አንድ አይነት ነገር አይተን፤ አንድ አይነት ነገር ሰምተን፤ ትኩረት ካልሰጠነው፤ እንዳላየነውና እንዳልሰማነው ሆኖ ይቀራል፡፡ ልብ ማለትና ትኩረት መስጠት፤ የሚሰራ መፍትሄ ለማግኘት ጥሩ አቅጣጫ ያሳያል፡፡ መጀመሪያ ግን አንድ ታሪክ ልንገራችሁ፡፡ ደባልቄና ጀምሬ ቀለም ለመቀባት የቀን ስራ ይቀጠራሉ፡፡ ጀምሬ ቀኑን ሙሉ ምንም ሳያርፍ ሲቀባ ዋለ፡፡ ደባልቄ ግን በየሰአቱ ለ10 ደቂቃ ያህል ያርፍ ነበር፡፡ ማታ አካባቢ ላይ ጀምሬ የቀባውን ከደባልቄ ጋር ሲያስተያየው በብዛትና በጥራት በልጦት አየው፡፡ ጀምሬ ደባልቄን እንድህ ብሎ ጠየቀው፤ በየሰአቱ እያረፍክ ነበር አንተ የማልከው፡፡ አይቼሃለሁ፡፡ እኔ ግን ትንፋሼ እስኪሚቆረጥ ድረስ ምንም ሳላርፍ ስቀባ ውዬ እንዴት አንተ በለጥከኝ ብሎ ይጠይቀዋል፡፡
ደባልቄ ግን እኔኮ ለ10 ደቂቃ ሳርፍ ቀለምና ቡርሽ እየቀየርኩ ነበር አለው ይባላል፡፡ ከደባልቄ የተለያየ ትምህርት መውሰድ ይቻላል፡፡ ቀለምና ቡርሽ እየቀያየር ምንም ሳይቸገር በጥራትና በፍጥነት ሲቀባ ዋለ፡፡ ውጤቱም አማረለት፡፡ በየሰአቱ ለ10 ደቂቃ ያህል እያረፈ ሃይሉን አሰባስቦ ቶቶ ቶሎ ለመቀባት ቻለ፡፡
በሚቀጥለው ቀን ለስራ ሲመለስ በቀላሉ ድካም አይሰማውም፡፡ የመስራት ፍላጎትና ሞራሉ ክፍ ያለ ይሆናል፡፡ እራሱን በደንብ አርጎ ተንከባከበ፡፡ ደባልቄ ቀለም እንዴት እንደሚቀባ የሚያውቅ ሰው መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ለራሱ፣ ለስራውና ለውጤቱ የሚሰራ መፍትሄ ነበረው፡፡ ችሎታውንም አሳምሮ ተጠቀመበት፡፡ ሲያርፍ ደግሞ ምን እያደረገ እንደነበር እውቀቱን ለጀምሬ አካፈለው፡፡ የጎበዝ ሰው ምልክት፤ የጥሩ ሰው ምልክት ማለት ይኸ ነው፡፡
ጀምሬ ግን የልፋቱን ያህል ብዙ ውጤት አላገኘም፡፡ እረፍት አልወሰደም፡፡ በማግስቱ ወደ ስራ ሲመለስ በቀላሉ ሊደክም ይችላል፡፡ ድካም በራሱ እዳ ነው፡፡ የቀን ደመወዙ ሊቆረጥበት ይችላል፡፡ እንዴት ነው ታዲያ? ጀምሬ ያሳዝናችኋል፡፡ ማሳዘን እንኳን ምንም አይረዳውም፡፡ ከማዘን ይልቅ የሆነ ምክር መስጠት ይሻላል፡፡ ስራውን ከመጀመርህ በፊት ቀለም እንዴት እንደሚቀባ አጣራ ብሎ መንገር ይሻላል፡፡ እራስህን ተንከባከብ፡፡ ስራ ዛሬ ብቻ አይደለም፡፡ ለነገም አውቀህና በደንብ ተዘጋጅተህ በጥራት ለመስራት አስብበት ብሎ መንገር ይሻላል፡፡
ነገን በጥሩ መንፈስና የተሻለ ቀለም ቀቢ ሆነህ ተቀበላት፡፡ የሚሰማ ከሆነ፡፡ ጀምሬ ግን ደባልቄን እንዴት በለጥከኝ ብሎ ስለጣየቀ የተሻለ ለማወቅ ግልጽ የሆነ ፍላጎት አለው፡፡ ምክርም ቢሆን የሚቀበል ይመስላል፡፡ ይኸ በራሱ ጥሩ ነው፡፡ አይቶ ዝም አላለም፡፡ አሮጌና አድካሚ ልማዱን በሚሰራ አድስ ልምድ ለመተካት ፈልጓል፡፡ እኔ በበኩሌ ጀምሬን በጣም አደንቀዋለሁ፡፡ ለምን ብትሉኝ፤ እንዴት አርገህ ሰርተህ ከኔ የበለጠ ውጤት አመጣህ ብሎ ደባልቄን ስለጠየቀው ለራሱ ትልቅ ውለታ ውሏል፡፡
ሁላችንም በህይወታችን ውስጥ ቶሎ ብለን ባንድ ጊዜ የማናውቃቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ አይደለም ሳናውቅ አውቀናል ብለን በትክክል የማናውቀው እውቀት ሊኖር ይችላል፡፡ አይተናል ብለን ያላየነው እይታ ሊኖር ይችላል፡፡ ተምረናል ብለን ያልተማርነው ትምህርት ሞልቷል፡፡ ትምህርት አያልቅም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ይሰራል ብለን ያሰብነው ሃሳብ ወደ ተግባር ሲቀየር የተጠበቀውን ውጤት አያመጣም፡፡ ዋናው ነገር ግን ለማወቅና ለመማር ፍላጎት ማሳየት ችግሮችን ለመቀነስና መፍትሄ ለማግኘት ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ ይኸን ጥሩ አጋጣሚ ለመፍጠር ደሞ ልብ ማለትና ትኩረት መስጠት ከሁሉም በፊት ቀዳሚ ነው፡፡
ልብ ማለትና ትኩረት መስጠት፤ በህይወታችን ውስጥ ሊደርሱ የሚችሉ ምልክቶችን ማየት መቻል እና መፍትሄ ለመስጠት ፍላጎት ከማሳየት ጋር ይመሳሰላል፡፡ የዚህ አይነት ቆንጆና አቀራራቢ አስተሳሰብ መከታተል ከፈለጉ "መጀመር" ጣቢያን አንዳንድ ጊዜ ይጎብኙ፡፡
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች