mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

የሞባይል ስልክ ክፍል 4፤ አጭር መልዕክት

ጭር መልዕክት ለመላክ የምንጠቀምበት ቴክኖሎጂ፣ በጣም ተወደጅ ነው። በዚህ የተነሳ፣ የሞባይል ስልካችን፣ ለአጭበርባሪዎች የተመቻቸ ኢላማ ነው። ለምሳሌ፣ የሆነ ነገር ወይም ሽልማት ሳያመልጥህ፣ ቶሎ ብለህ እንድትመልስ ይጠይቁሃል። ማንኛውም አይነት የግል መረጃህን፣ እንድታቀብላቸው ይጠይቃሉ። ለምሳሌ በሆነ ነገር እያባበሉ፣ መጠቀሚያ ስምህን፣ ማለፊያ ቃልህን፣ የባንክ ነገርህን፣ የሆነ እቃ የተላከልህ ስለሆነ፣ ቶሎ ብለህ እንድትወስድ ይጠይቃሉ። ማጭበርበሪያ መንገዳቸው ተቆጥሮ አያልቅም! የጋራ ማጭበርበሪያ ወጥመዳቸው ግን ይመሳሰላል። ለምሳሌ እነሱ ወደሚፈልጉበት ቦታ ወይም ወጥመድ እንድትገባለቸው፣ የሚያሳስት ሊንክ ተጭነህ እንዲትገባ ይጠይቁሃል። አንዳንድ ጊዜ ደግሞ፣ የሆነ ፎርም ሞልተህ፣ እንድትልክላቸው ይፈልጋሉ።

መሰረቱ፣ የራስህን የግል ነገር፣ ለማንም አሳልፈህ መስጠት የለብህም። አጭበርባሪዎቹ፣ አንተን ለማሳመን፣ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ለምሳሌ፣ የእውነተኛ ድርጅት የሚያደርገውን ተመሳስለው ይቀርቡሃል። የምታውቀውን የሰው ስም እየጠቀሱ፣ የሆነ ነገር እንድትነግራቸው ሊጠይቁህ ይችላሉ። ሽማግሌ እንደላካቸው ሆነው ሊቀርቡ ይችላሉ። በነገራችን ላይ፣ ሽምግልና፣ አይደለም ሳይታይ፣ እየታየ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያን ዝህብ ለማታተል የተፈጠረ ወጥመድ ይመስለኛል። ለማንኛውም፣ በሆነ ወጥመድ እንዳትያዝ፣ የደረሰህን መልዕክት መጀመሪያ ታያለህ፣ ታስባለህ፣ ትቆማለህ። እነዚህን ሶስቱን የጥንቃቄ ባህሪ፣ ለመከተል ከለመደብህ፣ እውነተኛውን እና ማጭበርበሪያ መልዕክቱን ለመለየት፣ ከባድ መሆን የለበትም። የሰውንም ባህሪ ቢሆን፣ በዚህ መንገድ መመርመር ትችላለህ። ለፍቅረኛህ ሳትመልስ፣ ወይም ሳትመልሺ ቀርተሽ ብትጣሉ ግን፣ የኔ ጥፋት አይደለም። ከዚህ ላይ መቆም ሳይሆን መሄድ ነበረብህ። ሁሉም ነገር፣ በሚዛን እና በልኬት, መታየት አለበት ለማለት ነው።

ለምሳሌ ሸሚዝ ለመግዛት በምንፈልግበት ጊዜ፣ መጀመሪያ አይናችን ማየት አለበት። የሆነ ቀዳዳ ወይም የቆሸሸ ምልክት ካየንበት፣ ለመሞከርና ለመግዛት አናስበውም። ለዚህም ነው አይን እና ጭንቅላት፣ በተቻለ መጠን፣ ስህተት እንዳናበዛ የሚጠቅሙን። ሌላውም ህይዎታችን ቢሆን፣ በስኬት የተላበሰ እንዲሆን፣ ተመሳሳይ እርምጃ ይፈልጋል። ደህንነት በጣም አስፈላጊ ስለሆነ፣ ለጓደኛ፤ ለዘመድ እና ለቤተሰብ ይንገሩ። ከዛሬው ጠቃሚ ማሳሰቢያ ጋር፤ መልካም ውሎ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!