mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

አቀራረብ እና ልብስ

mejemer get the jobb looks and clothes

ቃለ መጠይቅ ሲጠሩ እንዴት ሆኜ ልታይ? ምን ልልበስ? ምን ልጫመት? ምን ልኳኳል? እያሉ ማሰብ አይቀርም፡፡ ልብስ የእርቃን መሸፈኛ ብቻ ነው ብሎ ችላ ማለት አያስፈልግም፡፡ አለባበስ እንደ አየሩ ሁኔታ ይለያያል፡፡ ገላ ከታጠበ በኋላ ንፁህና ከሰውነት ጋር ፊት የሚያደርግ ልብስ መልበስ በቂ ነው፡፡ ጫማ ቢሆንም ንጹህ መሆን አለበት፡፡ ከረባት የግድ ማድረግ አያስፈልግም፡፡ ለጋብቻ እንደተጠራ ሰው አሸብርቆ እና አጊጦ መሄድም ማጋነን ነው፡፡ ባርኔጣ ወይም ኮፍያ የሚጠቀሙ ከሆነ ቃለ ምልልሱ ሲካሄድ መደረግ የለበትም፡፡ ለማንኛውም ባርኔጣና ኮፍያ ቤት ውስጥ ማድረግ የተለየ ዝግጅት ካልሆነ በስተቀር ቦታው አይደለም፡፡ ፈዘዝ ያለ የልብስ ቀለም መምረጥ ለመታየት ቀላልና ተፈጥሯዊ ያደርገዋል፡፡ የቀለሙ ቅንብርና ለሰውነት የሚስማማ ልብስ መርጦ መጠቀም እራሱን የቻለ ችሎታ ይጠይቃል፡፡ ለዚህ እኮ ነው ስንቱ በየመንገዱ ተንከርፎ የሚታየው፡፡ እርግጠኛ ነኝ ለቃለ መጠይቅ ተጠርቶ እንደዛ ሆኖ መታየት የሚፈልግ ሰው አይኖርም፡፡

ስለዚህ ለእርስዎ የሚስማማ የልብስና የጫማ አይነት መምረጥ ከባድ መሆን የለበትም፡፡ ጥፍር መከርከምና ፀጉር መበጠር አለበት፡፡ ከሩቅ የሚጣራ ሽቶ ያስገምታል፡፡ የከንፈር ቀለምና ኩላኩል ነገርም ማብዛት ለስራ ቃለ መጠይቅ ቦታው አይደለም፡፡ ሌላ ጊዜም ቢሆን ኬሚካል ነገር ለጤና ጥሩ አይደለም፡፡ ደረትና ጡት ባይጋለጥ ይመረጣል፡፡ ለምሳሌ ወንዶች አንገት የሚደርስ ሙሉ ክብ ሹራብ ለብሰው ኮት ወይም ጥሩ ጃኬት ቢደርቡበት ያምርባቸዋል፡፡ ሴት አመልካቾች ደግሞ ከልብሳቸው ቀለም ጋር የሚስማማ ሻሽ ነገር አንገታቸው ላይ ሸብ አድረገው በደረታቸው ላይ ቢንጠለጠል ያምርባቸዋል ይመስለኛል፡፡ ያየሩ ንብረት ከፈቀደ ሴቶች ቀሚስ ቢለብሱ የተሻለ ሆነው ይታያሉ፡፡

የቃለ መጠይቅ አቀራረብ እና ውይይት፤ እንዴት እንደሆነ በሚቀጥለው ጽሁፍ ላይ ቀርቧል !

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!