መሆን
መከባበር በውስጡ ጉድ አለው
ይኸ ጽሁፍ ትህትና፣ መቻቻልና ፍቅር ከመከባበር ጋር ሲነጻጻሩ የትኛው እንደሚበልጥ ለማሳየት ነው፡፡ መጀመሪያ ግን መከባበር እንዴትና የት መጠቀም እንደሚቻል አንዳንድ ወሳኝ ነጥቦች ባጭሩ ላሳይ፡፡ ለምሳሌ ሰው ማክበር፣ ህግ ማክበር፣ ድንበር ማክበር፣ ሃሳብ ማክበር፣ ሃገር ማክበር፣ ስራ ማክበር፣ ችሎታና እውቀት ማክበር፣ ተፈጥሮ ማክበር፣ ቤተሰብ ማክበር፣ ታሪክ ማክበር፣ ባህል ማክበር፤ የመሳሰሉት ናቸው፡፡
አፍራሽ አስተሳሰብ ምን ይመስላል?

አፍራሽ አስተሳሰብ እንዲህ ይመስላል፡፡ ሰው ተጠቀመብኝ፡፡ ተበድያለሁ፡፡ ማንንም አላምንም፡፡ እጠራጠራለሁ፡፡ አልችልም፡፡ ዛሬ በቀኜ ጎን አልተነሳሁም፡፡ ዝናብ ስለሚጥል ተደበርሁ፡፡ የፈለገ ብለፋ አይሳካልኝም፡፡
ሰው እንደ ሚያስበውና ሚበላው ይሆናል!
ገንቢ አስተሳሰብ እንዴት ማግኘት ይቻላል?
ስኬት የሚጀምረው ከገንቢ አስተሳሰብ ነው፡፡ በተቃራኒ ደግሞ ውድቀት የሚጀምረው ከአፍራሽ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ግን ገንቢ መሆን ይወዳል፡፡ ገንቢ ለመሆን ምን ይጠበቅብናል?
በሃሳብ መጠየቅና መተዋወቅ፤ ክፍል ፪
ማውራትና መጠየቅ ብቻውን ሙሉ አያረግም፡፡ አንድ ሰው ሁሉንም ጥያቄ መፍጠር አይችልም፡፡ አንድ ሰው ለሁሉም ነገር መልስ ሊኖረው አይችልም፡፡ የሆነ ነገር ተጠይቀን የማናውቀው ከሆነ፤ ደፍረን አላውቀውም ማለት ይሻላል፡፡
በሃሳብ መጠየቅና መተዋወቅ፤
ማዳመጥና መጠየቅ ህይወታችን ውስጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ ለምሳሌ ሁላችንም በሚባል ደረጃ ስንደመጥ ደስ ይለናል፡፡ የኛን ፍላጎት ለመረዳት ሰው ዝግጁ ሆኖ ቀርቦ ፍላጎት ሲያሳይ ዋጋ እንሰጠዋለን፡፡
እንኳን ወደ ልዩ "መጀመር"ጣቢያ መጡ!
ፋንታው እባላለሁ፡፡ ኢትዮጵያ እንዴት ብላ ማደግ ትችላለች እያሉ አስበው ያውቃሉ? አስተሳሰብዎ አንደኛ ደረጃ እንዲሆን ይፈልጋሉ? ለሃገሬ ምን ላርግ እያሉ ውስጥዎ ይቃጠላል? አስተሳሰብዎን ማስተዳደርና መቆጣጠር ይፈልጋሉ? ወይስ እንደ ነገሩ ልክ እንደ እንሰሳት በእግራችን ተንቀሳቀስን ውለን ካደርን በቂ ነው? እንግዳውስ ወደ ትክክለኛ ጣቢያ መጥተዋል፡፡