ስኬት የሚጀምረው ከገንቢ አስተሳሰብ ነው፡፡ በተቃራኒ ደግሞ ውድቀት የሚጀምረው ከአፍራሽ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ግን ገንቢ መሆን ይወዳል፡፡ ገንቢ ለመሆን ምን ይጠበቅብናል? አፍራሽ አስተሳሰብ እንዴት መቀነስ እንችላለን? ሁለቱንም ለማስረዳት ይፈቀድልኝ፡፡ ገንቢ አስተሳሰብ ለሁለት ይከፈላል፡፡
፩ኛ) ቁሳዊ አስተሳሰብ፤
፪ኛ) ሰዋዊ አስተሳሰብ፡፡
ሁለቱም አስተሳሰቦች ያስፈልጉናል፡፡ ሁለቱንም በተራ ለማስረዳት ልሞክር!
ቁሳዊ አስተሳሰብ ማለት ለምሳሌ የምንጫወትበት ኳስ፣ የምንኖርበት ቤት፣ የኤሌክትሪክ መብራት፣ የምንበርበት አውሮፕላን፣ የምንጠቀምበት ስልክ ወዘተ የፈለቀበት አስተሳሰብ ማለት ነው፡፡ ይኸ ቁሳዊ አስተሳሰብ ከራስም አልፎ ለህብረተሰብ፣ ለሃገርና ለሃገራት የሚጠቅም ነው፡፡ የዚህ ቁሳዊ አስተሳሰብ ዋና ምንጩ ህይወታችን ቀላል እንዲሆን የምናደርገው ፍላጎታዊ ትግል ነው፡፡ ምክንያቱም ለመጫወት ኳስ ያስፈልገናል፡፡ ለመኖር ቤት ያስፈልገናል፡፡ እሩቅ ሃገር ቶሎ ለምድረስ ዘመናዊ መጓጓዢያ ያስፈልገናል፡፡ ሲጨልም የኤሌክትሪክ መብራት ያስፈልገናል፡፡ ከተረዳችሁኝ ምሳሌዎቹ ብዙ ናቸው፡፡
ሰዋዊ አስተሳሰብ፤
ሰዋዊ አስተሳሰብ ልክ እንደ ቁሳዊ አስተሳሰብ በስም ለማስረዳት ቀላል አይደለም፡፡ ግን ልሞክር፡፡ ሰላም መባባል አስፈላጊ ቢሆንም ተራ ነገር ነው፡፡ እንኳን ሰው ቀርቶ፤ እንሰሳትና አራዊትም በራሳቸው መንገድ ሰላም ይባባላሉ፡፡ ሰዋዊ አስተሳሰብ ግን ከዚህ ከፍ ያለ ነው፡፡ ሰዋዊ አስተሳሰብ ማለት አይተንና አዳምጠን የሰወች ፍላጎትና ሁነታ ምን እንደሆነ ማወቅ መቻል ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ ሰወች ሲቸገሩና ሲያጡ መርዳት ባንችልም ችግራቸውን ማባባስ የለብንም፡፡ ሰወች ሲሳካላቸው አብረን የደስታቸው ተካፋይ ባንሆንም ምቀኛ መሆን የለብንም፡፡ ሰወች ሃዘን ላይ ሲሆኑ አብረን ከነሱ ጋር ተቀምጠን ባናለቅስም ልባቸው እንደተሰበረ እውቅና መስጠት ይጠበቅብናል፡፡ ገንቢና ሰዋዊ አስተሳሰብ ያላቸው ሰወች ጋር ወዳጅነት መግጠምና አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ከአፍራሽ አስተሳሰቦች ያርቃል፡፡
ዋነኛ ሰዋዊ ገንቢ አስተሳሰብ ማለት አንድ ሰው ለራሱና ለህበረሰቡ ጠቃሚ ለመሆን የጋለ ፍላጎት ሲኖረው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የትኛውም አስተሳሰብ በህይወታችን ላይ ከፍተኛ አወንታዊ ቅርጽ አለው፡፡ የጋለ ጥሩ ፍላጎት ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ የተሻለ ሰው እንዲንሆን ይገፋፋናል፡፡ በተጨማሪ የጋለ ፍላጎት ስለሚጮህ ውጤቱን ለማየት ይናፍቃል፡፡ ያጓጓል፡፡
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች