mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

የሰነፍ እና የጎበዝ አቅጣጫ ምርጫ

mejemer ethiopia amaharic the choice of sign

በዝ ለመሆን የወሰነ ሰው ጎበዝ መሆን ይችላል፡፡ ሰነፍ ለመሆን የመረጠ ሰው ሰነፍ መሆን ይችላል፡፡ ዋናው የሰነፍና የጎበዝ ልዩነት ምርጫ እና ውሳኔ ላይ ያረፈ ነው፡፡ ሰነፍ እና ጎበዝ ተብሎ ተመርጦ የተፈጠረ ሰው ግን የለም፡፡ የሚከበሩ ሰወች፤ መጀመሪያ እራሳቸው ማክበር እንዳለባቸው ምልክት ያያሉ፡፡ ሃቀኛ በመሆን የሚያምኑ ሰወች፤ መጨረሻ ላይ እውነት ማሸነፏ እንደማይቀር ምልክት ለማየት አይቸገሩም፡፡ ሃሰተኛ የሆኑ ሰዎች ግን አንድ ቀን እንደ ሚጋለጡና ዋጋ እንደ ሚያስከፍላቸው ማየቱን ይረሱታል፡፡ ሃቀኛና ሃሰተኛ ተብሎና ተመርጦ የተፈጠረ ሰው ግን የለም፡፡ ዛሬ ስለ ማክበርና መከበር አብረን እንያለን፡፡

ጎበዝ የሆነ ሰው ጎበዝ መሆኑ ይታወቀዋል፡፡ ምክንያቱም ያስገኘውን ውጤት ማየትና መጠቀም ይችላል፡፡ ተጨማሪ ውጤት፣ ተጨማሪ ውጤት፤ ተጨማሪ ውጤት ማሳየት ይፈልጋል፡፡ ሰነፍ የሆነ ሰው ግን ሰነፍ መሆኑ አይታወቀውም፡፡ እንደምንም ብሎ ከኖረ በቂ ይመስለዋል፡፡ ይኸ ሁሉ የምታዩት፤ ከፍተኛና ዝቅተኛ አኗኗራችን በውሳኔና በምርጫ የተገኘ ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ደግሞ መከበር እንደሚፈልግ መገመት ቀላል ነው፡፡ ይኸን ተከትሎ ግን፤ እያንዳንዱ ሰው ለመከበር የሚያሳየው ምልክትና ፍላጎት ይለያያል፡፡ አንዳንድ ሰው መከበር ፈልጎ የሚናቅ አለ፡፡ መወደድ ፈልጎ የሚጠላ አይጠፋም፡፡ ጥሩ ተናግሮ የሚሰደብ አለ፡፡ በጊዜ ሂደትና ተግባር፤ ከታየና ከተፈተነ በኋላ መጨረሻ ላይ ተከብሮ የሚናቅ አለ፡፡ ይኸ ደግሞ አያድርስ ነው፡፡ ከተዋደደ በኋላ የሚለያይ አለ፡፡ ቃሉን አክብሮ ወይም ሰብሮ የሚገኝ ሰው አለ፡፡ ተለያይቶ የሚታረቅ አለ፡፡ ፍጹም ብሎ ነገር የለም፡፡ ለማንኛውም አብዛኛው የህይወታችን አቅጣጫና የማንነታችን መገለጫ በመከባበር ምልክት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

ለ መከባበር ምልክት ግን በደንብ አይነገርም፡፡ በደንብ ትምህርት አይሰጥበትም፡፡ በደንብ አይታሰብበትም፡፡ በደንብ አንጠቀምበትም፡፡ ለምድነው ግን ሰወች ባለባበሳቸው ይወደዳሉ፤ ከልብስ ይልቅ ፈገግታ ይሻላል! ሰወች ባነጋገራቸው ይታመናሉ፤ ከወሬ ይልቅ ተግባር ይበልጣል፡፡ ተሳሳትኩ? በዚህ መካከል ከሁሉም በላይ ትኩረት የሚያስፈልገው ትልቁ ቃል፤ መከባበር ይባላል፡፡

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!