mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

መርህ ምንድነው?

mejemer ethiopia hero how

ርህ ማለት የሰው ልጅ በህይዎቱ ውስጥ ለማድረግ የሚፈልገው ሚዛናዊ ሀሳብና እምነት ነው። መርህ ጥርት ያለ ይዘትና ግብ አለው፡፡ ለምሳሌ እውነት መናገር፤ ርህራሄ ማሳየት፤ ጥያቄ መጠየቅ፤ መርዳት፣ ለመማር ዝግጁ መሆን፣ በደንብ መስራት፣ ለመከባበር ትልቅ ቦታ መስጠት፤ አሳታፊ የሆነ ሀሳብ ማቅረብ ጥሩ መርህ ናቸው። ሰወች ይቀያየራሉ። መርህ ግን አይቀየርም። ምክንያቱም እውነት ምን ጊዜም አለ። ትምህርት ይቀጥላል። ርህራሄ አይጠፋም። ጥያቄ አያልቅም። መከባበር ከፊታችን አለ። ስራ ሞልቷል።

መርህ በግልና በህብረት መርህ ግለሰብ ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ተቋማት እንዴት እንደሚሰሩ መመሪያ ይሆናል። በተለያየ ደረጃ ላይ ያሉ መሪዎች ሃላፊነታቸውን እንዴት እንደሚወጡ መመሪያ ይሆናል። ቤተሰብ ልጆቻቸውን እንዴት እንደ ሚያሳድጉ አቅጣጫ ያሳያል።

መርህ እና ህሊና ጥሩ መርህ ያለው ሰው የበሰለ ህሊና አለው። ምክንያቱም በህይዎቱ ውስጥ ያስፈልጋል ብሎ የሚኖርለት ሀሳብ እና እምነት አለው። ከላይ የተጠቀሱት ሀሳቦች ማንንም አይጎዱም። ጥሩ መርህ ከባህል እና ሃይማኖት ይበልጣል። ባህል እና ሃይማኖት ሃገረኛ ናቸው። መርህ ግን በአንዲት ሃገር ውስጥ ብቻ የተወሰነ አይደለም። መሬትና ውቅያኖስ ያቋርጣል። ማንኛውም ዜጋ ተመሳሳይ መርህ ሊኖረው ይችላል። መርህ የሚከተል ዜጋ አስተዋይ እና የሰለጠነ ዜጋ ነው።

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

Avatar
New
Mulualem Adamsays...

ጥሩ ብለሃል ወንድሜ ፋንታዉ