mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

የአስተሳሰብ ጀግና ግንኙነት

mejemer ethiopia hero

አስተሳሰብ ጀግና ማለት ምንድነው? የዚህ አይነት አስተሳሰብ ያስፈልጋል? አሳምሮ ያስፈልጋል፡፡ አባባሉ የተለመደ አይደለም፡፡ አስተሳሰብ ያው ማሰብ ማለት ነው፡፡ ጀግና ማለት ደግሞ ድፍረት ጋር ግንኙነት አለው፡፡ ይኸንን ማስረዳት የኔ ፋንታ ስለሆነ ችግር የለም፡፡

እራሴን ለማወቅ ሰጥቼው ፈተና፣
ሳፈላልግ ነበር የአዕምሮን ቁንጅና፣
አየኋት፤ ተገኘች፤ ያስተሳሰብ ጀግና !

ያስተሳሰብ ጀግና ማለት ከአስተሳሰብ ጋር ግንኙነት ስላለው መጀመሪያ አስተሳሰብ ከየትና እንዴት እንደምናገኝ ትንሽ ላስረዳ፡፡ ለምሳሌ አስተሳሰብ በማየት እናገኛለን፡፡ በመስማት እናገኛለን፡፡ በመናገር እንገኛለን፡፡ በማንበብ እንጋኛለን፡፡ በእንቃቃሴ እንጋኛለን፡፡ በውይይትና ሃሳብ በመለዋወጥ እናገኛለን፡፡ በመንካትና በመዳሰስ እናገኛለን፡፡ በመቅመስ እንገኛለን፡፡ በስሜት እናገኛለን፡፡ በማሽተት እናገኛለን፡፡ አስተያየት እምናገኝባቸው መንገዶች ብዙ ናቸው፡፡ አንዳንዶቹን ብቻ ነው የጠቀስሁት፡፡ የነዚህ አስተሳሰብ ምንጮች ውጫዊና ውስጣዊ ናቸው፡፡ ውስጣዊ ሲሆኑ ከውስጣችን የፈለቁና ወደውጭ የምናሳያቸው ናቸው፡፡ ውጫዊ ሲሆኑ ደግሞ ወደእኛ የሚደርሱ ናቸው፡፡ ለማንኛውም እነዚህን አስተሳሰቦች ካገኘንና ከሰጠን በኋላ እንደ ችሎታ፣ አቅምና ፍላጎትታችን ትርጉም እንሰጣቸዋለን፡፡ ይኸ ትርጉም እራሱን የቻለ ሌላ አይነት አስተሳሰብ ስለሆነ የተለየ ትንታኔ ይፈልጋል፡፡ ሌላ ጊዜ እምለስበታለሁ፡፡

ያስተሳሰብ ጀግና ምንድነው?

ስተሳሰብ ከየት እንደምናገኝ ባጭሩ ተናግሬአለሁ፡፡ አሁን ደሞ ያስተሳሰብ ጀግና ማለት ምን እንደሆነ ላስረዳ፡፡ ያስተሳሰብ ጀግና ማለት ውስጣዊና ውጫዊ አስተሳሰቦችን በሚገባ ማስተናገድ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ይኸን ለማሳካት ደግሞ አዕምሯችን ማመዛዘን የሚያውቅና የተዘጋጀ ሆኖ መገኘት አለበት፡፡ እንዴት ማዘጋጀት ይቻላል? መለማመድና ልብ ማለት አንዱ ቀላል መንገድ ነው፡፡ ማንም ሰው ይችለዋል፡፡ ለማየት ብቻ ከሆነ ሁላችንም እናያለን፡፡ ለመስማት ብቻ ከሆነ ደሞ ሁላችንም እንሰማለን፡፡ ለማንበብ ከሆነ ብዙወቻችን ማንበብ እንችላለን፡፡ ለመናገር ብቻ ከሆነ ሁላችንም መናገር እንችላለን፡፡ ግን ማየት፣ መስማት፣ ማንበብና መናገር ብቻቸውን በቂ አይደሉም፡፡ ያስተሳሰብ ጀግና ለመሆን ለምሳሌ ያየነውን መመርመር አለብን፡፡ የሰማነውን ማጣራት አለብን፡፡ ከአፋችን የሚወጡ ቃላትን መቆጣጠር መቻል አለብን፡፡ በእጃችን የሚጻፉ መልዕክቶችን ማረም መቻል አለብን፡፡

ማጣራትና መመርመር ከፍተኛ የሆነ ያስተሰሰብ አቅም ይሰጣል፡፡ ያስተሰሰብ አቅም ብዙ ነገሮች በቁጥጥራችን ስር እንዲሆኑ ለማድረግ ይረዳናል፡፡ ለምሳሌ ስህተት መቀነስ እንችላለን፡፡ አዲስ ነገር ለመፍጠር መንገድና አቅጣጫ ማየት እንችላለን፡፡ ተቀባይነት ለማግኘት በጣም ይቀላል፡፡ በራሳችን ላይ እንዲንተማመን ያደርጋል፡፡ የበታችነት እንዳይሰማን ጥሩ ምክንያት ይፈጥራል፡፡ ያስተሳሰብ ጀግና የሆነ ሰው ከትላንቱ ትምህርት ይወስዳል፡፡ ለዛሬ መስራት ላይ ያተኩራል፡፡ ለነገ ደግሞ የተሻለ ሰው ሆኜ መገኘት እችላለሁ ብሎ ያምናል፡፡ በጣም ባጭሩ አባባል፤ ያስተሳሰብ ጀግና ማለት አርቆ አሳቢ ማለት ነው፡፡

አርቆ አሳቢ ብሎ መጨረስ ቢቻልም፤ በስፋት ማስረዳት አይከፋም፡፡ ሳንቲሞች ተጠራቅመው ብር ይሆናሉ ይባላል፡፡ እንደዛ ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ እውነት መሆን አለበት፡፡ ለማንኛውም በዝርዝርና ባጭሩ ለማስረዳት የተቻለኝን አድርጊያለሁ፡፡

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!