ለምሳሌ አንድ ሰው ት/ቤት ሄዶ ጸሃፊ፣ ሀኪም፣ ገበሬ እና መሃንድስ ለመሆን ይማራል። እጁ መጻፍ ይለምዳል። ህክምና አገልግሎት ይሰጣል። ዘመናዊ ግብርና ይጀምራል። ህንጻ እና ድልድይ ይነድፋል። ለችግሮች መፍትሄ ያበጃል። በአዕምሮው ሃይል እጆቹን ለበጎ ነገር ያንቀሳቅሳል። እየቆየ ሲሄድ ደግሞ አዕምሮ ይልቃል። እጃችንም አብሮ ይከተላል። እከሌ ታታሪ ነው! እከሌ ጥሩ ልምድ አለው የሚባለው ለዚህ ነው። እጁ ሰርቶ ያሳያል።
ልብ ከስሜት ጋር የተገናኘ ስለሆነ ውስብስብ ነው ይባላል። የሆነ ነገር ከሰማን እና ካየን በኋላ እንደ አይነቱ ልባችን ይሰማዋል። ልብ ግን ይሰማዋል እንጂ አያስብም። በልቡ የሚመራ ሰው ችግር ያባዛል። በልብ መመራት ማለት ለመወሰን ከአዕምሮ በፊት ልብን ማስቀደም ማለት ነው። ብልህ ልብ ከአዕምሮ ጋር ይተባበራል።
አዕምሮ ሲቀድም እጅ ትክክለኛ ነገር ይነካል። ልብ ተገቢ ርህራሄ ያሳያል። አፍ ሚዛናዊ ቃላት ያወጣል። አንድ ህዝብ በሰላም መኖር እንዲችል መከባበር ምን እንደሆነ አውቆ ማደግ አለበት። መከባበር ከፍቅር እና ከሃይማኖት ይቀድማል። ፍቅር እና ሃይማኖት የግል ናቸው። መከባበር ግን የጋራ ነው። የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ጠላት ኋላ ቀር አስተሳሰብ ነው። የአንዲት ሃገር እድገት እና ውድቀት በህዝቧ አዕምሮ አቅም ይለካል። ከሌለህ የለህም!
ማሰብ እና መቁጠር መከባበር እና ፍቅር ኢትዮጵያ እና ባህሪ ሞኝ እና ደግ ሰው አንደኛ ደረጃ አስተሳሰብ ስራውን አሳደው ያግኙት መሰረታዊ ኮምፕዩተር ዕውቀት አማርኛ ፊዴላት መማሪያ ግጥም፣ ፌዝ፤ ልብ-ወለድ
ለሚሰራ እጅ፣
ለሚወድ ልብ
ለሚያስብ አዕምሮ፤
mejemer.com
ኮምፒውተር በተሰጠው መመሪያ መሰረት አስልቶ ስራዎችን የሚያከናውን ማሽን ነው። ቅደም ተከተል እና መመሪያዎቹ ግን ለኮምፕዩተሩ በሚገባው ቋንቋ ተደርገው በሰው የተሰሩ ናቸው። ኮምፕዩተሩ ስራውን ሲሰራ ከሰው በብዙ እጥፍ ይፈጥናል። መሰረታዊ ነገሩ በቀላሉ እንዴት እንደሚሰራ ለ9 ተከፋፍሎ ቀርቧል። መልካም እድል!
ስራ ማግኘትና መስራት የመኖሪያ እንጀራ ነው። በተለይ የሚወደድ እና ያለሙትን ስራ አሳዶ ለማግኘት ገና ሲጀመር ምን ማድረግ እንዳለብዎት ያውቃሉ? ከማስታወቂያ ጀምሮ ስራውን አግኝተው እንዴት በቀላሉ ይዞ መቆየት እንደሚቻል ለ8 ተከፋፍሎ ቀርቧል። መነሻ፤ ክትትል፤ ማመልከቻ፤ ቃለ-መጠይቅ፤ ስራ፤ ኑሮ፤ ወዘተ። ይቅናዎት!!
ሰላም! ፋንታው እባላለሁ፡፡ ህይዎት ከባድ ትመስላልች። ልብ ለሚል ሰው ግን ከባድ አይደለችም። ለምሳሌ እንክርዳድ ከስንዴ ለመለየት በአይናችን ማየት በቂ ነው ። ክፉ እና ደግ ነገር ለመለየት ደግሞ አዕምሮአችን ማየት መቻል አለበት። የአይን እይታ እና የአዕምሮ እይታ ይለያያል። አዕምሮ በተከታተይ ልምምድ ይፈልጋል። የሚሰራ እጅ፣ የሚወድ ልብ እና የሚያስብ አዕምሮ ያለው ሰው ግን በቀላሉ ያያል። በዚህ ምክንያት ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ የተሻለ ሰው ሆኖ መገኘት ይችላል።
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ከኔ ጋር ይጓዙ!
የሆነ ነገር ጀምረህ ውጤት ካላመጣ ከመተው ይልቅ "ለምን ጀመርኩ" ብለህ እራስህን ጠይቅ! መተው እና እጅ መስጠት ለሰነፍ ብቻ ነው።
ማታ ለእንቅልፍ ስትዘጋጅ ዛሬ ምን ጥሩ ነገር አድርጌ ዋልኩ ብለህ እራስህን ጠይቅ። የዛሬው ተገባርህ የነገ መሰረትህ ነው።