የመስራት ባህሪ እና ልምድ" ጽሁፍ ላይ የቪዴዎ ሲግናል የሚያልፍበት ሽቦ ከተጎዳ የቪዴዎ ሲግናሉ ጥራት ይቀንሳል ብየ ጠቅሸ ነበር፡፡ ዛሬ ደሞ ክፍል ሰፋ አድርጌ ለማስረዳት ዝግጁ ነኝ፡፡ የውኋው ታሪክም ከዚሁ ጋር አብሮ በቀላሉ ይቀርባል፡፡ የትም ሃገር ቢሆን፤ በተልይ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ፤ ታዝባችሁ ከሆነ፤ ለምሳሌ ጥሩ ሆቴል ቢሆንም የተበላሸ ቪዴዎ ማየት የተለመደ ነው፡፡ የግል መኖሪያ ቤት ቢሆንም፤ ችግሩ አንድ አይነት ነው፡፡ ዋናው የችግሩ ምንጭ፤ ብዙውን ጊዜ፤ ማስተላለፊያ ሽቦው ላይ ነው፡፡ ያለፈው ክፍል 7 ላይ እንደጠቀስኩት ማስተላለፊያ ሽቦው ልክ እንደ እንቁላል እንክብካቤና ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡
ሽቦው በግድግዳና በጣራ ማዕዘን መካከል ተቀልብሶ ማለፍ አለበት፡፡ በማዕዘኑ መካከል ተስተካክሎ ሲያልፍ አቅጣጫ መቀየር አለበት፡፡ ይኸን አቅጣጫ ለማስቀየር የተለየ መሳሪያ አይፈልግም፡፡ በተለይ ባሁኑ ጊዜ ጥሩ መቅጃዎች እንዳሉ ታውቃላችሁ፡፡ ስልካችንም ቢሆን ደህና አድርጎ መቅዳት ይችላል፡፡ በስልክ ለመቅዳት ግን የመጀመሪያ ምርጫ መሆን የለበትም፡፡ ለማንኛውም፣ መጨረሻ ላይ፤ ሲግናሉ ሲተላለፍ፤ ሽቦው ሲዘረጋ፣ ሲቀለበስና ሲገጣጠም ከተበላሸ፣ የቪዴዎ ጥራት ይቀንሰዋል፡፡
ለምሳሌ በሆነ በቆሸሸ ቱቦ ውስጥ፣ ውኋ ብንለቅበት መውጫው ጫፍ ላይ ውኋው መልኩን ቀይሮ ይወጣል፡፡ ሲግናልም ቢሆን ከዚህ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ለምሳሌ አንቴናው ከፎቁ ላይ የተተከለ የውኋ ገንዳ ጋር ይመሳሰላል፡፡ የገንዳው ውኋ ወደቤት ለመድረስ የውኋው ማለፊያ ቱቦ በየቤቱ ግድግዳና ጣራ ማለፍ አለበት፡፡ እንደ ምታውቁት ውኋው እቤት ከደረሰ በኋላ፤ ሌላ ማከፋፈያ አለ፡፡ ሌላ ማያያዢያ አለ፡፡ ምክንያቱም ውኋው ወደ መታጠቢያ ቤት፣ ወደ ሽንት ቤት፣ ወደ ማድ ቤት መከፋፈል አለበት፡፡ ወደ መኝታ ቤትስ? ቧንቧ መኝታ ቤት ድረስ እንዲዘረጋለት የሚፈልግ ሰው አለ? እኔ በበኩሌ አልፈልግም! ለማንኛውም ሲግናልና ሽቦ ከቧንቧና ውኋ ጋር ይመሳሰላል ለማለት ነው፡፡ ለምሳሌ ገንዳውና የውኋ ቱቦው ንጹህ ካልሆነ፤ የሚደርሰን ውኋ የደፈረሰ ይሆናል፡፡ የቱቦው ማያያዢያና መቀጠያ በደንብ ዝግትና ግጥም ብሎ ካልታሰረ ውኋው ይንጠባጠባል፡፡ አገር ቤት ውኋ እየንተጠባጠበ ችግር የሆነው በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ሲግናልም ቢሆን ሲተላለፍ ባይናችን ስለማይታይ እንጂ በሽቦው ላይ ሲጓዝ ብዙ አይነት ችግር ያጋጥመዋል፡፡
ምክንያቱም ሽቦው ከተጎዳና ማያያዢያው ላይ ግጥም አድርጎ በደንብ ካልታሰረ ሙሉ ሃይሉን ይቀንስበታል፡፡ ሽቦው በግድግዳና በጣራ ላይ በጥንቃቄ ካልተዘረጋ ማስተላለፊያ ሽቦው ስለሚጎዳ ሲግናሉ ይበላሻል፡፡ ይኸ ማለት እንግዲህ፤ እያንዳንዷ የሽቦ ጉዳት፤ የማራዘሚያና የማከፋፈያ ማያያዢያ ቦታ፤ ሲግናሉን ማበላሸት ብቻ ሳይሆን ሃይሉንም ይቀንሰዋል፡፡ ቪዴዎ በሚታይ ጊዜ የሲግናሉ ጥራት መቀነሱን ለይቶ ለማወቅ በጣም ቀላል ነው፡፡ ለምሳሌ በአይናችን እያየነው ይንቀጠቀጣል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከጠፋ በኋላ እንደገና በራሱ ይመለሳል፡፡ ስፈልገው ነበር!!! ስጠብቀው ነበር!!! አሁንስ መጣልኝ!! አመስግናለሁ ይላሉ! ተመልካቾች! እያጨበጨቡ፡፡ አሁን ለቴሌቪዢን ማጨብጨብ ምን ይባላል? ሌላ ጊዜ ደግሞ ብዢዢዢዢ ይልበታል፡፡ የቪዴዎ ጥራት በጣም የወረደ እንደሆነ ለመለየት፤ ልዩ ችሎታ ከማንም አይፈልግም፡፡
አንድ ሰው በሚያየው ቪዴዎና በሚሰማው ድምጽ ላይ ልብ ካለ ቶሎ ብሎ ያውቀዋል፡፡ እውነቴ ነው፡፡ በዚህ በኩል እመኑኝ፡፡ ብዙዎቹ ተጠቃሚወች ይኸን የሚያውቁት ይመስለኛል፡፡ በሰራተኞቹ በኩል ግን ... አሁሁሁሁንንን ጥያቄው መጣ! ሽቦው ሲዘረጋና ቱቦው ሲቀጣጥል በቂ ትኩረት አያገኝም፡፡ ቢያገኝማ ኖሮ ውኋ አያበሽቀንም ነበር፡፡ ቴሌቪዥኑ ደግሞ አይደናገርውም ነበር፡፡ ስራው ካለቀ በኋላ፤ የመጨረሻው ውጤት ቆንጆ እንዲሆን፤ ልባዊ የሆነ የመስራት ፍላጎት ማሳየት ለውጤቱ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡
ማንኛውንም አይነት ስራ በጥራት ለመስራት ልባዊ የሆነ ፍላጎት ስራው ላይ ማሳየት ውጤት ያሳምራል። ህይወታችን ውስጥ የትም ቦታ ቢሆን ልባዊ የሆነ ፍላጎት ማሳየት ከሁሉም በላይ ቀዳሚ ነው፡፡
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች