Skip to main content
ቆንጆ አስተሳሰብ እንዴት ይሰራል?

መሰራታዊ የኮምፕዩተር እውቀት፤ ክፍል 1

Mejemer Fantaw Tesema Norway Ethiopia Amharic Tatariw mejemeriya

ኸን የስራ ክንውን ለመፈጸም ኮምፕዩተር በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ ከታች የቀረቡት አራቱም መሰረታዊ ክፍሎች ኮምፕዩተሩ እንደ ኮምፕዩተር እንዲሆንና ትእዛዞቹም እንዲፈጸሙ ያስችሉታል፡፡ በአይነትም ሆነ በትልቅነት የተለያዩ ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ ደስክቶፕ፣ ላፕቶፕና ታብሌት የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ሁሉም አይነት ኮምፕዩተሮች ከአካል መጠን ጀምሮ እስከ ፍጥነትና አቅም ልዩነታቸው በስተቀር መሰረታዊ አሰራራቸው ይመሳሰላል፡፡ ሁሉም ትእዛዝ ተቀባይና ፈጻሚ ናቸው፡፡

፩)ኮምፕዩተር ውስጣዊ አካል አለው፡፡ ትእዛዝ ለመቀበልና ለማሰብ ሰዋዊ ያልሆነ ጭንቅላት አለው፡፡ ይኸ ጭንቅላት ፕሮሰሶር / Processor ይባላል፡፡ ሰነዶችና ዴታወችን ማስቀመጫ ካዝና አለው፡፡ ይኸ ካዝና ሃርድ-ድራይቨ / Hard drive ይባላል፡፡ የሚታዩ ነገሮችን ማሳያው ላይ እየታዩ እንዲቆዩ የሚያደርግ ራም / RAM ወይም ጊዚያዊ ተሸካሚ የሚባል ጉልበት አለው፡፡ ድምጽ እንዲከናወን የድምጽ ካርድ / Sound Card አለው፡፡ ቪዴወ እንዲታይ የቪዴወ ካርድ / Graphic Card አለው፡፡ ሁሉም አካሎቹ እርስ በርስ ግንኙነት እንዲያደርጉና ትእዛዝ እንዲቀባበሉ እናት-ካርድ / Motherboard የሚባል ዋና ካርድ ላይ በየቦታቸው ይሰካሉ፡፡

፪)ኮምፕዩተር የውጭ አካላዊ ክፍሎችም አሉት፡፡ ለምሳሌ የምንሰራውን እንዲናይ የሚያደርግ ድስፕለይ ወይም ማሳያ ጋር ይያያዛል፡፡ ይኸ ማሳያ ዋና ካርዱ ላይ የተሰካው ቪዴወ ካርድ ጋር ተገናኝቶ ይገጠማል፡፡ የምንጽፍበት ኪቦርድ ወይም መጻፊያ-ገበታ ዋና ካርዱ ጋር እዲገናኝ ይሰካል፡፡ ጠቅ እያደረግን የፈለግነውን እንዲናዝ ማውስ ወይም አይጥ ዋና ካርዱ ጋር ይያያዛል፡፡ የሁሉም የውስጥና የውጭ አካል የጋራ ስም ደግሞ ሃርድዌር ይባላል፡፡ ይህ ሃርድዌር በአካል የሚታይና የሚነካ ነው፡፡

፫) ሶስተኛው ደግሞ አካላዊ ያልሆኑ ሶፍትዌር / Software ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህም ለምሳሌ ሰነድ ለመጻፍ፣ ሂሳብ ለማስላት፣ ኢንተርኔት ለማሰስ፣ ጨዋታ ለመጨወት፣ ስዕል ለመሳል፣ ፎቶና ቪዴወ ለማቀናበር ወዘተ የሚያገለግሉ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ እንደተጠቃሚው ፍላጎትና ስራ በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የሁሉም ፕሮግራሞች አጭር የጋራ ስም ሶፍትዌር ወይም የትእዛዝ ጥርቅሞች ሊባሉ ይችላሉ፡፡ ሶፍትዌር ልክ እንደ ሃርድዌር የሚነካና የሚጨበጥ አይደለም፡፡ ሶፍትዌር የማይነካና የማይጨበጥ ቢሆንም ያለሶፍትዌር ለምሳሌ ጨዋታ መጫወት አንችልም፡፡ ኢንተርኔት ውስጥ መግባት አንችልም፡፡ ሃርድዌሩ ብቻውን ምንም አይፈይድም፡፡ ትእዛዝ ማስተላለፍ አይቻልም፡፡ ልክ መኪና ነዳጅ ወይም መብራት ሳይኖራት ተንቀሳቅሳ የፈለግንበት ቦታ መድረስ አንችልም፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ እያንዳንዳቸው የኮምፕዩተሩ የውስጥና የውጭ አካሎች የራሳቸው ድራይቨር /Driver ወይም አስማሚ የሚባል ሶፍትዌር አላቸው፡፡ ለምሳሌ የድምጽ ካርዱ የድምጽ ካርድ መሆኑን ኮምፕዩተሩ ማወቅ አለበት፡፡ መጻፊያ ገበታው መጻፊያ ገበታ መሆኑ ማወቅ አለበት፡፡ ይኸንን የሚያስተሳስር አስማሚ ሶፍትዌር እያንዳንዳቸው አካሎች አላቸው፡፡

፬) አራተኛው ክፍል ደግሞ ኦፕሬቲንግ ስይስተም / Operating Systm (OS) ወይም ግብረተ ሲስትም ይባላል፡፡ የግብረተ ሲስተሙ ዋና ሚና ካላቸው ውስጥ አንዱ ክፍል ነው፡፡ ብዙ ሰወች ግብረተ ሲስተሙንና ሶፍትዌርን አደባልቀውና አደናግረው ይነጋራሉ፡፡ ግን በቀጥታ ትክክል አይደለም፡፡ ባጭሩ ዋናው የግብረተ ሲስተሙ ስራ የኮምፕዩተር የውስጥና የውጭ አካል እና ሶፍትዌሮች በአንድ ላይ ተጣጥመው ወይም እጅና ጓንት ሆነው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡ ለምሳሌ ዊንዶውስ፣ ማክ፣ ሊነክስ የመሳሰሉት ግብረተ ስይስተም ናቸው፡፡ የግብረተ ሲስተሙ ዋና ተግባር የውጭና የውስጥ አካላት እንዲሁም ሶፍትዌሮች ተቀናጅተውና ተስማምተው መስራት እንዲችሉ የሚያደርግ ነው፡፡ እነዚህ አራት ክፍሎች እንዴት እንደሚሰሩ በሚቀጥለው ገጽ ቀርበዋል፡፡

firehiwot Wed, 02/23/2022 - 06:55

Computer knowledge

Add new comment

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.