mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

የሞባይል ስልክ ደህንነት ክፍል 1፤ መግቢያ

ሞባይል ስልክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ነው። ባሁኑ ጊዜ፤ ስልካችን የግል መታወቂያ እና መረጃ የሚታይበት ነው። ለምሳሌ ስም እና አድራሻችን አለበት። የኢሜይል መልዕክታችን ይቀመጥበታል። በመስመር ላይ የምናደርገው ማንኛውም አይነት እንቅስቃሴ ይታወቃል። በኛ ላይ የተመዘገበው የግል መረጃ፤ ለምሳሌ የባንክ እና የጤና መረጃ ይገኝበታል። የምናነሳቸው ፎቶዎች እና የመዘገብናቸው የስልክ ቁጥሮች፤ ሌላም ሌላም፤ የግላችን ነገር ስልካችን ላይ ተመዝግቦ ይቀመጣል።

በተጨማሪ ምናልባት በስልካችን ግብይት እናካሂድበት ይሆናል። የባንክ አገልግሎትም እንጠቀምበት ይሆናል። በዚህ ምክንያት፤ ስልካችን ላይ ያለው ማንኛውም የግል መረጃ፤ ለሳይበር ጠላፊዎች የተጋለጠ ነው። የሞባይል ስልክ ተጠቃሚ በጨመረ ቁጥር፤ የግል መረጃችን ያልሆነ ሰው እጅ ላይ ለመውደቅ፤ ከፍተኛ እድል አለው። ይኸ ሊሆን የሚችለው፤ ተጠቃሚው ሳያውቅ ይቀርና፤ ወይም ጥንቃቄ ሳያደርግ ሲቀር ነው። የግላችን መረጃ፤ አደጋ ላይ ከመውደቁ በፊት፤ የተለያዩ ወሳኝ ጥንቃቄዎች በራሳችን ማድረግ እንችላለን። ሞባይል ስልክ፤ ከእለት ወደ እለት የምንፈጽማቸው ተግባራት፤ በቀላሉ እንዲካሄድ ይረዳናል።

ዚህ ምክንያት የፈለግነው ነገር እና የነካካነው ነገር ይታወቃል። ያለንበትን አቅጣጫና ቦታ ለማወቅ ብዙ አዝቸጋሪ አይደለም። ለዚህ አጋጣሚ፣ አውቀንም ይሁን ሳናውቅ ተስማምተንበት ነው። ባሁኑ ጊዜ፤ የስልክ ባለቤት መሆን የውደታ፤ ግዴታ የሆነ ይመስላል። የሞባይል ስልክና የግል መረጃዎን ከሳይበር ሌባ ለመከላከል፤ አይነቱ የተለያየ ነው። አስቸጋሪ ግን አይደለም። በአንድ ዙር ብቻ ለማቅረብ ስለሚበዛ፤ ተከፋፍሎ በመልክ በመልኩ ይቀርባል። በአይነታቸውም ቆንጆ ምክሮች በተከታታይ ይቀርባሉ። በደንብ ይከታተሉ። የሞባይል ስልክ እና የግል መረጃ በጥንቃቄ መያዝ እጅግ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ፤ ለጓደኛ፤ ለዘመድ እና ለቤተሰብ ይንገሩ። ከዛሬው ጠቃሚ ማሳሰቢያ ጋር፤ መልካም ውሎ!

ከታች አስተያየት ይስጡ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!