ለሚሰሩ እጆች

ለሚወድ ልብ

ለሚያስብ አዕምሮ

mejemer.com ቀላል ፍልስፍና!

mejemer.com ቀላል ፍልስፍና!
እጆች ይሰራሉ

ለሚሰራ እጅ

ምሳሌ አንድ ሰው ት/ቤት ገብቶ እጁ መጻፍ ይለምዳል። ከመጻፍ በኋላ ሃኪም፣ መሃንድስ፣ አስተማሪ፣ ነጋዴ፣ ገበሬ፣ ጸሃፊ፣ ከዋኝ ወዘተ ይሆናል። ለተለያዩ ችግሮች መፍትሄ ያበጃል። አዕምሮውን ለሚረባ ፈጠራ ያሰራዋል። እጃቹም አብሮው ይከተላሉ። እከሌ ደግ እና ታታሪ ነው! እከሌ ጥሩ ልምድ አለው የሚባለው ለዚህ ነው። አእምሮው ፈጥሮ፤ እጁ ሰርቶ ያሳያል።

ልብ ይወዳል

ለሚወድ ልብ

ብ ከስሜት ጋር የተገናኘ ስለሆነ ውስብስብ ነው ይባላል። የሆነ ነገር ከሰማን እና ካየን በኋላ እንደ አይነቱ ልባችን ይሰማዋል። ልብ ግን ይሰማዋል እንጂ አያስብም። በልቡ የሚመራ ሰው ችግር ያባዛል። በልብ መመራት ማለት ለመወሰን ከአዕምሮ በፊት ልብን ማስቀደም ማለት ነው። ብልህ ልብ ከአዕምሮ ጋር ይተባበራል።

እዕምሮ ያስባል

ለሚያስብ አዕምሮ

ዕምሮ ሲቀድም እጅ ትክክለኛ ነገር ይነካል። ልብ ተገቢ ርህራሄ ያሳያል። አፍ ሚዛናዊ ቃላት ያወጣል። አንድ ህዝብ በሰላም መኖር እንዲችል መከባበር ምን እንደሆነ ተምሮ ማደግ አለበት። የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ጠላት ኋላ ቀር አስተሳሰብ ነው። የአንዲት ሃገር እድገት እና ውድቀት በህዝቧ አዕምሮ አቅም ይለካል። ከሌለህ የለህም!

እንኳን ደህና መጡ!

ለሚሰሩ እጆች፣
ለሚወድ ልብ
ለሚያስብ አዕምሮ፤
mejemer.com

ተጨማሪ

እንኳን ደህና መጡ!

እንኳን ወደ "መጀመር" መጡ!

ላም! ፋንታው እባላለሁ፡፡ ህይዎት ከባድ ትመስላልች። ልብ ለሚል ሰው ግን ከባድ አይደለችም። ለምሳሌ እንክርዳድ ከስንዴ ለመለየት በአይናችን ማየት በቂ ነው ። ክፉ እና ደግ ነገር ለመለየት ደግሞ አዕምሮአችን ማየት መቻል አለበት። የአይን እይታ እና የአዕምሮ እይታ ይለያያል። አዕምሮ በተከታተይ ልምምድ ይፈልጋል። የሚሰራ እጅ፣ የሚወድ ልብ እና የሚያስብ አዕምሮ ያለው ሰው ግን በቀላሉ ያያል። በዚህ አይነት ሁነታ ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ የተሻለ ሰው ሆኖ መገኘት ይችላል።
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ከኔ ጋር ይጓዙ!

ተጨማሪ