ምግብ እና መጠጥ ከውስጣችን ከገቡ በኋላ ሶስት አይነት ምልክት ያሳያሉ። ምልክቶቹ ከጊዜ ጋር አብረው ይሄዳሉ። 1ኛ) ወዲያውኑ፤ 2ኛ) ትንሽ ቆይቶ፤ 3ኛ) እየቆየ ሲሄድ ባህሪ ይሆናል። 1ኛ) ወዲያውኑ፤ ለምሳሌ አንድ ሰው ተስማሚ ምግብ ከበላ በኋላ ሆዱ አይወጠርም። ሆዱ ውስጥ አየር አይበዛም። 2ኛ) ትንሽ ቆይቶ፤ ምግቡ ሆድ ውስጥ ተረጋግቶ ይቀመጣል። ለመፈጨት ቀላል ነው። መጸዳጃ ቤት ሲወጣ አያስቸግርም። 3ኛ) ከሰነበተ በኋላ ግን የተጠራቀመ የችግር ወይም ጤናማ ስሜት ያሳያል። ይኸ ጽሁፍ በግሌ ህይወት ውስጥ ያገኘሁትን ልምድ ለማካፋል ነው።
ማዳመጥና ምልክት ችግር ከሆነ ለምሳሌ ከመጠን ያለፈ ክብደት መጨመር ሊመጣ ይችላል። የአካልና የመንፈስ ድካም ሊከተል ይችላል። የጤና ከሆነ ደግሞ የቀን ውሎ እና ህይወታችን ቀልጣፋ ይሆናል። ከምግብ በተጨማሪ የአካል እንቅስቃሴ እና በጥሩ መንፈስ መኖር ለጤናማ ህይወት አስትዋጾኦ አላቸው። ሌላ የተለየ ችግር ካለ ደግሞ ሃኪም ማነጋገር አንዱ መፍትሄ ነው። እድሜ እየገፋ ሲሄድ ቦርጭ ይጨምራል ይባላል። ይኸ አባባል ግን ሙሉ በሙሉ ትክክል አይመስለኝም። በእድሜ ምክንያት ምናልባት ጸጉር ይመለጣል። ቆዳ ይጨማደዳል። ቦርጭ የሚጨምረው ግን ከእድሜ ጋር ለሰውነታችን የምንሰጠው እንክብካቤ እና እንቅስቃሴ እያቀነሰ ስለሚሄድ ነው። የምንበላው ምግብ አይነት ላይም የምንሰጠው ጥንቃቄ ስለሚቀንስ ነው።
በልክ የሆነ ተስማሚ ምግብ መመገብ ከባድ አይደለም። ውድ መሆንም የለበትም። አንድ ሰው የሚስማማውን ምግብ ለማወቅ ሰውነቱ ማዳመጥና ፍላጎት ማሳየት አለበት። ለአንዱ ሰውነቱ የተቀበለው የምግብ አይነት ለሌላው ሙሉ በሙሉ አይስማማውም። ምግብና ፈሳሽ ወደ ሰውነታችን ውስጥ ስለሚገቡ ለጤናችን ስንል ጥንቃቄ ልዩ ማድረግ አለብን። ለምሳሌ ልብስ፣ ጫማ፣ መኪና፣ ቤት ወዘተ ጤናችን ትክክል ካልሆነ ብዙ ሊያስደስቱ አይችሉም። ምክንያቱም ውጫዊ ናቸው።
ነገርስ ከሆነ እንዴት ነው? ማንኛውም አይነት ነገር ቀስ በቀስ እያሳሳቀ እና በደንብ ልብ ሳንለው ወደ ውስጣችን ይገባል። ከምግብ አይተናነስም። ነገር ወደ ውስጣችን ገብቶ ከጨረሰ በኋላ ግን አዕምሯችን ውስጥ ይቀመጣል። ነገር የሚገባበት መንገድ ለምሳሌ በማየት፣ በመስማት፣ በማንበብ እና በመሳተፍ ነው። አንድ ሰው ያልሆነ ነገር ወደ ውስጡ ከገባ ሊያብድ ሁሉ ይችላል። የሚበሳጭ እና ጠበኛ ሊሆን ይችላል። ጥሩ ነገር ወደ ውስጡ እንዲገባ መምረጥ የቻለ ሰው ግን ሰላም፣ ፍቅር እና ጤንነት እሩቅ አይደሉም።
ስለዚህ ወደ ውስጣችን የሚገቡት ምግብና መጠጥ ብቻ አይደሉም። ነገርም ወደ ውስጣችን ይገባል። ለሁለቱም መድሃኒቱ ግን ለመምረጥ ያለን የእውቀት አቅም ይወስነዋል። ለምሳሌ የምግቡን አይነት፣ ጥራት እና የምንበላበትን ወቅት ካወቅነው አንድ መፍትሄ ነው። ለነገር ደግሞ በሚታይ፣ በሚነገር፣ በሚነበብ እና አሳታፊ በሆኑ ነገሮች ላይ የራሳችን ሚዛናዊ የሆነ አስተናጋጅ እይታ ሲኖረን ነው። ምግብ ብቻ ሳይሆን ነገርም ወደ ውስጣችን ይገባል።
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች