mejemer.com
ቀላል ፍልስፍና
ፍቅርና ህብረተሰብ የግል ፍቅር የዋህና ፍቅር

ፍቅር የግል ነው

mejemer ethiopia amharic love is private

አለማችን በሰፊው ከሚወራለት ትልቅ ጉዳይ ውስጥ አንዱ ፍቅር ነው። ስለ ፍቅር ብዙ መጽሀፍ ተጽፏል። በወሬም ብዙ ይነገርለታል። በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ፍቅር ትልቅ ቦታ አለው። ግን ፍቅር ለምን አነሰ? ምክንያቱም ሰዎች ፍቅርን ተስማሚ ቦታና ሰው ላይ ለመጠቀም ስለሚቸገሩ ይመስለኛል። ይኸ አጭሩ መልስ ነው። ረጅሙ መልስ ደግሞ እንደሚከተለው ነው።

የፍቅር ትክክለኛ ቦታ፤ የፍቅር ትክክለኛ ቦታ ለፍቅረኛ እና ለባለ ትዳር ነው። ፍቅር ሲይዘን ልባችን ይነግረናል። ልባችን በቃላት የማይገለጽ ሚስጥር ሲነግረን ይሰማናል። በጠረን ሊሆን ይችላል። በፈገግታ ሊሆን ይችላል። ባቀራረብ ሊሆን ይችላል። ለዚህ ነው ወንድና ሴት እርስ በርስ ፍቅር የሚዛቸው። ፍቅር ከወሲብ ጋር ግንኙነት አለው። ነገር ግን ወንድና ሴት እርስ በርስ ተግባብተው አብረው ለመቆየት ፍቅር ያስፈልጋቸዋል። ፍቅር ሁለት ተቃራኒ ጾታዎች አብረው እንዲደሳሰቱ መሰረትና ምሰሶ ነው።

ንድ ህብረተሰብ ግን በሰላም እንዲኖር መከባበር እና እርህራሄ የሰላም ሰንሰለት ናቸው። ከቤተሰብ እና ከፍቅረኛ ውጭ ማንንም አግበስብሶ ማፍቅር አይቻልም። ይኸንን የሚክድ ካለ የሚሰራ ምክንያት አለው ብዬ አላስብም። ለምሳሌ ውሸታምና መጥፎ ሰወች የትም አሉ። ስናያቸው የሚደብሩን ሰወች የትም አሉ። ሲቀርቡን ልባችን የማይፈቅዳቸው ሰወች የትም አሉ። ለምሳሌ ባነጋገራቸው፣ ባቀራረባቸው፣ በንጽህና ጉድለት፣ ሰነፍ ስለሆኑ ሊሆን ይችላል። እነዚህን ሰወች ግን እንጠላቸዋለን ማለት አይደለም። የግል ህይወታችን ውስጥ ተካፋይ እንዲሆኑ ግን አንፈልግም። ይኸ ምርጫችን ነው። ሰው ስለሆኑ ግን ማክበር እና ርህራሄ ማሳየት አለብን። ምክንያቱም መከባበር የጋራ ነው። ፍቅር ግን የግል ነው። ፍቅር እንደሚወራው እርካሽ አይደለም። አንድ ሰው ልቡን ለፍቅር የሚሰጠው ለአንድ ሰው ብቻ ነው። ፍቅርን የጋራ እንደሆነ አስመስለው የሚያወሩ አራት አይነት ሰወች ናቸው። ቄስ፣ ሙዚቀኛ፣ ሞኝና አታላይ ናቸው። አራቱም እንዴት እንደሆኑ ወደፊት እመልስበታለሁ።

ከታች አስተያየት ወይም ኮከብ ለመስጠት ያስታውሱ!

ከታች አስተያየት ይስጡ

* መጻፍ ያለበት
2000

የተሰጡ አስተያየቶች

አስተያየት ገና አልተሰጠበትም። የመጀመሪያው ይሁኑ!