mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ዋጋ ተወደደ፤ ናላየ ዞረብኝ ሰሞነኛ!

mejemer ethiopia amaharic expensive

በቀን ሶስት ጊዜ ምግብ እንድትበላ፣
ከተሳካ ደግሞ ጨምረህ አስገባ፣
ብለው ጽፈው ነበር የተማሩት አባ።

ይቺን ሶስት ቁጥር በየቀኑ እትርሳ!
በጤናህ ባካልህ እንዳይደርስ አበሳ፣
ማስላትም ማሰብም እንዳትዘነጋ።

ዛሬም ሶስት ጊዜ ምግብ አስፈለገኝ፣
መጠጥ ሲሆን ግን ቁጥሩም ትዝ አላለኝ፣
የጠየቀኝ የለ ስንቴ እንደጠጣሁኝ፣
ሻጩ ብቻ ቀርቦ ጠጥተሃል አለኝ፣
ለምግቡ ሲሆን ግን ምንም አልጠየቀኝ፣
ለካ ጽፎት ነበር ስንት እንደበላሁኝ፣
ስንቴ ተናገርኩኝ?
ስንት ሰው ጠላሁኝ?
ስንቴና ስንት እኔን ምነው አስቸገሩኝ?

ሁሉንም ደምሮ ዋጋውን ነገረኝ፣
የሬስቶራንት ዋጋ ዛሬስ አሳበደኝ፣
ከቤቴ እንዳልበላ የቆጠብኩ መስሎኝ፣
ወይም መጀመሪያ ማሰብ ነበረብኝ፣
ሲያቀብጠኝ ወጥቼ ያለኝን ጨረስኩኝ!

በስንትና ስንቴ የሚቀልድ መስሎኝ፣
ዋጋ ቀንስልኝ?
ማስላት ትችላለህ!! አለና ሳቀብኝ፣
አይቀንስም አለኝ፣
ያን ሁሉ አስከፈለኝ፣
ናላየን አዞረኝ፣
ኪሴ ተገልብጦ ከቤቴ ገባሁኝ፣
መጠጡ ይሆናል እንዲህ ጉድ የሰራኝ?

ዘግይቶ ቢሆንም እንዲህ ነው ማስተዋል፣
ምግብ ብቻ አይደለም መጠጥም ተወዷል!
ህይወት ግን ረክሷል።

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

Avatar
New
leul tadesse(Norway)says...

በትክክል ምግብ እየተወደደ ሰው እየረከሰ ነው