mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

የኦፕሬቲንግ ሲስተም እንክብካቤ እና ደህንነት

mejemer computer security

ታወቁትና ዋና ዋና ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ዊንዶውስ፣ ማክ እና ሊነክስ ናቸው፡፡ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ማለት ምን እንደሆነ በፊት በቀላሉ አስረድቻለሁ፡፡ ብዙ ሰው ዊንዶውስ ለጥቃትና ለስለላ የተጋለጠ ነው፡፡ ይህ ማለት ዊንዶውስ ለመጠቃት ብዙ ቀዳዳ ስላለው በተደጋጋሚ ይጠቃል፡፡ በተለይ ተጠቃሚው ቀላልና ተገቢ ጥንቃቄ ካላደረገ ሳይታወቅ ጭምር ብላሽ ሶፍትዌሮች ኮምፕዩተሩ ላይ ሊሰፍሩ ይችላሉ፡፡

እነዚህን ብላሽ ሶፍትዌሮች ለማስወገድ አንቲ-ቫይረስ እየተባሉ የሚሸጡ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ እነዚህ ሶፍትዌሮች 100% ሊረዱ አይችሉም፡፡ ሆኖም ግን አንቲ-ቫይረስ እየተባለ ተጠቃሚው ተጨማሪ ሶፍትዌር እንዲገዛ ይደረጋል፡፡ ለአንዳንዶች ንግድና መኖሪያ እንጀራ ነው፡፡ ዊንዶውስ ስራወችን ኮምፕዩተሩ ላይ ለማከናወን ከጊዜ ወደ ጊዜ ዘገምተኛ መሆኑ የተለመደ ነው፡፡ ማይክሮሶፍት፤ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ቢያመርትም ሃርድዌሩንና ሌሎች ተጨማሪ ሶፍትዌሮች ግን በሌላ ድርጂት የሚመረቱ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ዊንዶውስን ለተጨማሪ ጥቃት ያጋልጠዋል፡፡

ማክ አፐል የሚባል ድርጂት የሚሰራው ነው፡፡ አፐል የኮምፕዩተሩን ሃርድዌር፣ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙንና ተጨማሪ ፕሮግራሞችንም በራሱ ዘይቤ ይሰራል፡፡ በዚህም ምክንያት ሲስተሙ ከዊንዶውስ የበለጠ ዝግ ስለሆነ በቫይረስ የመጠቃቱ እድል አነስተኛ ነው፡፡ ለስለላ የመጠቃት እድሉ አነስተኛ ነው፡፡ ሽያጭን በተመለከተ የማክ ዋጋ ከዊንዶውስ ይበልጣል፡፡ ብዙ ግራፊክስ ነክ የሚሰሩና የዜና አውታሮች ይጠቀሙበታል፡፡ ማክ እኔ ተጠቅሜ አላውቅም ግን ማክ አስተቸገርኝ የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ሆኖም ግን አንድ ሰው ማክን ጊዜ ተጠቅሞ ከተለማመደ በዛው ይቀራል ይባላል፡፡

ነክስ ባጭሩ ኮዱ ክፍት ምንጭ ነው፡፡ በአለም ውስጥ ባሉ ስማርት ህብረተሰቦች የሚሰራ ነው፡፡ ለመጠቀም ነጻም ነው፡፡ ሰሪው ህብረተሰቡ ገቢ የሚያገኘው በልገሳና በድጋፍ ሰጪወች ነው፡፡ ሊነክስን ማጥቃት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ሊነክስ በህብረተሰብ ስለሚሰራና ስለሚዳብር ሊነክስ ላይ የመጠቃት ጥርጥራ ከታየ ወዲያውኑ ስለሚነቃ ቶሎ ብሎ ህብረተሰቡ መፍትሄ ያገኛል፡፡ ቀዳዳው ይደፈናል፡፡ ችግሩ ይታረማል፡፡ ግለሰቦች ሊነክሰን ልክ እንደ ዊንዶውስና ማክ መጠቀም ይችላሉ፡፡ ሊነክሰን የበለጠ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ትልልቅ ካምፓኒወች፣ ድረጅቶች፣ ባንኮች፣ መንግስቶች፣ ወዘተ ሰርቨራቸው ላይ ሊነክስን በሰፊው ይጠቀማሉ፡፡ ምክንያቱም ሊነክስን መጠቀም ነጻ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ደህንነቱ ከፍተኛ ነው። ፍጥነትም አለው፡፡

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!