የጽሁፉ አላማ፤ በተፈጥሮ ምልክትና በሰው-ሰራሽ ምልክት መካከል ያለውን ልዩነት ለማሳየት ነው፡፡ መጀመሪያ ከቀላሉ ልጀምር፡፡ የመጀመሪያው ዙር ላይ፤ የተፈጥሮ ምልክት ማየት እንደሚቻል ጠቅሸ ነበር፡፡ ምልክቱን ካየንና ከተሰማን በኋላ፤ ተመሳሳይ መፍትሄ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ባጭሩ ጠቅሸ ነበር፡፡ ከዛ በኋላ ደግሞ ሰው-ሰራሽ ምልክት ምን እንደሆነ ለማቅረብ አስቤ ነበር፡፡ ባጭሩና በቀላሉ ተፈጥሮና ሰው-ሰራሽ ምልክቶችን ለማነጻጻር እንሞክር፡፡
የተፈጥሮ ምልክት በሚገጥመን ጊዜ፤ የሚሆነውንና የሚያስከትለውን ውጤት በአንድ ጊዜ እናውቀዋለን፡፡ ሰው-ሰራሽ ምልክት ከሆነ ግን፤ የሚሆነውና የሚያስከትለው ውጤት ልክ እንደ መልክና ጸባያችን ይለያይል፡፡ አሁን ምን ማለት እንደፈለኩ ባጭሩ ላስረዳ! የተፈጥሮ ምልክት ከሆነ፤ ለምሳሌ ሲደክመን ለማረፍ እናስባለን፡፡ እንቅፋት እንዳይመታን እንጠነቀቃለን፡፡ ከዝናብ ለማምለጥ እንቻኮላለን፡፡ ከመሸ በኋላ፤ ወደቤት ገብተን ረጋ ብሎ ማረፍ እንወዳለን፡፡ ከራበንና ከጠማን ለመብላትና ለመጠጣት እንፈልጋለን፡፡ ተጋልጠን እንዳንታይ፤ ልብስ እንለብሳለን፡፡ ከዚህ ያነሰ፤ ወይም የበለጠ መፍትሄ የለንም፡፡ መፍትሄውን በፍጥነትና በአንድ ጊዜ እናውቀዋለን፡፡ የተፈጥሮ ችግሮችን ለማቃለል፤ የታወቀ፤ የሚሰራና አንድ አይነት የሆነ የጋራ መፍትሄ አለን፡፡
መፍትሄው ብቻ ሳይሆን ውጤቱንም ጭምር ገና ሲጀመር እናውቀዋለን፡፡ ለምሳሌ፤ ከበላን እንደምንጠግብ፣ ከጠጣን፤ ጥማችን እንደሚቆረጥ እናውቃለን፡፡ አያሳስትም፡፡ የሰው ልጅ የሚግባባበት አንዱ ጥሩ አጋጣሚ፤ በተፈጥሮ ፍላጎቱ ላይ መሰረት አድርጎ ነው ብየ አስባለሁ፡፡ ምናልባት ይሄ ከአራዊትና እንሰሳት ጋር ያመሳስለናል፡፡ እኔ በበኩሌ ይኸ በጣም ያስገርመኛል፡፡
ሰው-ሰራሽ ምልክት፤
ሰው-ሰራሽ ምልክት የሚያስፈልገን፤ በተፈጥሮ ምልክትና መፍትሄ ብቻ፤ ተገድቦ መኖር ስለማይቻል ነው፡፡ እንደምታውቁት በምግብና በመጠጥ ብቻ ተገድቦ ዝም የሚል ሰው፤ ሰው መሆኑ ይቀንስበታል፡፡ በህይወታችን ውስጥ፤ ሌላም የሚያስፈልገን ነገር ሞልቷል፡፡ ለምሳሌ ሰላም እንመኛለን፡፡ መከባበር እንወዳለን፡፡ ማደግ እንፈልጋለን፡፡ ለዚህ የሚሰራ መፍትሄ ባይጠፋም፤ እስካሁን ድረስ ግን፤ በተፈላጊነቱ መጠን ስራ ላይ አልዋለም፡፡ ምክንያቱም ሰላም፣ መከባበርና ማደግ፤ የውስጥና የግል ፍላጎታችን ጋር የተያያዘ ስለሆነ ነው፡፡ ልክ እንደ ተፈጥሮ ምልክት፤ የተለመደና አንድ አይነት የሆነ መፍትሄ የለውም፡፡ በሰላም ለመኖር፣ ለመከባበርና ለማደግ ይሰራል ብለን የምናሳየው ምልክትና የምንጠቀምበት መፍትሄ እስካሁን ድረስ አልሰራም፡፡ ለምን አልሰራም?
ሰው-ሰራሽ ምልክት የሚያስፈልገን፤ በተፈጥሮ ምልክትና መፍትሄ ብቻ፤ ተገድቦ መኖር ስለማይቻል ነው፡፡ እንደምታውቁት በምግብና በመጠጥ ብቻ ተገድቦ ዝም የሚል ሰው፤ ሰው መሆኑ ይቀንስበታል፡፡ በህይወታችን ውስጥ፤ ሌላም የሚያስፈልገን ነገር ሞልቷል፡፡ ለምሳሌ ሰላም እንመኛለን፡፡ መከባበር እንወዳለን፡፡ ማደግ እንፈልጋለን፡፡ ለዚህ የሚሰራ መፍትሄ ባይጠፋም፤ እስካሁን ድረስ ግን፤ በተፈላጊነቱ መጠን ስራ ላይ አልዋለም፡፡ ምክንያቱም ሰላም፣ መከባበርና ማደግ፤ የውስጥና የግል ፍላጎታችን ጋር የተያያዘ ስለሆነ ነው፡፡ ልክ እንደ ተፈጥሮ ምልክት፤ የተለመደና አንድ አይነት የሆነ መፍትሄ የለውም፡፡ በሰላም ለመኖር፣ ለመከባበርና ለማደግ ይሰራል ብለን የምናሳየው ምልክትና የምንጠቀምበት መፍትሄ እስካሁን ድረስ አልሰራም፡፡ ለምን አልሰራም?
ምክንያቱም ለሰላም የምንጠቀምበት አስተሳሰብ፣ ለመከባበር የምናሳየው ፍላጎት፣ ለማደግ ያለን አላማ ልክ እንደ ረሃብና መብላት፤ ልክ እንደ ጥማትና መጠጣት፤ ልክ እንደ ዝናብና መጠለል፤ ልክ እንደ ጨለማና መብራት አይደለም፡፡ አንድ አይነት መፍትሄ የለውም፡፡ ለሰላም፣ ለማደግና ለመከባበር ከሆነ ግን በአንድ ጊዜና ባቋራጭ የሚገኝ መልስ የለም፡፡ ለዚህ ደግሞ በቂ ወይም ተቀራራቢ የሆነ መፍትሄ፤ እስካሁን ያልተገኘው እኛ መጥፎዎች ሆነን አይደለም፡፡ የሚፈለገው አንድ አይነት ውጤት ቢሆነም አንድ አይነት መፍትሄ የለውም፡፡ የሚሰሩትን መፍትሄወች መለየትና የታሰበው ውጤት ላይ ፍሬ እንዲያሳዩ ማድረግ ፈተና ስለሆነ ነው፡፡ ፈተናው ከባድ ሆኖ ሳይሆን ለመፍትሄው የሚሰጠው ትኩረት ዝቅተኛ በመሆኑ ነው፡፡ መፍትሄው ከሰራ ውጤቱ ይመጣል፡፡
ቁጭ ብሎ ውጤቱ ላይ ብቻ ማሰብ ዋጋ የለውም፡፡ ዝም ብሎ ልክ እንደ እቃ ምንም ሳያደርጉ፤ አርፎ ቁጭ ማለትም ውጤት አያመጣም፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ለመድረስ አስቧል እንበል፡፡ የውጤቱ መዳረሻ አዲስ አበባ ነው፡፡ መፍትሄው ደግሞ በመኪና ሊሆን ይችላል፡፡ በግር መሄድ ሊሆን ይችላል፡፡ ባውሮፕላን መሳፈር ሊሆን ይችላል፡፡ በቅሎ ላይ ተፈናጦ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰወየው ፈጥኖም ይሁን ዘግይቶ ወደ አዲስ አበባ መድረሱ አይቀርም፡፡ ሁሉም መፍትሄወች ይሰራሉ፡፡ ከደሴ ወደ አዲስ አበባ ለመድረስ፤ መስመሩ የባቡር ሃዲድ የለውምና በባቡር መሳፈር አይችልም፡፡
በኢትዮጵያ 2ሺ 13 ላይ በባቡር እችላለሁ ብሎ ካሰበ የማይሰራ መፍትሄ አስቧል ማለት ነው፡፡ ሰወየው ባቡር ለምን እንደፈለገ ትክክለኛ ምክንያቱ አይታወቅም፡፡ ግን መገመት ይቻላል፡፡ መንገዱ እንዴት እንደሆነ አልገባውም ወይም እየቃዠ ነው ወይም አላጣራም፡፡ ለማንኛውም ሰላም እንዲሰፍን፣ መከባበር እንዲኖር፤ ማደግ እንዲመጣ፤ ነጻነት እንዲስፋፋ፤ የሚሰራ መፍትሄ ያስፈልገናል፡፡ ልክ ባቡር እንደፈለገው ሰውየ መሆን የለብንም፡፡ በሚቀጥለው ተከታታይ ዝግጂት በዚህ ዙሪያ ላይ የማቀርበው ሃሳብ አለኝ፡፡ ባቡር እንደፈለገው ሰውየ እንዳልሆን እጠነቀቃለሁ፡፡ ይከታተሉ፡፡ መጀመሪያ ላይ እንደጠቀስኩት፤ የተፈጥሮና ሰው-ሰራሽ ምልክቶች እንዴትና ምን እንደሆኑ ያቀረብኩት መጠነኛ ትንታኔ፤ ጠቃሚ እንደሆነ ተስፋ አለኝ፡፡
This policy contains information about your privacy. By posting, you are declaring that you understand this policy:
This policy is subject to change at any time and without notice.
These terms and conditions contain rules about posting comments. By submitting a comment, you are declaring that you agree with these rules:
Failure to comply with these rules may result in being banned from submitting further comments.
These terms and conditions are subject to change at any time and without notice.
የተሰጡ አስተያየቶች