Skip to main content
ቆንጆ አስተሳሰብ እንዴት ይሰራል?
ለሚሰሩ እጆች፣ ለሚወዱ ልቦችና ለሚያስቡ አዕምሮዎች፤ መጀመር

ያስተሳሰብ ጀግና እንዴት መሆን ይቻላል?

mejemer fantaw Ethiopia Amharic Tatariw mejemeriya Addis Ababa amharic Fantaw Tesema

ስተሳሰብ ጀግና መሆን እራሱን የቻለ ስራና ፈተና ነው! ችግር የለም! ያስተሳሰብ ጀግና እንዴት መሆን እንደሚቻል በቀላሉ ሃሳቤን ማጋራት እችላለሁ፡፡ ይኸን የሚያስችሉ 3 ዋና ዋና ነጥቦች አብረን እንይ፡፡

1ኛ ረጋ ማለትና ጊዜ መጠቀም፤
2ኛ ልብ ማለትና ትኩረት መስጠት፤
3ኛ መለማመድና መፈጸም ናቸው፡፡

ሁኑ ዙር ላይ ረጋ ማለትና ጊዜ መጠቀም እንዴት እንደሚቻል ባጭሩ ላስረዳ፡፡ በሚቀጥለው ጊዜ የቀሩት ሁለት ነጥቦች ይቀርባሉ፡፡ የመጀመሪያው፤ ረጋ ማለት ሃሳባችንን ለማሰባሰብ ይረዳናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ጊዜ ያስፈልገናል፡፡ ለዚህም ነው በህይወታቸው ውስጥ ጥሩ ውሳኔ የሚወስኑ ሰወች ላስብበት የሚሉት፡፡ ጊዜ እፈልጋለሁ፤ አስብበታለሁ የሚሉት፡፡ ምክንያቱም ማጣራትና ማወቅ ያለባቸው ነገር ካለ ረጋ ብለው ጊዜ ይጠቀማሉ፡፡ እንቁላል ቀስ በቀስ በግሩ ይሄዳል ይባል የለ፡፡ የጥንት አባቶቻችን አባባል እስካሁን ድረስ ይሰራል፡፡ አስተሳሰብም እንደዚሁ ነው፡፡ በኛ ባህል ላስብበት ማለት ብዙም የተለመደ አይደለም፡፡ ቀስ ብለው ያሰቡበት ጉዳይ ግን መጨረሻ ላይ ውጤቱ ያማረ ይሆናል፡፡ ሁሉም ነገር ላይ ዘገምተኛ እንሁን ማለቴ አይደለም፡፡ በፍጥነት መወሰን ያለብን ነገር ካለ ቶሎ መወሰን ይቻላል፡፡ ስንናገር እንኳ ትንፋሽ መውሰድና በሰኮንዶች ውስጥ ቃላት መምረጥ መቻል በራሱ በፍጥነት መወሰን ነው፡፡

ተለይ አሁን በምንኖርበት ዘመን ብዙ መረጃወች ይደርሱናል፡፡ በመስማት፣ በማየትና፣ ተካፋይ በመሆን የተለያዩ መረጃወች ይደርሱናል፡፡ ረጋ ማለትና ጊዜ መጠቀም ብቻ ሳይሆን መመርጥ መቻልም እራሱን የቻለ ፈተና ነው፡፡ የችኮላ አስተሳሰብና ስራ ነካ ነካ ስለሚሆን የመጨረሻ ውጤቱ የሚያኮራ አይሆንም፡፡ ለምሳሌ የተባለውን ቶሎ እንዳንረሳ ረጋ ማለትና ማሳቢያ ጊዜ ያስፈልገናል፡፡ ረጋ ማለትና ጊዜ መጠቀም የሰማነውን ለማስታወስ ያግዘናል፡፡ ያየነው ደሞ አዕምሮአችን ውስጥ ቅርጽ እንዲሰራ ያደርጋል፡፡

ማስታወስ ጊዜ የሌለው ለችግር መፍትሄ የለውም፡፡ ልክ ሳያጠና ፈተና ተፈትኖ እንደወደቀ ሰነፍ ተማሪ ይቆጠራል፡፡ ከዛ ባለፈ ደሞ እያንዳንዱ ሰው የማያልቅ የህይወት ፈተና አለበት፡፡ ህይወታችን ውስጥ ብዙ ነገር ይደርስብናል፡፡ የሚሆኑትን ነገሮች ልክ እንደ ጎበዝ ተማሪ ካጠኗቸው መፍትሄ ለማግኘት ከባድ አይደለም፡፡ ሁላችንም በህይወት ውስጥ ተፈታኝ ተማሪዎች ነን፡፡ ፈተናውን ለመቋቋም የመጀመሪያው መነሻ እርምጃ ሃሳባችንን ረጋ ብለን ማጥናት ነው፡፡ ሃሳብን ረጋ ብሎ ማጥናት የሚያኮራ እንጂ የሚናቅ አቋም አይደለም፡፡

አመለ Mon, 10/26/2020 - 11:34

በጽሞና ማዳመጥ ወይም መደማመጥ በግለሰብም ሆነ በማህበረሰብ ደርጃ ለመግባባትና ለመተዋወቅ ወሳኝ ነው:: እዚህ ሀገር አብዛኛው የእኛ ሰው ከየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣን ጥያቄ ደስ ብሎን ነጻ ሆኖን ለመመለስ ስንቸገር ይታያል:: ፍላጎትም አይታይብንም ለዚህም ብዙ ምክንያቶች ልንሰጥ እንችላለን::

በተጨማሪም እኛ ከሌላ ሀገር ሰዎች የሚመጡ የግል የታሪክ የባህል የሀይማኖት ወዘተ ጥያቄዎችን ለመመለስ ከቋንቋ በተጨማሪ የእውቀትና የዝግጅት ማነስ ስላለብን እንዲሁም መጠራጠር ስለምናበዛ ከመጠየቅም ከመጠየቅም ስንቆጠብ ይስተዋላል:: በዚህም ምክንያት እኛም ስለሌላው በደንብ እንዳናውቅ ወይም ጥራዝ ነጠቅ ትንሽ እውቀት ብቻ እንዲኖረን ሲያደርግ ስለእኛም ለሌሎች በሚገባ ሳናሳውቅ ይቀራል::

tatariw Tue, 10/27/2020 - 11:42

In reply to by አመለ

ለትውውቅና የተለያዩ ነገሮች ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረን የጠቀሻቸው ምክንያቶች እንዳይከለክሉን ሁላችንም የተሻለ ማድረግ እንችል ነበር፡፡ ለአስተያየትሽ አመሰግናለሁ አመለ! መልካም ውሎ! ፋንታው

Add new comment

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.