mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ጥሩ መርህ እንዴት ይገኛል

mejemer ethiopia amharic principle

ጭሩ መርህ ማለት አንድ ሰው በህይዎቱ ውስጥ መጠቀም የሚፈልገው ሚዛናዊ አስተሳሰብና ግብ ነው። መርህ ለአንዲት ሃገር እና ዜጋ እንደ ሞራል ሊቆጠር ይችላል። ይኸን ለማሳካት ሶስት አይነት ማወቂያ መንገድ አለው። በቤተሰብ አስተዳደግ፣ በትምህትር ቤት እና በራስ ፈልጎ ማወቅ ናቸው። ሶስቱንም መንገዶች ለማስረዳት እሞክራለሁ።

1) በቤተሰብ አስተዳደግ አንድ ህጻን ሲወለድ ልክ እንደ ንጹህ ነጭ ወረቀት ነው። ቤተሰብ የሰጠውን ይቀበላል። በቤተሰብ ተኮትኩቶ ማደግን የመሰለ ወርቃማ ጊዜ የለም። ቤተሰብ መርህ አልባ ከሆነ ለልጅ የሚያሳየው የህይወት አቅጣጫ የለም። ቤተሰብ ስለ መርህና ሞራል የሚያውቅ ከሆነ ግን፤ ለምሳሌ ስለ ሃገር መውደድ፣ ታሪክ እና ነጻነት፣ መከባበር፣ ርህራሄ ማሳየት፣ መማር፣ ራስ መቻል፣ የመሳሰሉትን ማስረዳት እና ማሳየት ይችላል። ቤተሰብ መርህ አልባ ከሆነ ክፍተት ይፈጠራል። ምክንያቱም በልጅነት ከቤተሰብ በላይ የቀረበና የተሻለ አይገኝም። በተጨማሪ ቤተሰብ እና ጎረቤት ለልጆች ጥሩ ፊት እና አክብሮት ማሳየት አለበት። ለምሳሌ ልጅን አታውቅም ከማለት ይልቅ አስረድቶ እውቀት ማካፈል ይሻላል።

2) ትምህርት ቤትና ህብረተሰብ በተለይ 6 አመት ከሞላን በኋላ ወደ መደበኛ ት/ቤት እንሄዳለን። በዛውም ከህብረተሰቡ ጋር እንቀላቀላለን። ገና ሲጀመር ስለ መከባበር ከቤተሰብ ያልሰማ ህጻን በቀላሉ ት/ቤት አይለምድም። መግባባት ሊቸግረው ይችላል። ችግሩን ለማቅለል ትክክለኛ ትምህርትና መርህ ያለው አስተማሪ በቦታው መኖር አለበት። የዚህ አይነት አስተማሪ በቦታው ካለ በጣም ተፈታታኝ ቢሆንም ቀስ በቀስ መፍትሄ ይገኛል። ት/ቤት ለልጆች ከቀለም ትምህርት ባለፈ የአዕምሮ ማሳደጊያ ተቋም ነው። ልጆች ስራ ሲጀምሩ ለራሳቸውና ለሃገራቸው እንዴት ጠቃሚ መሆን እንዳለባቸው ታንጸው የሚሰናበቱበት ተቋም ነው።

3) በራስ ደርሶ ማወቅ አንድ ሰው ከቤተሰብና ከት/ቤት ያልተገኘውን መርህ በራሱ ለማግኘት አንዱ የመጨረሻው ምርጫ አሁን ነው። የቆመለትን መርህ ማዳበር ወይም አዲስ መርህ ማስቀመጥ ይችላል። አሁን አድማሱ ሰፍቷል። አንድ ሰው በወላጅ እና በት/ቤት ብቻ የተወሰነ አይሆንም። ወጣትና ጎልማሳ ሆኗል። የተለየ የህይወት ምእራፍ ይጀምራል። እራሱን ለመቻል ተፈታታኝ ጊዜ ውስጥ ገብቷል። ለምሳሌ ስራ ለማግኘት ሊሆን ይችላል። ቤተሰብ ለመመስረት ማሰብ ሊሆን ይችላል።

ብዙ ሰወች ህይወት የሚከብዳቸው መርህ አልባ ሲሆኑ ነው። የሰው ልጅ በተለይ ስለ መከባበር እና ርህራሄ በልጅነቱ መማር አለብት። መርህ ህይወትን ያጣፍጣል። የሰው ልጅ ለመርህ ብሎ ይኖራል። በተስፋ ከመኖር በመርህ መኖር እራስን ለማሳደግ እና ከሰው ጋር ለመግባባት ወሳኝ የህይወት መብራት ነው። ተስፋ የሰነፍ መደበቂያ ብርድ ልብስ ነው። መርህ የታታሪ መገለጫ አላማ ነው። ምክንያቱም መርህ አንድ ሰው በህይወቱ ውስጥ መጠቀም የሚፈልገው ሚዛናዊ አስተሳሰብና ግብ ስለሆነ ነው። ስለ መከባበር እና ርህራሄ ከቤተሰብ ያልሰማ፣ ከት/ቤት ያልተማረ እና በራሱ ያልደረሰበት ዜጋ እርስ በርሱ ለመግባባት ይቸገራል። እየሆነ ያለው ይኸ ነው። በሚቀጥለው ጊዜ መርህ አልባ መሆን ምን አይነት ጉዳት እንዳለው አቀርባለሁ። ይከታተሉ። ሰላም!

ከታች አስተያየት ወይም ኮከብ ለመስጠት ያስታውሱ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!