በቅርብ ጊዜ የገቡ
መቼ ይሆን እኔ ለውጦች የማይበት?
ቀኖቹ ተቆጥረው ወራት ይሰፍራሉ፣
ወራትም ተቆጥረው ዓመት ይሞላሉ፣
እንዲሁም ዓመታት ዘመን ይለያሉ።
የሚገርም እኮ ነው እንዲህ በድንገት፣
ይቺ ጊዜ እሚሏት አላት ብልሃት፣
ይዛ ትመጣለች አዲሱን ዓመት፣
ከተፍ ትላለች ሰው ሳይነቃባት።
እራሴን ስጠይቅ በዚህ አዲስ ዓመት፣
ቁጥር ጨመረና ምንድነው የኔ እድገት?
አዲስ ዓመት ቢሆን ልክ እንደ መስታዎት፣
ምን አንዳደረኩኝ ልኩን የማይበት፣
እያልኩ ጠየኩት እራሴ በድንገት፣
መቼ ይሆን እኔ ለውጦች የማይበት።
በሃሳብ መጠየቅና መተዋወቅ፤ ክፍል ፪
ማውራትና መጠየቅ ብቻውን ሙሉ አያረግም፡፡ አንድ ሰው ሁሉንም ጥያቄ መፍጠር አይችልም፡፡ አንድ ሰው ለሁሉም ነገር መልስ ሊኖረው አይችልም፡፡ የሆነ ነገር ተጠይቀን የማናውቀው ከሆነ፤ ደፍረን አላውቀውም ማለት ይሻላል፡፡ እኔ ይኸን አሁን አላውቀም፡፡ ወደፊት ግን ማወቅ ....
በሃሳብ መጠየቅና መተዋወቅ፤
ማዳመጥና መጠየቅ ህይወታችን ውስጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ ለምሳሌ ሁላችንም በሚባል ደረጃ ስንደመጥ ደስ ይለናል፡፡ የኛን ፍላጎት ለመረዳት ሰው ዝግጁ ሆኖ ቀርቦ ፍላጎት ሲያሳይ ዋጋ እንሰጠዋለን፡፡ የደስታችን ተካፋይ ስናገኝ ያስደስተናል፡፡
መጀመር ላይ የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ምክርና ማሻሻያ ሃሳብ ካለዎት ለኔ በጣም ይረዳኛል፡፡ እዚህ ጣቢያ ላይ የቀድሞው ኢትዮጵያ ተነሺና ታታሪው፤ አሁን ደግሞ መጀመር ዶት ኮም ላይ የተሰጡ አስተያየቶች ናቸው፡፡ በቅድሚያ አመሰግናለሁ!!
እንኳን ወደ ልዩ "መጀመር"ጣቢያ መጡ!
ፋንታው እባላለሁ፡፡ ኢትዮጵያ እንዴት ብላ ማደግ ትችላለች እያሉ አስበው ያውቃሉ? አስተሳሰብዎ አንደኛ ደረጃ እንዲሆን ይፈልጋሉ? ለሃገሬ ምን ላርግ እያሉ ውስጥዎ ይቃጠላል? አስተሳሰብዎን ማስተዳደርና መቆጣጠር ይፈልጋሉ? ....