mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

መልካም አዲስ አመት 2023

mejemer ethiopia amharic happy new year 2023

አውሮፓውያን 2023 ሊገባ ነው። 2022 ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ጦርነት፣ እልቂት እና የኑሮ ውድነት የናረበት አመት ነበር። እንደ ምልክቱ ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰላም እና መረጋጋት አይገኝም። ኑሮና ሃሳባችን ላይ ዘዴ መጨመር እንዳለብን የሚጋብዝ ጊዜ ውስጥ እንገኛለን። ገንዘባችንም በሆነ ባልሆነው እንዳይባክን ጥንቃቄ ማድረግ እና መቆጠብ አለብን። ኮሮናም ከመጣ ጀምሮ አኗኗራችን ተለውጧል።

ኢትዮጵያም ፈተና ውስጥ ነች፤ ኢትዮጵያም ፈተና ውስጥ ነች። የዲያስፖራ ፌስቡክ ጽሁፍ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ፈተና የሚቀንስ አይደለም። መድረኩን ለሚችልበት ሰው ግን መጥፎ ቦታ አይደለም። ሆኖም ግን እኔ mejemer dot com ላይ ጽሁፎች ማስገባት ካልሆነ በስተቀር ፌስቡክ ላይ ተሳትፎየ በጣም በጣም ዝቅተኛ ነው። መከታተልም ቀንሻለሁ። ምክንያቱም የሆነ ነገር ሳይ ትምህርት የሚሰጠኝ መሆን አለበት። ሆኖም ግን ሰው ነኝ እና አንዳንድ ጊዜ አያስችልም። በጣት የሚቆጠሩ አስተያየቶች ሰጥቻለሁ። ምናልባት 2022 ላይ በአስተያየቴ ያስቀየምኳችሁ እህቶችና ወንድሞች ካላችሁ ይቅርታ!

ሰላም እንፈልጋለን፤ እርግጠኛ ነኝ ብዙዎቻችን ሰላም እንፈልጋለን። ተፈታታኝ ችግር ግን በመደበኛ አስተሳሰብ መፍትሄ አያገኝም። የለመዱት ሃሳብ ምቾት ይሰጣል። ከሳጥኑ ውጪ ያለውን እውነተኛ ስዕል ግን አያሳይም። አዕምሮአችን ውስጥ ያለውን ማዞሪያ ትንሽ ማነቃነቅ ያለብን ይመስለኛል። በዚህ መልኩ ብትረዱት አመሰግናችኋለሁ። ግልጽ መሆን በጣም እወዳለሁ። ሂስ ሲሰጠኝ ደግሞ እማራላሁ እንጂ አልሸሽም። እርግጠኛ ነኝ ሰወች በእኔ ላይ የሆነ ግምት ይኖራቸዋል። እኔም ደግሞ ሰወች በሚያቀርቡት ሃሳብና በሚሰጡት አስተያየት ተነስቼ የሆነ ግምት ይኖረኛል። እውነትም ፌስቡክ!! ፍጹም ነገር የለም። ሁላችንም ግን የተሻለ ሰው መሆን እንችላለን። እኔ በበኩሌ ለራሴ ቃል ገብቻለሁ።
ሰላም!!
መልካም አዲስ ዓመት!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!