mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ለሚሰሩ እጆች

mejemer ethiopia fantaw tesema amharic መጀመር

ምህርት ቤት ስንገባ እጃችን መጻፍ ይለምዳል። አዕምሮ ማሰብ ይጀምራል። ቀስ በቀስ ሃኪም፣ መሃንድስ፣ አስተማሪ፣ ከዋኝ፣ ገበሬ፣ ነጋዴ፣ ጸሃፊ ወዘተ እንሆናለን። ለችግሮች መፍትሄ ለማግኘት እናስባለን። እጆችም አብሮው ይከተላሉ። እከሌ ታታሪ ነው፤ እከሌ ጥሩ ልምድ አለው የሚባለው ለዚህ ነው። እጁ ሰርቶ ያሳያል። ሳንማር እጃችን ቢዘረጋ ለመብላት እና ለጥፋት ይቀድማል። ህይዎት በየቀኑ ትምህርት ነች። አፋችን ሲከፈት ምክንያታዊ ቃል ያወጣል። አዕምሮ ያየውን እጅ ይነካል። እጅ የነካውን አዕምሮ ያያል። እጅ ከሌለን አዕምሮ ብቸኛ ይሆናል። አዕምሮ ከደከመ እጃችን ባዳ ነው። እጆችህን ፊት ለፊት ዘርጋና ተመልከታቸው። ምን ይታይሃል? ህይወትህ በሌላ ሰው የተቃኘ ከሆነ እጅህን አታውቀውም። ዛሬ እጅህ ተዘርግቶ ምን አደረገ? ጥሩ ውጤት አሳይተህ ከሆነ እጅህ የሰራውን ስታስብ ደስ ይልሀል። ምናልባት የሰራኸው ስህተት ካለበት፤ ለማሻሻል ነገ ሌላ እድል አለህ።

የሚያሰላ አዕምሮ እና ገጣጥሞ የሚሰራ እጅ ካለህ ለሃገርህ ሸክም እና ውርደት አትሆንም።

ችግርህ መፍትሄ ስትፈልግ የባህል መነጸር የምታደርግ ከሆነ፤ እጅህ ላይ የሚታየው ቀይ ቀለም አረንጓዴ ይመስልሃል። ህይዎት ልክ ወደፊት የምትሽከረከር መኪና አይነት ነች። ሁሉም የመኪና ትራፊክ ቀለም አረንጓዴ ብቻ አይደለም። ቀይ ሲሆን ቆመህ አስብ። ቢጫ ሲሆን ተዘጋጅ። አረንጓዴ ሲሆን ሂድ። የራስህ ኑሮ ሾፌር አንተው ነህ። ኑሮህ በቁጥጥርህ ስር ከሆነ ፈጣሪህ እሰይ የኔ ልጅ ብሎ ይኮራብሃል። ምክንያቱም ታታሪ ሰራተኛ እና ነጻ ሰው ነህ። ለሃገርህ ሸክም አትሆንም። ምክንያቱም የሚያሰላ ሚዛናዊ አዕምሮ እና ገጣጥመው የሚሰሩ እጆች አሉህ። ጽሁፉን እንዴት አገኘኸው?

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!