mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ዋይፋይ እና ደህንነት

ፈለክበት ጊዜ በቀላሉ ስለሚገኝ ክፍት የሆነ ዋይፋይ መጠቀም በጣም ተፈታታኝ ይሆናል። ያለህበት ቦታ ምናልባት ሆቴል አውሮፕላን ማረፊያ ሬስቶራንት ካፌ መጽሀፍት ቤት ወይም ባቡር ውስጥ ሊሆን ይችላል። የሆነ ነገር ለማየት ፈልገህ የሆነ መልዕክት ለመላክ አስበህ ወይም ደግሞ የምታደርገው ነገር ይጠፋብህና ኢንትተርኔት ገብተህ ዜና ለመለቃቀም እና ለማውደልደል ሊሆን ይችላል። ዞሮ ዞሮ ግን ማየት የፈለከውን ለማየት የተረጋገጠ ኮኔክሽን እስከምታገኝ ድረስ መጠበቅ ይሻላል። ወይም ደግሞ አስቸኳይ ጉዳይ ካለብህ የዴታ ፓኬጅህን መጠቀም ከሁሉም ይሻላል። በመሰረቱ በተለይ ጉዞ ላይ በምትሆን ጊዜ መጽሀፍ ማንበብ ከፈለክ ወረቀት ላይ ማንበብ ይሻላል። የተሻለ እውቀት ለማግኘት ብቻ ሳይሆን ለአይንህም ይቀለዋል።

ፍት የሆነ የነጻ ዋይፋይ መጠቀም አደገኛ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም የምትልከው መልዕክት እና የምታሳየው እንቅስቃሴ በሌላ ሰው ሊታይ ይችላል። የምትጠቀምበት ነትዎርክ የጋራ ስለሚሆን አንተ ብቻ የምትጠቀምበት የሳሳ መረጃ የግልህ ብቻ አይሆንም። ተንኮለኞች ሊሰርቁህ ይችላሉ። ክፍት የሆነ ዋይፋይ በዚሁ ብቻ አያበቃም። ተንኮል ያዘለ ማጣቀሻ ወደ ስልክህ ሊላክብህ ይችላል። ይኸን ማጣቀሻ ጠቅ በምታደርገው ጊዜ ለጠለፋ ትመቻለህ። ስልክህ ክፍት የሆነ ዋይፋይ ሲያገኝ ደግሞ ሳታውቀው በራሱ እንዳይገናኝ ስልክህ ላይ ያለውን ፈቃድ ማጣራትና መዝጋት አለብህ። በተቻለ መጠን ስትፈቅድ እና ሳትፈቅድ የስልክህ ባህሪ እንዴት እንደሆነ ለማስተካከል ቦታውን ማወቅ ከሁሉም በላይ ቀዳሚ ነው። የሞባይል ስልክ እና የግል መረጃ በጥንቃቄ መያዝ እጅግ በጣም አስፈላጊ ስለሆነ ለጓደኛ ለዘመድ እና ለቤተሰብ ለመንገር ይተባበሩ። ከዛሬው ጥሩ ማሳሰቢያ ጋር መልካም ውሎ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!