mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና

ለሚወድ ልብ

mejemer ethiopia amharic መጀመር ኢትዮጵያ ፋንታው ተሰማ አማርኛ

ባችን ከስሜት ጋር የተገናኘ ስለሆነ በቃላት ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው። ነገር ግን የሆነ ነገር ስናይ እና ስንሰማ እንደ አይነቱ ልባችን ላይ ተጽዕኖ አለው። የምንወደው ሰው ሲቀርበን ልብቻን ይደሰታል። ፈገግ ብለን ናፍቆት ለማጋራት እንፈልጋለን። የስጋት እና ድንጋጤ ስሜት ሲሆን ደግሞ ልባችን ይፈራል። የሆነ አደጋ ሊደርስ ይችላል ተብሎ ሲወራ ሰምተን ሊሆን ይችላል። መጥፎ ነገር ደርሶ ስናይ ደግሞ ሃዘን ይሰማናል። የምንወደው ተለይቶን ሊሆን ይችላል። በግላችን ደስ የሚለን ሃሳብ በሌላ ሰው ሲገለጽ ከሰማን እምነታችን ከፍ ይላል። አሁን እኔ የማላውቀው ሌላም የልብ ሚና ይኖራል።

ሰው ልጅ በልቡ ስሜት ብቻ ተመርቶ መወሰን ሲጀምር በራሱ ላይ ስህተት ይጨምራል። ለምሳሌ ዛሬ የተሰማን ትንሽ ቆይቶ ሊቀየር ይችላል። አሁን አደጋ መስሎ የተሰማን ነገ የምናልፈው ፈተና ብቻ ሊሆን ይችላል። ዛሬ የወደድነው ዘላቂ ላይሆን ይችላል። ደስ ለሚለን ነገር የዘፈነልን ሰው እውነቱን ላይሆን ይችላል። ልባችን የሚያየው በመስኮት መስታዎት ላይ የሚፈስ የዝናብ ውኋ ነው። ከቤት ውስጥ ሆነን ውኋውን እናየዋለን እንጂ መንካት አንችልም። በልብ መመራት ማለት ለመወሰን ከጭንቅላት በፊት ልብ ማስቀደም ማለት ነው። የመጨራሻውን ውሳኔ መወሰን ያለበት ግን ጭንቅላታችን ነው።

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ልብህን ተከተል ይባላል። ዞሮ ዞሮ ግን ብልህ የሆነ ልብ ከጭንቅላት ጋር ይተባበራል። ምክንያቱም ልባችን እርህራሄ ጭንቅላት ደግሞ ብልሀት አለው። በልብ ብቻ ከሆነ ምክንያት አናይም። በጭንቅላት ብቻ ከሆነ ደረቅ ያደርገናል። እርህራሄ እና ብልሀት ያለው ሰው ሆኖ ለመገኘት ልብ እና ጭንቅላታችን ተባብረው እንዲሰሩ መፍቀድ አለብን። ሁለቱንም አመዛዝኖ መጠቀም ለጋራ ችግሮቻችን ስር ነቀል መፍትሄ መፈለጊያ መብራት ነው።

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!