mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ሶፍትዌር ባጭሩ ምንድነው?

mejemer computer software

ፍትዌር ማለት ባጭሩ አንድ ነጠላ ተግባር ማከናወን የሚችል የትእዛዞች ጥርቅም ማለት ነው፡፡ እነዚህም ነጠላ ሶፍትዌሮች ለምሳሌ ሰነድ መጻፊያወች፣ ኢንተርኔት መቅዘፊያወች፣ ጨዋታወች፣ ስእል መሳሊያወች፣ ፎቶና ቪዴወ ማቀናበሪያወች፣ ወዘተ ናቸው፡፡ እንደተጠቃሚው ፍላጎትና ስራ አይነት በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡

ለምሳሌ የማይክሮሶፍት ኦፊስ ወርድ ለተለያዩ ሰነዶች መጻፊያ ያገለግላል፡፡ ኤክሰል ማጥለያና ሁነታወች ማሰባሰቢያ ሰነዶች ማዘጋጃ ይሆናል፡፡ ፓወርፖይንት ደግሞ በዋነኝነት የስብሰባ አጀንዳና እቅድ ለማሳየት ያገለግላል፡፡ ምሳሌውን ጠቀስሁ እንጂ ሶስቱም እንደተጠቃሚው ችሎታና የስራው አይነት ብዙ አይነት ስራወችን ያከናውናሉ፡፡ ሌሎችም የድምጽ፣ የቪዴወ፣ የሂሳብ፣ የቀን መቁጠሪያ፣ ወዘተ ሶፍትዌሮች በያይነቱ አሉ፡፡ ሌሎችም በነጻና በግዢ የሚገኙ የተለያዩ በሺወች የሚቆጠሩ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡

ብዙ ኢትዮጵያውያን ለምሳሌ ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ኦፊስን አደናግረው ይናገራሉ፡፡ ራምና ካዝናን አደባልቀው ይናገራሉ፡፡ ጥያቄ ሲጠይቁም ለምሳሌ ልክ ቤት ከገዙ ወይም ከተከራዩ በኋላ እቤት ውስጥ ገብተው ወንበሩ ለመቀመጫ መሆኑን ዘንግተው ለምን እንደሚጠቀሙበት ደውለው የሚጠይቁም አሉ፡፡ ነገሩ አስቂኝ ነው፡፡ ግን ይደርሳል፡፡ በተጨማሪ አንድ ሶፍትዌር እንደሰሪው ብዛትና ፍላጎት ብዙ አይነት ዝርያ አለው፡፡ ይኸ ደግሞ ተጠቃሚወች ብዙ ምርጫ እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡ አንድ ተጠቃሚ የሚያስፈልጉትን መምረጥና መጠቀም ይችላል፡፡ ለምሳሌ የኢንተርኔት መቅዘፊያወች የተለያዩ እንደሆኑ ሁሉ ሌሎችም ሶፍትዌሮች የተለያየ አይነት አላቸው፡፡ በተጨማሪ ሶስፍትዌር የትእዛዝ ጥርቅም ስለሆነ ለምሳሌ አንዱ የፎቶ መስሪያ ሶፍትዌር ብቻ ላይ እንደ አይነቱና ትልቅነቱ ቢለያይም በመቶና በሺ የሚቆጠሩ ትእዛዞች አሉት፡፡

ምሳሌ ፎቶው ላይ የተለያዩ ቀለሞችንና መጠን ለመቀየር፣ ለማሳመር፣ ለማበላሸት፣ ለመደረብ፣ ለመደባለቅ፣ ቅርጽ ለመቀያየር፣ ወዘተ የሚያስችለው የፎቶው ሶፍትዌር ሰሪ እነዚህን የትእዛዝ ጥርቅሞች ስላዋቀረው ነው፡፡ እንደጠቀስሁት የነጻም ሆነ የሚሸጡ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ ጥራታቸው ይለያያል፡፡ ብዙውን ጊዜ የሚገዙት የተሻሉ ቢሆኑም የነጻም ሆነው ከሚሸጡት በላይ የሚሻሉ አሉ፡፡ እንደተጠቃሚው ችሎታ ፍላጎትና ቅምሻ ይለያያል፡፡ ባሁኑ ጊዜ የነጻ ሶፍትዌሮች ብዙ ስለሆኑ መግዛት የማይፈልጉ ተጠቃሚወች ጥቂት አይደሉም፡፡ በተረፈ እዚህ ድረስ ስላነበቡ አመሰግናለሁ፡፡ አስተያየት ለመስጠት አይርሱ፡፡

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!