mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና
ፍቅርና ህብረተሰብ የግል ፍቅር የዋህና ፍቅር

የዋህና ፍቅር

mejemer ethiopia amharic being naive and love

ብዙዎቻችን አስተዳደግ ባህላዊ ነው። ባህል ማለት ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፈ ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ማለት ነው። ባህል ጥሩ ነገር ቢኖረውም በባህል ብቻ ማደግ የዋህ ያደርጋል። የዋህ መሆን ማለት በራሳችን ኑሮ ላይ ሃላፊነት ለመውሰድ ጥበብና ልምድ ለማግኘት መቸገር ማለት ነው። በባህል ማደግ በይሉኝታ ማደግ ጋር ይመሳሰላል። ለመመሳሰል ብለን ቀላልና ከባድ ስህተት መስራት ይሉኝታ ይባላል። ባህል አንድ ሰው እራሱን የቻለ ልዩ ሃሳብ እንዲኖረው ብዙ አይፈቅድም።

ለመወሰን ባህል በቂ አይደለም፤ ባህል የታሪካችን አንዱ ክፍል ቢሆንም በህይወታችን ላይ የውሳኔ መስጫ ምክንያትና መሰረት መሆን የለበትም። ማንኛውም ሁኔታ ላይ ለመፍረድ ጥበብና ልምድ ይጠይቃል። ጥበብ ማለት ባጭሩ የመፍትሄ ፈላጊ አካል መሆን ማለት ነው። ልምድ ማለት ባጭሩ ከስህተት መማርና ወደፊት ማየት ማለት ነው። ባህል በሚሰጠን ልምድ ላይ ጥበብ ብንጨምርበት መርህ ይሆናል። በመርህ ተደግፎ ያደገ ዜጋ እራሱን ችሎ ሚዛናዊ አስተሳሰብ፣ ግብና ጥበብ ማዳበር ይችላል። እጁ ትክክለኛ ነገር ይነካል። ልቡ ተገቢ ርህራሄ ያሳያል። አፉ ሚዛናዊ ቃላት ያወጣል። አዕምሮው ወንዝ ላይ እንደ ወደቀ ደረቅ ቅጠል በቀላሉ አቅጣጫ አይቀይርም። እያንዳንዱ ሃገር በትውልድ ያገኘው ባህል አለ። ባህል ብቻውን ከላይ የጠቀስኩትን የህይወት መመሪያ መተካት ግን አይችልም።

ቅርም ቢሆን ልክ በቀበሌ ብርጭቆ ተለክቶ ለሁሉም ሰው የሚታደል ስኳር አይደለም። የተማሩ ሰዎች እንደ ነገሩ አሉን። እንደ ብዛታና ትምህርታቸው የሰለጠኑ መስለው አይታዩም። ፍጹም መሆን አይቻልም። በህበረሰባችን ውስጥ አልተፈለግም እንጂ ትክክል መሆን ግን ይቻላል። ምናልባት በዚህ የማትስማሙ ወንድምና እህቶች እንደ ምትኖሩ እገምታለሁ። ምን መሆን ይፈልጋሉ? የዋህ? መርህ አለዎት?
ሰላም!

ከታች አስተያየት ወይም ኮከብ ለመስጠት ያስታውሱ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!