Mejemer ን ለጓደኛ ይንገሩ!
መጀመር ላይ ምን አለ?
➯ ማሰብና መቁጠር ይመሳሰላሉ➯ መከባበር ከፍቅር ይበልጣል
➯ የባህሪ እንጂ የሃገር መጥፎ የለም
➯ ሞኝነትና ደግነት ይለያያሉ
➯ ጠንካራ ባህሪ በልምምድ ይገኛል
➯ ሰው መሆን ብቻ በቂ አይደለም
➯ አንደኛ ደረጃ አስተሳሰብ ይቆያል
➯ የሚወዱትን ስራ አሳደው ያግኙት
➯ መሰረታዊ የኮምፕዩተር ዕውቀት
➯ ለልጆች የአማርኛ ፊዴላት
➯ የለማጁ ግጥም፣ ፌዝና ልብ-ወለድ

እንኳን ደህና መጡ!
ለሚሰሩ እጆች፣ ለሚወዱ ልቦችና ለሚያስቡ አዕምሮዎች፤ሰው መሆን ብቻውን በቂ አይደለም።
ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ ሁላችንም የተሻለ ሰው መሆን እንችላለን።
mejemer.com
ለሚሰሩ እጆች

ለሚወዱ ልቦች
ልባችን እንዲሰማው የሆነ ነገር ላይ መካፈል፣ ማየትና መስማት አለብን፡፡ ሌሎች የሚያሳዩትን ፍላጎት፣ ችግርና ደስታ ለማወቅ ልባችን ክፍት መሆን አለበት። የብዙ ኢትዮጵያውያን ዋነኛ ችግር የግላችን ስሜት ስራ ይበዛበታል። የጋራ ችግርና ደስታ ላይ ንቁ የሆነ እይታ ሲኖረን ለችግሮች መፍትሄ ለማግኘት እና ለደስታው ተካፋይ ለመሆን ይቀላል።
ለሚያስቡ አዕምሮዎች

መሰረታዊ የኮምፕዩተር እውቀት
ኮምፒውተር በተሰጠው መመሪያ መሰረት አስልቶ ስራዎችን የሚያከናውን ማሽን ነው። ቅደም ተከተል እና መመሪያዎቹ ግን ለኮምፕዩተሩ በሚገባው ቋንቋ ተደርገው በሰው የተሰሩ ናቸው። ኮምፕዩተሩ ስራውን ሲሰራ ከሰው በብዙ እጥፍ ይፈጥናል። መሰረታዊ ነገሩ በቀላሉ እንዴት እንደሚሰራ ለ9 ተከፋፍሎ ቀርቧል። መልካም እድል!
ዘመናዊ ስራ አፈላለግ


እንኳን ወደ "መጀመር" መጡ!
ሰላም! ፋንታው እባላለሁ፡፡ በችኮላ አስበን የመጨረሻ ውሳኔ በምንሰጥ ጊዜ ስህተት ለመስራ እድሉ ሰፊ ነው። ስህተት መሆኑ በምን ይገለጣል? አቅጣጫው ሲታይ ወይስ ችግር ከደረሰ በኋላ? በየጊዜው እሳት ከማጥፋት ይልቅ ዘላቂ መፍትሄ ማግኝት ይሻላል። ህይወታችን ውስጥ ስህተት ለመቀነስ የአስተሳሰብ ልምምድ እና ተግባር ይፈልጋል። ልብ ለሚልና ልምምድ ለሚወድ ሰው ህይወት እንደምናስባት ከባድ አይደለችም። ለምሳሌ እንክርዳድ ከስንዴ ለመለየት አይናችን ስለሚያይ ቶሎ እናውቀዋለን። ክፉና ደጉን ለመለየት ደግሞ አዕምሯችን ማየት ይችላል። የአይን እና የአዕምሮ እይታ ግን ይለያያሉ። አዕምሮ ጥልቅ ልምምድና ጊዜ ይፈልጋል። ታዲያ ምን ይጠብቃሉ? ምን ይመስልዎታል?
የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ጠላት ኋላቀር አስተሳሰብ ነው፡፡ የችግር ሳይሆን የመፍትሄ አካል ለመሆን ፈቃደኛ ለሆነ ሰው መፍትሄ አለው።