mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ቀጠሮ ካላከበርክ ማነህ?

ጠሮ የማያከብር ሰው ምን ይመስልሻል?
ባጭሩ፤ በቃሉ የማይገኝ ሰው ማለት ነው። እቅድ የሌለውና ባጋጣሚ የሚኖር። ለመብቱም ቢሆን የሚያስብበት አይመስለኝም። ቀጠሮ የሰውን ማንነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

አንቺ ደግሞ ዛሬ ምን ነካሽ? ምን ማለትሽ ነው?
እኔ ምንም አልነካኝም። አንተ እራስህ እንደማትዘገይ አውቃለሁ። አየህ ቀጠሮ ካላከበርን ታማኝ መሆን አንችልም። ቀጠሮ ስንይዝ፤ ከሰው፣ ከቃላችን፣ ከጊዜና ከሆነ ጉዳይ ጋር ነው። አብሶ ተምረህ ቀጠሮ የማይገባህ ከሆነ ሰነፍና ግድ የለሽ ትሆናለህ። ሰነፍ ስትሆን ለቃልህ ጊዜ የለህም። ግድ የለሽ ስትሆን ቃልህ ምንም አይመስልህም። ስለዚህ ለራስህ እና ለህብረተሰቡ ችግር ነህ ማለት ነው። ይኸ ደግሞ በኢትዮጵያውያን ላይ ይብሳል። በቀጠሮ ቃልህ የማትገኝ ከሆነ፤ የፈለገ ብትማር ታማኝና ትክክል መሆን አትችልም። የተፈጥሮ መብትህ ይወሰድብሃል።

ጥሩ ብለሻል። ችግሩ ገብቶሻል። በኑሮአችን ላይ ቀጠሮ ዘርፈ ብዙ ሚና አለው። ትክክል ለመሆን ፍላጎት ሊኖረን ግን ይገባል።
አወ! አሁን አደራ እንበል።

አደራ ቀጠሮ ያክብሩ
አደራ ቀጠሮ ያክብሩ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!