mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

የኮምፕዩተር ውስጥና ውጭ አካሎች ስራ ድርሻ

mejemer computer hardware

መጀመሪያው ክፍል ላይ ኮምፕዩተር ምን እንደሆነና በአራት ዋና ዋና ክፍሎች እንደሚከፈል አቅርቤ ነበር፡፡ በተጨማሪም እነዚህ አራት ክፍሎች ምን እንደሆኑና ስማቸውም ተጠቅሶ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ እንዴት እንደሚሰሩ በዝርዝር ይቀርባል፡፡ ይኸን ሁለተኛውን ክፍል በሚገባ ለመረዳት የመጀመሪያውን ክፍል ማንበብ አለብዎት፡፡

ዋና ካርድ motherboard

ዋና ካርድ motherboard የመጀመሪያው ምስል ነው። ለመረዳት እንዲቀል ዋና ካርዱን በመጀመሪያ አብራራለሁ፡፡ ዋና ካርዱ የኮምፕዩተር ዋና መሰረታዊ የአካል ክፍል ነው፡፡ ምክንያቱም ማንኛውም የውስጥም ይሁን የውጭ የኮምፕዩተር ክፍል ዋናው ካርድ ላይ ስለሚሰኩ ነው፡፡ ዋናው ካርዱ የተለያዩ የኮምፕዩተር አካሎች እርስ በርሳቸው እንዲገናኙና ተባብረው እንዲሰሩ የመገናኛ መንገድ ወይም ሃዲድ አለው፡፡

central processing unit፤ አማካይ አዛዥ

አማካይ አዛዥ central processing unit፤ አማካይ አዛዡ የኮምፕዩተሩ አዕምሮ ነው፡፡ አማካይ አዛጁ ከሃርድዌርና ከሶፍትዌር የሚመጡትን ትእዛዞች ለማስተናገድ ሃላፊነት አለበት፡፡ በአንድ ሰከንድ ውስጥ በሚልዮን የሚቆጠሩ ትእዛዞችን ማስተናገድ ይችላል፡፡ አማካይ አዛዡ የተለያዩ ትእዛዞችን በፍጥነት ስለሚያተናግድና ስራ ስለሚበዛበት በጣም ይሞቃል፡፡ ስለዚህ እራሱን የቻለ ማራገቢያ ካናቱ ላይ አለው፡፡ ትእዛዙንም ለማስተላለፍ ዋናው ካርዱ ላይ ትእዛዝ በሚዘዋወርባቸው ብዙ እግሮቹ ተሰክቶ ይቀመጣል፡፡ አማካይ አዛዡ ከሌሎች አካሎች በበለጠ እጅግ በጣም ውስብስብ በሆነ ቴክኖሎጂ የተሰራ ነው፡፡

cd/dvd rom፡ የሲዲ ዲቪዲ ቤት

ሲዲ ዲቪዲ ቤት cd/dvd rom፡ የሲዲ ዲቪዲ ቤት እንደሚታወቀው ሲዲ ዲቪዲ ላይ ሙዚቃ፣ ቪደወ፣ ፎቶ፣ ሶፍትዌር፣ ወዘተ የመሳሰሉትን ለማንበብ ነው፡፡ ወይም ዴታወቹን ሲዲ ዲቪዲ ላይ ለማቃጠል ነው፡፡ የሲዲ ዲቪዲ ቤቱ ከዋናው ካርድ ጋር እንዲገናኝ እንዲሁም ትእዛዝ እንዲቀበልና እንዲልክ በብዙ ሽቦወች ከዋና ካርዱ ጋር ይያያዛል፡፡

ካዝና

ካዝና HD-Hard Drive ወይም SSD-Solid State Drive፤ የካዝና ዋና አገልግሎቱ ዴታወችን በቋሚነት ቆጥቦ ለመያዝ ነው፡፡ ለምሳሌ የሆነ ሰነድ ጽፈው መቆጠብ ከፈለጉ የሚቆጠበው ካዝናው ላይ ነው፡፡ እንደተለመደው ካዝናው ዋና ካርዱ ላይ ይሰካል፡፡ ካዝናው ዴታ ሲያነብና ሲጽፍ ማግኔታዊ ነው፡፡ የውስጥም ሆነ የውጭ ካዝና አለ የዚህ አይነት ካዝና ከፍተኛ ንቅናቄ አይወድም ለምሳሌ ኮምፕዩተርወ ከጠረንጴዛ ላይ ከወደቀ እንዳወዳደቁ ቢሆንም ካዝናው ሊበላሽ ይችላል፡፡ ባሁኑ ጊዜ ግን 2104 ፍላሽ እና SSD ካዝና የሚባሉ ግን ውድ የሆኑና በቀላሉ የማይበላሹ ካዝናወች አሉ፡፡

ቁልፍ ሰሌዳና አይጥ

ኮምፕዩተር ውጫዊ አካሎች አንዳንዶቹ ቁልፍ ሰሌዳና አይጥ ናቸው፡፡ ከዋናው ካርድ ጋር በሽቦ የተያያዙ ወይም ሽቦ-አልባ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ተጠቃሚው መጻፍ ሲፈልግ ቁልፍ ሰሌዳው ላይ ፊደላት፣ ቁጥሮች ወይም ሌሎች ምስሎች እየመታ ይጽፋል፡፡ በአይጧ ደግሞ እየጠቆመ ወይም ጠቅ እያደረገ ትእዛዞችን ያከናውናል፡፡ እየተመቱ የሚጻፉትና ጠቅ የሚደረጉት ክንውኖች ማሳያው ላይ ስለሚታዩ ተጠቃሚው በቀላሉ መከታተል ወይም መቀያያር ይችላል፡፡

ራም RAM-Random Access Memory፤

ራም የተቀሰቀሱ ወይም የተከፈቱ ፕሮግራሞች እንዲነዱ የሚጠቅም ነው፡፡ የተቀሰቀሱትም ፕሮግራሞች በማሳያው እይታ ላይ እንዲቆዩ ይረዳል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ኮፕዩተሩ እነዚህን የተቀሰቀሱ ፕሮግራሞች ለጊዜው ተቀስቅሰው እስካሉ ድረስ ለምሳሌ ከካዝና ወይም ከሲዲ ከማንበብ ይልቅ ከራም ላይ ያነባቸዋል፡፡ ይህ ማለት ራም ጊዚያዊ ፕሮግራም ተሸካሚ ግን በፍጥነት አቅራቢ እንደማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አንድ ተጠቃሚ ኢንተርነት የሚቀዝፍ ከሆነ ቀዛፊውን ይጠቀማል፡፡ ሰነድ የሚጽፍ ከሆነ ወርድን ይጠቀማል፡፡ ፎቶ ወይም ቪደወ የሚሰራ ከሆነ የፎቶና የቪደወ ፕሮግራሞች ይጠቀማል፡፡ እና እነዚህ ፕሮግራሞች እስከተከፈቱ ድረስ ራም ለጊዜው ተሸክሞ ይይዛቸዋል፡፡ ለዚህም ነው ራም ከፍ ባለ ቁጥር የኮምፕዩተሩም ፍጥነት የሚጨምረው፡፡ ያው አማካይ አዛዢም እራሱን የቻለ ሚና ቢጫወትም ራም ልክ እንደሌሎቹ ክፍሎች ዋና ካርዱ ቦታ ስላለው እዛ ይሰካል፡፡

power supply-PS ሃይል አዳዩ

ይል አዳይ power supply-PS የሃይል አዳዩ ስራ የኤሌክትሪክ ሃይልን መጥኖ ለተለያዩ የአካል ክፍሎች ማደል ነው፡፡ ሁሉም የኮምፕዩተር አካል ክፍሎች አንድ አይነት የኤሌክትሪክ ሃይል ቮልት አይጠቀሙም፡፡ ስለዚህ የሃይል አዳዩ ቮልቱን መጥኖ ለሁሉም ክፍሎች ይድላል፡፡ ለምሳሌ 12 ቮልት 9 ቮልት 6 ቮልት 48ቮልት ሊሆን ይችላል፡፡ ሃይል አዳዩ በሙቀት እንዳይግል እራሱን የቻለ ማራገቢያ አለው፡፡

የድምጽ ካርድ Sound Card

የድምጽ ካርድ Sound Board ኮምፕዩተሩ ድምጽ እንዲያመርት የሚያስችል ነው፡፡ ድምጽ ካርዱ ለድምጽ ማውጫ ወደ ድምጽ ማጉያ ማያያዢያ አለው፡፡ የድምጽ ማጉያና ካርዱ ጥራቱ በጨመረ ቁጥር የተሻለ ድምጽ ያሰጣል፡፡

ቪደዎ ካርድ Video Card

ስክሪኑ ምስል፣ ፊዴልና ቀለም የሚያሳየው በቪደዎ ካርድ ታግዞ ነው፡፡ ለምሳሌ የሚያነቡና የሚጽፉ ከሆነ ፊደዎ ካርዱ ማሳያው ላይ እንዲታይ ያደርጋል፡፡ ፎቶና ቪደወም የሚያዩ ከሆነ ቪደወ ካርዱ ማሳያው ላይ ያሳያል፡፡ ተጠቀሚው የሚያያቸውና የሚያደርጋቸው ነገሮች በሙሉ እንዲታዩ የሚያደርገው ቪደወ ካርዱ ነው፡፡

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!