mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ቅዤት

mejemer ethiopia amaharic nigthmare

ልጆቹ ተባብረው፣
በቋንቋ ተግባብተው፣
በሃሳብ ተሳስረው፣
በልብ ተዋህደው፣
በአዕምሯቸው ነቅተው፣
በነቂስ ተነስተው፣
አሮጌውን ጥለው፣
ካለፈው ተምረው፣
አዲሱን አንግበው።

አምላክም አየና በጣም ተደስቶ፣
እሰይ የኔ ልጆች ሲላቸው ተኩራርቶ፣
አንድ ሰውም ቢሆን እንዳይቀር ተረስቶ፣
እንዳይጠፋባችሁ ወደኋላ ቀርቶ።

ሲላቸው ሰማሁኝ፣
በጣም ተደሰትኩኝ፣
ወደኋላ እንዳልቀር ቶሎ ገሰገስጉኝ።

እኔም ደረስኩና ልሆን አብሬያቸው፣
ቆሜ ከጎናቸው፣
እቅፍ አረኩና መሳም ጀመርኳቸው።

ናፍቆቴን ሳልጨርስ፣
ገና ስተነፍስ፣
ከመስማቴ በፊት የወገኖቼን መልስ፣
ባንኜ ተነሳሁ እንቅልፌን ሳልጨርስ፣
እየቃዤሁ ነበር በሞቀኝ ብርድ-ልብስ።

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!