Skip to main content
ሰው መሆን ብቻውን በቂ አይደለም፤ መጀመር።

ግጥምና ቀልዶች

ቀና ብለህ እየው ልጄ ነው ይበልህ!

ሰበብ እያበዛህ፣
መዘምን አለፈህ፣
መሰልጠን ቀረብህ፣
እሱ ያውቃል ብለህ፣
አንገትህን ደፍተህ፣
አይንህን ጨፍነህ፣
አዕምሮህን ዘግተህ፣
ልብህንም ደፍነህ፣
ምንም አይታይህ፣
ወደታች እያየህ፣
ክፉና በጎውን መለየት አቅቶህ፣
የሰነፈው ባህል እንዲህ ጠልፎ ያዘህ፣
ወይ ባስተሳሰብህ፤ ወይ ባስተዳደግህ፣
ፊትህን ደብቀህ፣
እንዴት አርጎ ይስማህ፣
እንዴት አርጎ ይይህ፡፡

ቀና ብለህ እየው፣
ባየሩ በጉሙ ሲንሳፈፍ ካየኸው፤
ያንተ ልጅ ነኝ በለው፤
ሰበበኛ እንዳልሆንክ ወስነህ ንገረው፣
ሌላ ጊዜም ቢሆን እንዳታስቸግረው
መልሱንም አዳምጠው፡፡

እንኳን አደረሰሽ 365!

እንኳን አደረሰሽ 365፣
ምንድነው የኔ እድገት?
ትምህርት ለመውሰድ ካለ ያጠፋሁት፣
ገትሮ ለመያዝ ካለ ያለማሁት፣
በጎ ወይስ መጥፎ ካፌ ያወጣሁት?
ሰው ስለመሆኔ ምንድነው ያሰብሁት?
ዝም ብዬ እያየሁ ባሪያ የሆንኩበት፣
ወይም ወገኔ ላይ ጨካኝ የሆንኩበት፣

ቀና ሃሳብ ካለኝ ለማሳየት ውጤት፣
አንድ ሁለት ብዬ የሚቆጠር ስኬት፣
ምን እንደሰራሁኝ ልኩን የማይበት፣
ውሸት የሌለበት፣
መጀመሪያ ክብር ስለ ሰው ልጅ ህይወት፣
መከበር ከፈልግሁ በሰፊው ህዝብ ፊት፡፡
መልካም አዲስ ዓመት!
ኮተት ያልበዛበት

ቀጠሮ የማንነት ማሳያ ትልቅ አጋጣሚ!

ተወጥቶ ተወርዶ የትም ሀገር ቢኖር፣
አገርቤትም ሆነ ከባህር ባሻገር፣
ጉድለት አለ ሲባል ሥሰማ ሲነገር፣
ብዙ ያገሬ ሰው ቃሉን ሳያከብር፣
እቅድ ሳያወጣ ባጋጣሚ መኖር፣
እንዲህ የገነነ አይመስለኝም ነበር፡፡

ስማችን አይጥፋ በቀጠሮ ምክንያት፣
እስኪ በቃ ብለን ዛሬ እንነሳበት፣
በሰዓቱ እንድረስ ቃል ለገባንለት፣
ቶሎ ሳንዘገይ በተባለው ሰዓት፣
ከዛ ከተባለው ቦታ ለመገኘት፣
ለቀጠርነውም ሰው ክብር ለማሳዬት፣
በደንብ ተገንዝበን የቀጠሮን ክብዴት።

በሰዓቱ መድረስ እንደምን አቃተን?
እስከመቼ ድረስ ሁልጊዜ ዘግይተን፣
በትንሿ ነገር ካልተለማመድን?
ነጻነትና እድገት መቼ እናገኛለን?

መቼ ይሆን እኔ ለውጦች የማይበት?

ቀኖቹ ተቆጥረው ወራት ይሰፍራሉ፣
ወራትም ተቆጥረው ዓመት ይሞላሉ፣
እንዲሁም ዓመታት ዘመን ይለያሉ።

የሚገርም እኮ ነው እንዲህ በድንገት፣
ይቺ ጊዜ እሚሏት አላት ብልሃት፣
ይዛ ትመጣለች አዲሱን ዓመት፣
ከተፍ ትላለች ሰው ሳይነቃባት።

ራሴን ስጠይቅ በዚህ አዲስ ዓመት፣
ቁጥር ጨመረና ምንድነው የኔ እድገት?
አዲስ ዓመት ቢሆን ልክ እንደ መስታዎት፣
ምን አንዳደረኩኝ ልኩን የማይበት፣
እያልኩ ጠየኩት እራሴ በድንገት፣
መቼ ይሆን እኔ ለውጦች የማይበት።

Subscribe to ግጥምና ቀልዶች