በህይወታችን ውስጥ ልክ እንደ መከባበር ትልቅ ነገር የለም። ታላቅ ማክበር፣ ልጆች ማክበር፣ እራስን ማክበር፣ ሴቶችን ማክበር፣ ሃላፊነት ማክበር፣ ትዳር ማክበር፤ ፈጣሪን ማክበር፣ ቀጠሮ ማክበር ምርጥ የሆነ የህይወት አቅጣጫ ለማሳየት አያሳስትም፡፡ አንዳንዶቹን ብቻ ነው የጠቀስኩት፡፡ አንባቢወች በደንብ እንደምትረዱኝ እርግጠኛ ነኝ፡፡ መከባበር የሚታሰብ ብቻ ሳይሆን፤ በአይን የሚታይ፣ በጅ የሚዳሰስና የሚጨበት ይመስለኛል፡፡
ከላይ እንደ ጠቀስኩት መከባበር በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ይገኛል። ባጭሩ መከባበር ማለት ሚዛናዊ መሆን ማለት ነው። መከባበር በፍቅር እና በትህትና አይገኝም። ፍቅር እና ትህትና ግን በመከባበር ይገኛሉ። ምክንያቱም አንድ ሰው ሌላውን ማፍቀር የሚችለው መጀመሪያ መከበሩን ካወቀ በኋላ ነው። ትህትና ማሳየት የሚችለው መጀመሪያ መከበሩን ካየ በኋላ ነው። መከባበር ቀዳሚ ነው። ፍቅርና ትህትና ተከታዮች ናቸው። መጀመሪያ ሳይከበር እና ሳያከብር የሚወድ ካለ የውሸት ወይም ጊዜያዊ መውደድ ነው።
ይኸን እንዴትና ለምን እዳሰብኩ ማስረዳት አለብኝ፡፡ ለምሳሌ መቻቻል ማለት ወይ መተው ነው፤ ወይ መፍራት ነው፡፡ ስለ መቻቻል የሚያወራ ሰው ሲበደል ዝም የሚል ሲገፋ ደሞ ፈቅ የሚል ነው፡፡ በተለይ ነጻነት በልመና ወይም በጥያቄ የሚገኝ ይመስለዋል፡፡ ፍቅር ያሸንፋል ደሞ እተለመደ የአለም ቋንቋና ዘፈን ነው፡፡ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያውያን፤ የተሻለ መፍትሄ ሲያጡ ፍቅር ያሸንፋል ብለው ያስባሉ፡፡ በታሪክም ቢሆን እስካሁን ድረስ በፍቅር ያደገና ያሸነፈ ሃገርና ህዝብ አይተን አናውቅም፡፡ ሙዚቀኞች ገንዘብ ለማግኘትና ሰውን ለማስደሰት ፍቅር ያሸንፋል ይላሉ፡፡ ፍቅር ግን ከሙዚቃ ጭፈራ በኋላ የሚያስታውሰው የለም፡፡
የሃይማኖት አባቶች ደግም ሰወች እንዲለግሱና አምላክን እንዲያስታውሱ ፍቅር ያሸንፋል ይላሉ፡፡ ፍቅር ግን ከእምነት ቤት ውልቅ ብለው ሲወጡ፤ እዛው ይቀራል፡፡ ምን ማለት ነው ይኸ? አይሰራም ማለት ነው፡፡ የማይሰራ ነገር ላይ ችክ ማለት አያስፈልግም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የማይሰራ ነገር ላይ እርም ማውጣት ይጠቅማል እንጅ አይጎዳም፡፡ የዚህ አይነት አስተሳሰብ ለብዙ ዘመናት ታይቶና ተፈትኖ አልሰራም፡፡ በዚሁ መቀጠል የለብንም፡፡
ህይወትን ለመንዳት ፍቅር በመከባበር የታቀፈ መሆን አለበት፡፡ ፍቅር የመከባበር አንዱ ክፍል ነው እንጂ ልክ እንደ መከባበር ሰፊና ትልቅ አይደለም፡፡ ትህትና የሚባለው ደሞ ከልክ ያለፈ ሲሆን ታዛዥና ተከታይ ያደርጋል፡፡ በነገራችን ላይ እነ መቻቻል፣ ፍቅርና ትህትናን ዋጋ ሳልሰጣቸው ቀርቼ አይደለም፡፡ ሲሰሟቸው ደስ የሚሉ ቃላት ናቸው፡፡ ለመስማት ካልሆነ በስተቀር በተግባር አይሰሩም፡፡
ብዙ ሰው ግን ለነሱ ሲጨነቅ አይቻለሁ፡፡ እኔን የሚያሳስበኝ የተዘነጋው መከባበር ነው፡፡ መከባበር በግልጽ መታየትና መነገር አለበት፡፡ ከላይ እንደጠቀስኩት መከባበር የነ መቻቻል፣ የነ ትህትና፣ የነ ፍቅርና የመሳሰሉት አለቃና ተቆጣጣሪ ነው፡፡ ልክ እንደ መኪና ሞተር፡፡ ልክ እንደ ሳር ቤት ምሰሶ፡፡ ልክ እንደ ልባችን ትርታ፡፡ ልክ እንደ አይናችን ብሌን ነው፡፡ በልምና፣ በጥያቄ፣ በጸሎትና በምኞት ቢሆን ኖሮ እስካሁን የት እንደርስ ነበር? ያሳስባል አይደል? ስለዚህ ሌሎቹ ትናንሾቹ የምንወዳቸውና ደስ የሚሉን ቃላት ስራ ላይ እንዲውሉ መጀመሪያ አስኳሉን መከባበር ትኩረት እንስጠው፡፡ እንከባከበው፡፡ መከባበር ወሳኝ ከመሆኑ የተነሳ፤ እንዳውም የመከባበር ሚኒስቴር ቢኖረን ኖረ በመተሳሰብ ላይ መሰረት የጣለ ስልጣኔ ይኖረን ነበር፡፡ ለዚህ አላማ ተብሎ ከልብ ከተሰራበት፡፡ ምክንያቱም መጀመሪያ ሰዎች መከባበር ምን እንደሆነ ሲለማመዱና ሲያውቁ ሰላም ይከተላል፡፡ እንዲሁ በደረቁ ሰላምና እድገት አይመጣም፡፡
የዚህ አይነት አቅርቦት መከታተል ከፈለጉ አንዳንድ ጊዜ መጀመር ጣቢያን ይጎብኙ፡፡ ለጓደኛም ይንገሩ፡፡ መልካም ውሎ! መልካም ምሽት!
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች