Skip to main content
ሰው መሆን ብቻውን በቂ አይደለም፤ መጀመር።

ሰው እንደ ሚያስበውና ሚበላው ይሆናል!

Mejemer Fantaw Tesema Norway Ethiopia Amharic Tatariw mejemeriya መጀመሪያ መጀመር

ገንቢ አስተሳሰብ እንዴት ማግኘት ይቻላል?

ስኬት የሚጀምረው ከገንቢ አስተሳሰብ ነው፡፡ በተቃራኒ ደግሞ ውድቀት የሚጀምረው ከአፍራሽ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሁሉም ሰው ግን ገንቢ መሆን ይወዳል፡፡ ገንቢ ለመሆን ምን ይጠበቅብናል? አፍራሽ አስተሳሰብ እንዴት መቀነስ እንችላለን? ሁለቱንም ለማስረዳት ይፈቀድልኝ፡፡ ገንቢ አስተሳሰብ ለሁለት ይከፈላል፡፡

፩ኛ) ቁሳዊ አስተሳሰብ፤
፪ኛ) ሰዋዊ አስተሳሰብ፡፡

ሁለቱም አስተሳሰቦች ያስፈልጉናል፡፡ ሁለቱንም በተራ ለማስረዳት ልሞክር!
ቁሳዊ አስተሳሰብ ማለት ለምሳሌ የምንጫወትበት ኳስ፣ የምንኖርበት ቤት፣ የኤሌክትሪክ መብራት፣ የምንበርበት አውሮፕላን፣ የምንጠቀምበት ስልክ ወዘተ የፈለቀበት አስተሳሰብ ማለት ነው፡፡ ይኸ ቁሳዊ አስተሳሰብ ከራስም አልፎ ለህብረተሰብ፣ ለሃገርና ለሃገራት የሚጠቅም ነው፡፡ የዚህ ቁሳዊ አስተሳሰብ ዋና ምንጩ ህይወታችን ቀላል እንዲሆን የምናደርገው ፍላጎታዊ ትግል ነው፡፡ ምክንያቱም ለመጫወት ኳስ ያስፈልገናል፡፡ ለመኖር ቤት ያስፈልገናል፡፡ እሩቅ ሃገር ቶሎ ለምድረስ ዘመናዊ መጓጓዢያ ያስፈልገናል፡፡ ሲጨልም የኤሌክትሪክ መብራት ያስፈልገናል፡፡ ከተረዳችሁኝ ምሳሌዎቹ ብዙ ናቸው፡፡

ሰዋዊ አስተሳሰብ፤

ዋዊ አስተሳሰብ ልክ እንደ ቁሳዊ አስተሳሰብ በስም ለማስረዳት ቀላል አይደለም፡፡ ግን ልሞክር፡፡ ሰላም መባባል አስፈላጊ ቢሆንም ተራ ነገር ነው፡፡ እንኳን ሰው ቀርቶ፤ እንሰሳትና አራዊትም በራሳቸው መንገድ ሰላም ይባባላሉ፡፡ ሰዋዊ አስተሳሰብ ግን ከዚህ ከፍ ያለ ነው፡፡ ሰዋዊ አስተሳሰብ ማለት አይተንና አዳምጠን የሰወች ፍላጎትና ሁነታ ምን እንደሆነ ማወቅ መቻል ይመስለኛል፡፡ ለምሳሌ ሰወች ሲቸገሩና ሲያጡ መርዳት ባንችልም ችግራቸውን ማባባስ የለብንም፡፡ ሰወች ሲሳካላቸው አብረን የደስታቸው ተካፋይ ባንሆንም ምቀኛ መሆን የለብንም፡፡ ሰወች ሃዘን ላይ ሲሆኑ አብረን ከነሱ ጋር ተቀምጠን ባናለቅስም ልባቸው እንደተሰበረ እውቅና መስጠት ይጠበቅብናል፡፡ ገንቢና ሰዋዊ አስተሳሰብ ያላቸው ሰወች ጋር ወዳጅነት መግጠምና አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ከአፍራሽ አስተሳሰቦች ያርቃል፡፡

ዋነኛ ሰዋዊ ገንቢ አስተሳሰብ ማለት አንድ ሰው ለራሱና ለህበረሰቡ ጠቃሚ ለመሆን የጋለ ፍላጎት ሲኖረው ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ የትኛውም አስተሳሰብ በህይወታችን ላይ ከፍተኛ አወንታዊ ቅርጽ አለው፡፡ የጋለ ጥሩ ፍላጎት ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ የተሻለ ሰው እንዲንሆን ይገፋፋናል፡፡ በተጨማሪ የጋለ ፍላጎት ስለሚጮህ ውጤቱን ለማየት ይናፍቃል፡፡ ያጓጓል፡፡

አመለ Tue, 05/19/2020 - 11:52

ሁሉም ጠቃሚ ሀሳቦች ናቸው:: እይታዎችህን እወዳቸዋለሁ ፋንታው:: አንዳንዶቹም በብዙ መልኩ ትንታኔ የሚፈልጉ እንዳመለካከታችና እንደ ህይወት ገጠመኞቻችን በተለያየ መልክ የሚተረጎሙ ቢሆኑም ግልጽ ሀሳቦች ናቸው:: እናመሰግናለን

tatariw Fri, 05/29/2020 - 11:57

In reply to by አመለ

በዝቶ እንዳይሰለች በማሰብ ብዙ ትንተና ውስጥ አልገባሁም፡፡ ልክ ነሽ አመለ! ብዙው ነገር እንዳመለካከታችን ይለያያል፡፡ በተቻለ መጠን ለማሳጠርም ሞክሬአለሁ፡፡ ያሁኑ ዙር ላይ ለመክፈል ትንሽ ስላስቸገረኝ የበዛ ይመስለኛል፡፡ ብዙውን ጊዜ፤ አንድ ጽሁፍ ከ300 ቃላት እንዳያልፍ እፈልጋለሁ፡፡ ከዛ ካለፈ አንባቢያን ሲያዩት ብዙ ስለሚመስል የማንበብ ፍላገታቸው አንሶ እንዳያልፉት በመስጋት ነው፡፡ እያንዳንዱ አረፍተ ነገርም ከ 12 ቃላት በላይ ባይሆን ሃሳቦቹ ግልጽ ይሆናሉ፡፡ ምናልባት ለመረዳትም ይቀል ይሆናል፡፡ ባሁኑ ጌዜ ህይወት ሩጫ ነው፡፡ አንድ ነገር ግልጽ ላርግ፡፡ ማንኛውም ሰው ጠበብት መሆን ይችላል ያልሁት በምክንያት ነው፡፡ ለምሳሌ ቤት ቀለም በመቀባት ሊሆን ይችላል፡፡ ምግብ አሳምሮ በመስራት ሊሆን ይችላል፡፡ መኪና በመንዳት መሆን ይችላል፡፡ ነገሩ ብዙ ነው፡፡ ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው በጥራት አስተዋጾ ማድረግ ይችላል ለማለት ነው፡፡ ጠበብት ማለት ተአምራዊ ነገር ስላልሆነ እያንዳንዱ ሰው አስፈላጊ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ አመሰግናለሁ! ፋተ

Add new comment

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.