኮራ አይሆንም፡፡ ለምሳሌ የተባለውን ቶሎ እንዳንረሳ ረጋ ማለትና ማሳቢያ ጊዜ ያስፈልገናል፡፡ ረጋ ማለትና ጊዜ መጠቀም የሰማነውን ለማስታወስ ያግዘናል፡፡ ያየነው ደሞ አዕምሮአችን ውስጥ ቅርጽ እንዲሰራ ያደርጋል፡፡
ለማስታወስ ጊዜ የሌለው ለችግር መፍትሄ የለውም፡፡ ልክ ሳያጠና ፈተና ተፈትኖ እንደወደቀ ሰነፍ ተማሪ ይቆጠራል፡፡ ከዛ ባለፈ ደሞ እያንዳንዱ ሰው የማያልቅ የህይወት ፈተና አለበት፡፡ ህይወታችን ውስጥ ብዙ ነገር ይደርስብናል፡፡ የሚሆኑትን ነገሮች ልክ እንደ ጎበዝ ተማሪ ካጠኗቸው መፍትሄ ለማግኘት ከባድ አይደለም፡፡ ሁላችንም በህይወት ውስጥ ተፈታኝ ተማሪዎች ነን፡፡ ፈተናውን ለመቋቋም የመጀመሪያው መነሻ እርምጃ ሃሳባችንን ረጋ ብለን ማጥናት ነው፡፡ ሃሳብን ረጋ ብሎ ማጥናት የሚያኮራ እንጂ የሚናቅ አቋም አይደለም፡፡
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች